Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ማያ/መነጽር

የቴሌግራም ቻናል አርማ intheeyeoforthodox — የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ማያ/መነጽር
የቴሌግራም ቻናል አርማ intheeyeoforthodox — የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ማያ/መነጽር
የሰርጥ አድራሻ: @intheeyeoforthodox
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 344
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ማንኛውንም ነገሮች( አስተምህሮ ፣ ትምህርችም ፣ሃሳቦችም....በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እይታ/ማያ ወይም መነፀር ተመርምረው ተከሽነው የሚቀርቡበት ቻናል ብቻ ነው ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ማያ/መነጽር ርዕዮት ርዕይ ምልከታ ምንድነው ?
እውነተኛ መነጽር ፣ያልቆሸሸ ፣ያላደፈ ማያ:- ቀዩን ቀይ ጥቁሩን ጥቁር ነጩን ነጭ...አድርጎ ያሳያልና÷

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-17 13:34:03 በስመ አብ ፥ ወወልድ ፥ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ፩ አምላክ!

መልእክት ለኦርቶዶክሳውያን!

ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ከጥፋት ማን ይታደጋት?

ላለፉት 493 ዓመታት ክርስትናን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የምዕራቡ ዓለም ሚሲዮናውያን፥ ፖለቲከኞቻቸውና ዐረቡ ዓለም በብዙ ደክሟል። በተለያየ ጊዜ (ከግራኝ አህመድ እስከ ጣልያን ወረራ ድረስ) ብዙ ኦርቶዶክሳውያን ቢጨፈጨፉም ክርስትና ግን ጠላቶቻችን ያሰቡትን ያህል ሊጠፋና ሊዳከም አልቻለም፡፡

ከ1966 ወዲህ ግን የምዕራቡ ዓለም ጅቦችም ሆኑ የዐረቡ ዓለም ተኩላዎች የጥቃት መልካቸውን ቀይረው ብዙ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ የምዕራቡ ዓለም ፀረ ኦርቶዶክስ መሪዎች ሴኪውላሪዝም (ዓለማዊነት)፥ ምሥራቃውያን ደግሞ በኮሙኒዝም ስም በሃገራችን የጎሳ ፖለቲካ እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ የተፈጠረው የገሳ (ብሔር?) ፖለቲካ ደግሞ አማራንና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጠላት የፈረጀ ነበርና፥ በዚህ ሰበብ ባለፉት 34 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ሲታረዱ ኖረዋል፤ ሚሊየኖች ደግሞ ተፈናቅለው ሰቆቃን ሲቀበሉ ኑረዋል፤ አሁንም ቀጥለዋል፡፡

ዐረቡ (አክራሪው) የወሀቢ እንቅስቃሴ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጠላት የፈረጀና ማጥፋትን እንደ አላማ ይዞ የቆየ ነው፡፡ ለመቶዎች ዓመታት ከውጪ በማሥረግ ክርስትናን ከኢትዮጵያ ማጥፋት ባለመቻሉ፥ ከ40 ዓመታት በፊት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ወጣቶችን ከኢትዮጵያ ምድር በመመልመልና ወደ ውጪ በመውሰድ፥ ጅሃዳዊ ስልጠና እንዲወስዱ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለዋናውና የመጨረሻው ጂሃዳዊ ዘመቻ እንድትመች ለማድረግ ባለፉት 4 አሠርት ዓመታት ሲያመቻቹ ቆይተዋል፡፡ በዚህም ምጣኔ ሀብቱን፥ የፖለቲካ፥ ወታደራዊና የደህንነት መዋቅሩን በሥራቸው ለማድረግ የሠሩት ሥራ ፍሬ አፍቶላቸው፥ አሁን ለመጨረሻው ዘመቻቸው እየተዘጋጁ ይገኛል፡፡

ከሁሉ የከፋው ደግሞ "መንግሥት" ነኝ ብሎ የተቀመጠውና፥ ራሱን "ብልጽግና" ብሎ የሚጠራው አካል፥ በወዲህ "የኦሮሚያ ሪፐብሊክን" ለመመሥረት፥ በወዲያው ደግሞ አስተዳደሩ ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ በጀመረው ዘመቻ "አማራ እና ኦርቶዶክስ" የሚል ታፔላ በለጠፈባቸው ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸም ከጀመረ ድፍን 4 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የሰሜኑ ጦርነትም አማራውንና ትግሬውን ከጎዳው ይልቅ ኦርቶዶክሳውያን እርስ በርሳቸው እንዲፋጁ የተደረገበት ነበር፡፡

በዚህ ሁሉ መካከል ግን በደቡብ፥ በምስራቅና በምዕራብ ይህ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ እየታረደ ፥ ወጣት ክርስቲያኖች ምንም እንዳልተፈጠረ ቁጭ ብለን እንመለከታለን፡፡ በተለይ በአዲስአበባና በክልል ከተሞች (ይልቁንም በአማራ ክልል) የምንኖር ኦርቶዶክሳውያን፥ የወገኖቻችን መታረድ፥ መደፈር፥ መታሠርና መሰደድ (ነገ በኛ ላይ የማይደርስ ይመስል) ትኩረት ያልሰጠነው ነገር ሆኗል፡፡

ትንሽ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥቷል የሚባለው ወጣት እንኳን፥ ለጥምቀት ማንጠፍና ፋሽን ልብስ ቤተ ክርስቲያንን ይታደጋት ይመስል፥ በዓመት ለጥቂት ቀናት ብቻ ወደ ቁምነገር ሲመጣ ይታያል፡፡

ሰለዚህ ምን እናድርግ?

1፡ እንደ ሃገር ኢትዮጵያ፥ በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ የኅልውና አደጋ ላይ እንዳሉ እንወቅ፡፡

2፡ ከኅልውና የሚቀድም ምንም ነገር የለምና ከአክራሪው፥ ከፕሮቴስታንቱ፥ ከፖለቲከኛውና ከዘረኛው ቡድን ራሳችን፥ ሃገራችንና ቤተ ክርስቲያንን ለመታደግ እንዘጋጅ፡፡

3፡ በተበታተነ መንገድ መጓዝ ለጠላት ይመቻልና፥ በአንድ ልብና ዕዝ ሥር ሆነን የምንታገልበትን አሠራር እንከተል፡፡
4፡ እኛን ሊያዘናጉ ከሚችሉ ማናቸውም ነገሮች ራሳችንን እናቅብ፡፡

5፡ በየዕለቱ አጀንዳዎቻችን ቤተ ክርስቲያናችንና ሃገራችን ይሁኑ፡፡

6፡ ችግሩ ያልገባቸውን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ፈጥነን እናንቃቸው፡፡

7፡ ሁሉም ነገር የሚሳካው የእግዚአብሔር ረዳትነት ሲኖር ነውና በጸሎት እንጠይቅ፤ ንስሃም እንግባ!

ይህንን መልእክት ችላ ብንለው፥ በሰማይም ሆነ በምድር ለሚደርስብን ነገር ሁሉ ተጠያቂዎቹ እኛው እንሆናለን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
41 views10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 13:25:51 የመልካም ወጣት አባል መሆን ያስወግዛልን?

በመጀመሪያ የዚህ ተቋም መሥራችና ሥራ አስኪያጅ የሆነው ፓስተር ባስተላለፈው መልእክት ላይ የመልካም ወጣት ስልጠናን፡ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ኦርቶዶክሶች ረቡዕና ዓርብ ቀን እየጾማችሁ ወንጌል መማር ትችላላችሁ ብሏል
እና አስገድዶም ሊያበላቸው ያምረው ኖሯል እንዴ?
ግን የሚጾሙት የጴንጤነቱ ትምህርት እስኪሠርጽላቸውና የሚጾሙት ጼንጤ እስኪሆኑ ድረስ ነው አይደል?
ጾም ሙሉ የሚሆነው እየጾሙ ሲጸልዩ ሲመጸውቱ እንጂ እየጾሙ የፓስተር ትምህርት በመውሰድ ነው?
ደግሞ አስቡት እንጂ እዛ ሁሉ የፕሮቴስታንት መሃል የሚገኙ ጥቂት ኦርቶዶክሶች እንዴት አይነት የሞራል ድቆሳ ደርሶባቸው ጫናው ምን ያህል እንደሚሆን አስቡት እስኪ?
ደግሞስ የሌላ ቤተ እምነት ወንጌል እየተማሩ ኦርቶዶክስነት አለ እንዴ?
በጾም ከሚበላው ሥጋ በላይ በእየ እለቱ የሚሰሙት የሌላ ቤተ እምነት ትምህርትና ኑፋ* ከሥጋው አይበልጥምን?
ኧረ ለመሆኑ አንድ ኦርቶዶክስ የሌላ ቤተ እምነት የፕሮቴስታንት ስብከትን ዘወትር እየሰማ ጤነኛ ኦርቶዶክስ ነኝ ማለት ይችላልን?

በመሠረቱ እዚህ ፕሮግራም ላይ መሳተፍና የስልጠናው አባል መሆን ብቻውን ከሃይማኖት አያስወግዝም ወይ?
አንድ ሰው ከቤተ ክርስቲያን ተወግዞ ከሚለይባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በሌሎች ቤተ እምነቶች ቦታ ማለትም በፕሮቴስታንት አዳራሽ ውስጥ አብሮ ያመለከ፣ አብሮ የጸለየ፣ አብሮ ትምህርት የሚከታተል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ከመንጋዋ ትለየዋለች
ለመመለስ ቢፈልግ እንኳን ንዑሰ ክርስቲያን ብላ በቀኖናና በትምህርት ጊዜ ወስዶ ከተረዳ በኋላ ይመለሳል
ደግሞም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ"ከማያምኑት ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ ይላል 2ኛ ቆሮ 6:14 ከዚህ፡በላይ የማይመች ነገር የለም
ምንፍቅ*ን በልዩ ጥቅማ ጥቅም፡ጋር ቀላቅሎ ማታለልም ውጉዝ ነው"እስመ ኢኮነ ከመ ብዙኃን እለ ይትሜነይዎ ለቃለ እግዚአብሔር በካልእ ዳእሙ በንጽሕ ወከመ እም ኀበ እግዚአብሔር ንነግር በቅድመ እግዚአብሔር በእንተ ክርስቶስ
የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን 2ቆሮ 2:17 እንዲል በወጣት ስም ከሱስ በማውጣት ስም ኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ ዘረፋ ይቁም
ስለዚህ የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ማንም ኦርቶዶክሳዊ እዚህ ቦታ ገብቶ በነፍሱ እንዳይሞት ጥንቃቄ እናድርግ እንምከር
እኛ ቤት የሚለውጥና መልካም የሚያደርግ ትምህርትና ስብከት ጠፍቶ ነው?
ስልጠና የሚሰጥ አንደበተ ርቱዕ ስልጠና ሰጪ ስለሌለን ነው አንድ ፓስተር ፍለጋ ይሄ ሁሉ ሽር ጉድ?
የሃይማኖታዊ ፖለቲካ አጀንዳ ኮሽ ባለ ቁጥር እንደ አንበሳ እያጋሳን የምንነሳ አገልጋዮች በዚህ ጉዳይ ለምን ዝም አልን?
ለምን ግንዛቤና ምክር አንሰጥም?
ወጣት እኮ ነው እየተነጠቅን ያለው?
ትውልድ እኮ ነው የምንገብረው?
መንፈሳውያን ማህበራትና ተቋማትም ብትሆኑ አሁኑኑ ግንዛቤ ፍጠሩ
ነገ አልሰማሁም ነበር የበላይ አካል ችግር ነው የእነ አገሌ እጅ አለበት የሚል እሮሮ ማንንም አይጠቅምም
እኔ ግን እላለሁ የመልካም ወጣት ስልጠናን ለመሳተፍ የገባ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስነቱን ለመጣል ልምምድ እያደረገ ስለሆነ በየትኛውም መስፈርት ኦርቶዶክስ ነህ አልለውም።
Zelalem Hasebe
43 views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 18:08:10 ዉስብስቡ የሃገራችን የ ፖለቲካ እጅ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ___
የሃገራችንን የኢትዮጵያን የፕለቲካ ሁኔታ መረዳት የሚችል አስተዋይ የሆነና አረቆ ማሰብ የሚችል ሰው ብቻ ነው።በዓለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ የተወሳሰበ የተወሳሰበ ፖለቲካ አለ ብሎ ደፍሮ ለመናገር ያዳግታል።ይህ የተወሳሰበ የፖለቲካ ርዕዮተዓለም በምዕራባዊያንና በዐረቦች የሞት ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ነው።ለዚህም ነው የሃገራችን መሪዎች ኢትዮጵያን እየመሯት ኢትዮጵያዊነትን እንደመርገም ጨርቅ የሚጸየፉት። በዚህ ዘመን ኦርቶዶክሳዊነትናኢትዮጵያዊነት በፖለቲካኞቻችን ዘንድ የተጠሉና የተወገዙ ናቸው። ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አስቀድሞ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ማሽመድመድና መጣል እንደሚያስፈልግ ሁሉም ይሰማሙበታል።ምናልባት 2 ወይ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች ካልሆኑ በስተቀር የተቀሩት ሁሉም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ማጥፋት ነው ዓላማቸው።ለዚህ እኮ ነው ኦርቶዶክሱ በየቦታው ሲታረድና ሲፈናቀል ትንፍሽ የማይሉት።የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ እስትራቴጂ ቢኖራቸውም እንኳ ኦርቶዶክስን በመጥላት ይሰማማሉ።ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ ግን ይህንን ሴራ ስላልተረዳ የገዳዮቹ ተባበሪ ሆኖ ቀጥሏል፣የመከራ ጽዋ እየተጎነጨ ይገኛል።ፖለቲካው ላይ ላዩ ሲታይ የብሔር ይመስላል ነገር ግን የመጨረሻ ግቡ የሃይማኖት መንግሥት ለመመስረት ነው።አሁን ሥልጣኑን የተቆናጠጠው ገዢው ፓርቲ ሕዝባዊ ሳይሆን ሃይማኖታዊ( የፕሮቴስታንቶችና የእሰላሞች) መንግሥት መሆኑን አራት ዓመት ሙሉ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ እያደረሰ ባለው መከራ መረዳት ይቻላል።በኦርቶዶክሳዊያን ላይ አዋጅ አውጆ ለማጥፋት ስለማይሆንለት ፣የሕዝቡም ቁጣ ስለሚያስፈራው የክርስትናው እንብርት የሆኑትን የ አማራውና የትግሬው ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ እርሰበርሱ እንዲጠፋፋ የማድረግን ስትራቴጂ ነው እየተጠቀመ ያለው።አማራውና ትግሬውን ካዳከመ በኋላ በሌሎች ስፍራዎች ላይ ያሉትን ኦርቶዶክሳዊያንን በግድም ቢሆን ሃይማኖታቸውን እንዲክዱ ለማድረግ ምንም አይከብደውም።የትግራይ ኦርቶዶክሳዊያን ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ተለይተው በረሀብ፣በችግር እንዲራቆቱ ተፈርዶባቸዋል ።የአማራውን ኦርቶዶክስ በገዛ ክልሉ በአራቱም አቅጣጫ ከበባ ዉስጥ እንዲገባና እንዲጨፈጨፍ እያደረገው ነው በሌሎች ክልሎችም እንደ እባብ እየተፈለገ እንዲቀጠቀጥና ዘሩ ከምድር እንዲጠፋ እየተደረገ ነው።መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ ለ መናገር በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው ጦርነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የማጥፋት ጦርነት ነው።በሰሜኑ ሁለቱን ክልሎች አውድሟል አሁንም ሠራዊቱን ልኮ ሰሜን ሸዋን እያወደመ ነው።በኦሮሚያ ሺዎችን እያረደ ነው።በደቡብ የፕሮቴስታንቲዝም እምነት ተከታዮች ሠራዊት ኦርቶዶክስ የሆነውን እያጸዱት ነው፣በምሥራቅ በግድ ማዕተባቸውን እንዲበጥሱና እንዲሰልሙ እያደረገ ነው።በምዕራብም ወከባው ግድያው፣መፈናቀሉ፣የሃብት ዉድመቱ አለ።ይህንን ሥውርና ጠመዝማዛ የሃገራችንን ፖለቲካ የተረዱ ኦርቶዶክሳዊያን ጥቂቶች ናቸው።አሁን እየሆነ ባለው ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ እንደ ቱርክ ኦርቶዶክሳዊያን ከመኖር ወደ አለመኖር መምጣታችን አይቀሬ ነው።ባለፈው ከቤተ መንግሥቱ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ ቤት በድብቅ ሾልኮ የወጣው"ጽንፈኝነት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን" የሚለው ሰነድ የዚሁ ማሳያ ነው፣ መንግሥት ኦርቶዶክስን ለማጥፋት መነሳቱን የሚያረጋግጥልን ነው።ከኦርቶዶክስ የጸዳች"አዲሲቷ ኢትዮጵያ" የምትባል ሃገር የመምሥረት ራዕይያቸውን ወደ ማሳካት እየተጓዙ ነው።ሞኙና ቅርብ አሳቢው ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ ግን ይህንን ዉስሰብ ፈተና በዉዳሴ ማርያም ብቻ የሚሸነፍ እየመሰለው ጮጋ ብሎ ተኝቷል።ነገሩ መች በዚህ ብቻ ሆነን።ጸሎት የሁሉም ነገር ቁልፍ እንደሆነ ቢታወቅም ዘመኑን መዋጀትና ፈተናዎችን እንደ አመጣጣቸው መመከት ግድ ይለናል። ያ ከ470 ጊዜ በላይ እግዚአብሔር ጋር የተናገረው ሙሴ እንኳ ኤሎፍላፊያንን ያሸነፈውና እሥራኤል ዘሥጋን ከባርነት ነጻ ያወጣቸው በጸሎት ብቻ ሳይሆን ተዋጊውን እግዚአብሔር ከፊቱ በማስቀደም ከእነሱ ጋር በመዋጋት ነው።እኛም ፖለቲካውን ርኩስ አድርገን መሸሽ ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚፈጥር መረዳት ያስፈልጋል፣ለፖለቲካ ያለን አማለካከታችንም ይሰተካከል።ለምን ከሩሲያ ቤተክርስቲያን አንማርም? የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኮሚኒስት መንግሥት ፈራርሳ ምዕመኖችዋም ለመጥፋት ተቃርበው አሁን እንደገና አቆጥቁጣ የሃገሪቱ 95%በላይ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ የሆነው ለፖለቲካ ያላቸው አመለካከት መልካም ስለነበርና ፖለቲካውንም ስለተቆጣጠሩትም ጭምር ነው። ሩሲያ ዛሬ የእነ አሜሪካን ፉከራና ድንፋታ የተቋቋመችው ጠንካራ ኦርቶዶክሳዊ መንግሥት ስላላት ነው።ልብ ያለው ልብ ይበል_። ችግሩ እኔና እናንተን እያደነቆሩን ያሉት አፈ_ጻዲቆች ኦርቶዶክሳዊያን ዲስኩረኞች ናቸው።እነርሱን አለመስማትና ኦርቶዶክሳዊ መብታችንን ለማስከበር በአንድነት መቆም ከሁላችንም የሚጠበቅ ነገር ነው።
#በአከባቢያችንመደራጀት!
#ቤተሰቦቻችንንማንቃት!
#መከላከል!
#መወያያት
#መደማማጥናተመሳሳይአጀንዳሊኖረንይገባል!
#7ቱየሞዐተዋህዶጥያቄዎችላይማተኮር!
#ሚድያንመቆጣጠር!
#ሐሰተኛመረጃዎችንመቃወምናማጋለጥ!
116 viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 10:25:06 ከተቻለን በክርስትና ሚዛን፣ ከወረደ በተፈጥሮአዊ ሰውነት ልኬት፣ ካልሆነ ኃላፊነት እንደሚሰማውና በሕግ የዜግነት ግዴታ እንዳለበት ሰው በመቆም ጥፋትን እንከላከል!

በአገራችን እየተካሄደ ካለው አንፃር “ከሆነው ይልቅ ሊሆን ያለው የበለጠ ያሳስባል!”
ሰሞኑን እየሆኑና እየተሰሙ ያሉ ነገሮች የብልጽግና መንግሥት ህልውናውን ለመመሥረት ያቀደው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መቃብር ላይ መሆኑን የበለጠ ግልጽ ያደረገ ሆኗል፡፡ ለቤተ ክርስቲያኗ ህልውና የሚታገሉትን ማሰሩንና ማሳደዱን በአንድ በኩል፣ ቤተ ክርስቲያኗን የበለጠ ለማዳከምና ለማጥፋት የጀመረውን ሥራ ደግሞ በሌላ በኩል አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚያ ላይ ለሥልጣናቸዉም ሆነ በክልል ደረጃ ጥቃቅን አገር ለመፍጠር ሲሰሩ የኖሩ ቡድኖች አዳዲስ የብሔር ሲኖዶስ ለመመሥረት እየተጣደፉ ነው። ለዚህም ከጥንት ጀምሮ እንደተለመደው ውስጥ አዋቂ ዴማሳውያንን እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ይህ መንግሥት ነኝ የሚለው አካል እያደረገ ያለው ነገር እንደ ሕዝብና አገር ያለንን ህልውና ወደ ከባድ አደጋ እየገፋ ያለ የአጥፍቶ መጥፋት ድርጊት መሆኑን ቢያስተውል ተያይዞ ከመጥፋትን ሁላችንንም ሊታደግ የሚችል ሥራ መሥራት ይችላል። ይህን ካልፈቀደ ግን ውድቀቱ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ብቻ ካልሆነ በስተቀር ለማናችንም የማይጠቅም መሆኑ ለአእምሮ መቃወስ ከደረሰባቸው ሕሙማን ካልሆነ በስተቀር ለማንኛውም ጤናማ ሰው ግልጥ ነው። በመሆኑም የመንግሥትን ሥልጣን ይዘው የአገርና የሕዝብ ደኅንነት ከማስጠበቅ በተቃራኒ ቆመው ፖለቲካን በቁማርና በብልጠት ስሌት ብቻ የሚተረጉሙ መሪዎች ቆም ብለው በማሰብ ከባሰ ጥፋት መመለስ እንደሚቻል ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በሌላ በኩል ክርስቲያኖችና ጤናማ ዜጎች (ሰውነትንና ሕሊናን ያልካዱ) አሁን እየታየ ያለው ዴማሳዊነት መምህሩን ቅዱስ ጳውሎስን ትቶ የከተማ ድሎትን የመረጠውን፣ ቀጥሎ መምህሩን እየተከታተለ ያሳደደውን በዚያን ዘመኑ ዴማስ ልክ ብቻ የሚታዩ አይደሉም። የአሁኖቹ ከክርስቲያናዊ አገልግሎት ወደኃላ ከመመለስ በተጨማሪ ለአፅራረ ቤተክርስቲያን ጋር ሥልጣንና መዋቅር እየተጋሩ ለዘለቄታዊ ጥፋት የሚሠሩ የውስጥና የውጭ ሠራተኞች ከፍተኛ ምእመናን የመከፋፈልና ግራ የማጋባት ሚና አላቸው። ሕዝቡ ይህን ተገንዝቦ ራሱን ከጭፍን ተከታይነት በመጠበቅ ዋና የሕልውና አጀንዳዎቹን ከሚያረሳሱ አሰላለፎች መጠበቅ ይኖርበታል። አዳዲሶቹ ዴማሶች ከሰውነትም፣ ከዜግነትም በወረደ ፍጹም ክሕደት ውስጥ የገቡና አንዳንድ የዋሐን እና ነፋስ ወደ ነፈሰበት የሚንገዋለሉ ወገኖችን በማሰልጠን፣ በመደለልና በማሰማራት የክርስቲያኖችን መሠረታዊ የአጀንዳ እንደሚያደናቅፉ ተገንዝበን በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በአንድነት እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
111 views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:57:27 እኔ ግን አንዳንድ ሰዎች ተገርሙኛላችሁ መንግሥት በሐሰት የሚነግሪችሁን ነገር እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትቀበሉታላችሁ ከቤተክርስቲያን የሚተላለፉትን ወደ ኋላ ትላላችሁ።በእውኑ በዚህ ዘመን መንግሥት በኦርቶዶክስ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያደረገ መሆኑን የማያውቅ ሰው አለን? እኔ እንጃ! ለማንኛውም ስለ ሰነዱ ለመረዳት ይህንን ሊንክ ተጭናችሁ አድምጡት።



114 views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:55:01 "...ድብቁ ሰነድ።መንግሥት ኦርቶዶክሳዊያንን ለማጥፋት በድብቅ ያዘጋጀው ሰነድ ከቤተ መንግሥት ሾልኮ የወጣ መረጃ!!! ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ይህንን ጉድ አሰሙ!!!"
ትርጉም:_
Mootummaan Ortodoksoota irratti duguggaa sanyii gaggeessuuf sanada icciitiin qopheesse.Maasara mootummaa irraa dhoksaan kan bahe.ortodoksonni Hundiinuu gocha suukaneessaa kana akka dhagahaniif hunduumaafuu raabsaa!!!
115 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 16:21:09 https://telegra.ph/%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8C%BB%E1%88%95%E1%8D%8D%E1%89%B0-%E1%88%98%E1%8A%90%E1%8A%AE%E1%88%B3%E1%89%B1-%E1%8A%A0%E1%88%A8%E1%8C%8B%E1%8B%8A-%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8D%88%E1%88%B3%E1%8B%8A-%E1%88%9B%E1%8A%95-%E1%8A%90%E1%8B%8D-05-25
144 views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 13:16:44 #ከአንተ_ጋር_እሆናለሁ "" (ኢያ. ፩:፭)

(ዝክረ ቅዱስ ኢያሱ ወልደ ነዌ)

ሰኔ 26
199 views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ