Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተር ዋዲ ፋቲህ ይሰኛል። የሰለመበትን ገጠመኝ እንዲሀ እያዋዛ ይተርክልናል። እንደ አውሮፓውያን | ISLAM IS UNIVERSITY

ዶክተር ዋዲ ፋቲህ ይሰኛል። የሰለመበትን ገጠመኝ እንዲሀ እያዋዛ ይተርክልናል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1978 አሌክሳንድሪያ በሚገኘው ሙሀረም ቤክ ሆስፒታል ውስጥ ዶክተር ሆኜ አገለግል ነበር። በወቅቱ በድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን አንጋፋ ዲያቆን፣ የኮፕቲክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህር ነበርኩ።

ከእለታት በአንዱ ቀን ሳንታ ሉቺያ ምግብ ቤት ኩሽና እሳት ተነሳ።  አምቡላንሶች ቁስለኞችን ይዘው ወደ ሆስፒታላችን ከነፉ። ወደኔ ክፍል የገባው ታካሚ በጣም የተጎዳ ሰው ነበር። ምግብ አብሳይ ነው። ሰውነቱ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ ከስሏል። ያቃስታል የህመም ጩኸት ያሰማል።

ከልምድ አንፃር በ24 ሰአት ውስጥ እንደሚሞት ገምቼ ነበር። ሰውነቱ ውስጥ ያለው ቃጠሎ እንዲፀዳለት pain killers ሰጠሁት። በጣም በተረጋጋ መንፈስ ዶክተር ቆይ አለኝ ለስራ ባልደረቦቼ መድሀኒታቱን እንዳይግቱት ምልክት እየሰጠ። በጀርባው ተንጋሎ ማውራት ጀመረ
"ከአላህ ጋር ጥብቅ ትስስር አለኝ። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እንደምሞት አውቃለሁ። አደራ ራስህን አታድክም መድሃኒቶችንም በከንቱ አታባክን። ሞትን አልፈራም ግና የህመም ስሜት በተሰማኝ ቁጥር ቁርአንን እየቀራሁ አላህን መገናኘት እፈልጋለሁ" አለና ቁርአንን ከፍ ባለ ድምፅ በሚማርክ ዜማ ማንበብ ጀመረ።

በማግስቱ ጠዋት ሆስፒታሉ አልጋ ላይ አላገኘሁትም ነበር። ነርሶቹን ጠየቅኩ ከመሀላቸው አንዱ "ነፍሱ እስክትወጣ ቁርአን እየቀራ ነበር። ውሃና አንድ ሲሪንጅ ብቻ ነው የጠየቀው" አለኝ ምስሉ በምናቤ ተደቀነ።

ሞትን እንዴት አይፈራም? በጌታው ላይ ምን የሚሉት መተማመን ነው ያለው? ከእርሱ ጋር መገናኘትን እንዴት ቢናፍቅ ነው? ይህ መጽሐፍ (ቁርአን) ቃላቶቹ የተዳሰሱበትና በአስደማሚ አረፍተ ነገሮች የተዋቀረበት ሚስጥርስ ምንድን ነው? ራሴን ጠየቅኩ። ስለኢስላም ለመረዳት ጣርኩ። አነበብኩ። ከአስራ አምስት አመትበኋላ በ1993 ዓመት አላህ እስልምናን ወፈቀኝ። ቁርአንና ትርጓሜውን ስማር ያ ሰው ከአመታት በፊት የተናገረውን ተረዳሁ። ባስታወስኩት ቁጥር አላህ ሆይ እዘንለት ይቅርም በለው ቀብሩንም የጀነት ጨፌ አድርግለት ስል አላህን እማፀነዋለሁ።

በምላስህ ዳዕዋ ማድረግ ቢከብድህ በተግባርህ ሰዎችን ወደ ኢስላም ተጣራ።