Get Mystery Box with random crypto!

የመልካም ወጣት አባል መሆን ያስወግዛልን? በመጀመሪያ የዚህ ተቋም መሥራችና ሥራ አስኪያጅ የሆነው | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ማያ/መነጽር

የመልካም ወጣት አባል መሆን ያስወግዛልን?

በመጀመሪያ የዚህ ተቋም መሥራችና ሥራ አስኪያጅ የሆነው ፓስተር ባስተላለፈው መልእክት ላይ የመልካም ወጣት ስልጠናን፡ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ኦርቶዶክሶች ረቡዕና ዓርብ ቀን እየጾማችሁ ወንጌል መማር ትችላላችሁ ብሏል
እና አስገድዶም ሊያበላቸው ያምረው ኖሯል እንዴ?
ግን የሚጾሙት የጴንጤነቱ ትምህርት እስኪሠርጽላቸውና የሚጾሙት ጼንጤ እስኪሆኑ ድረስ ነው አይደል?
ጾም ሙሉ የሚሆነው እየጾሙ ሲጸልዩ ሲመጸውቱ እንጂ እየጾሙ የፓስተር ትምህርት በመውሰድ ነው?
ደግሞ አስቡት እንጂ እዛ ሁሉ የፕሮቴስታንት መሃል የሚገኙ ጥቂት ኦርቶዶክሶች እንዴት አይነት የሞራል ድቆሳ ደርሶባቸው ጫናው ምን ያህል እንደሚሆን አስቡት እስኪ?
ደግሞስ የሌላ ቤተ እምነት ወንጌል እየተማሩ ኦርቶዶክስነት አለ እንዴ?
በጾም ከሚበላው ሥጋ በላይ በእየ እለቱ የሚሰሙት የሌላ ቤተ እምነት ትምህርትና ኑፋ* ከሥጋው አይበልጥምን?
ኧረ ለመሆኑ አንድ ኦርቶዶክስ የሌላ ቤተ እምነት የፕሮቴስታንት ስብከትን ዘወትር እየሰማ ጤነኛ ኦርቶዶክስ ነኝ ማለት ይችላልን?

በመሠረቱ እዚህ ፕሮግራም ላይ መሳተፍና የስልጠናው አባል መሆን ብቻውን ከሃይማኖት አያስወግዝም ወይ?
አንድ ሰው ከቤተ ክርስቲያን ተወግዞ ከሚለይባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በሌሎች ቤተ እምነቶች ቦታ ማለትም በፕሮቴስታንት አዳራሽ ውስጥ አብሮ ያመለከ፣ አብሮ የጸለየ፣ አብሮ ትምህርት የሚከታተል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ከመንጋዋ ትለየዋለች
ለመመለስ ቢፈልግ እንኳን ንዑሰ ክርስቲያን ብላ በቀኖናና በትምህርት ጊዜ ወስዶ ከተረዳ በኋላ ይመለሳል
ደግሞም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ"ከማያምኑት ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ ይላል 2ኛ ቆሮ 6:14 ከዚህ፡በላይ የማይመች ነገር የለም
ምንፍቅ*ን በልዩ ጥቅማ ጥቅም፡ጋር ቀላቅሎ ማታለልም ውጉዝ ነው"እስመ ኢኮነ ከመ ብዙኃን እለ ይትሜነይዎ ለቃለ እግዚአብሔር በካልእ ዳእሙ በንጽሕ ወከመ እም ኀበ እግዚአብሔር ንነግር በቅድመ እግዚአብሔር በእንተ ክርስቶስ
የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን 2ቆሮ 2:17 እንዲል በወጣት ስም ከሱስ በማውጣት ስም ኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ ዘረፋ ይቁም
ስለዚህ የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ማንም ኦርቶዶክሳዊ እዚህ ቦታ ገብቶ በነፍሱ እንዳይሞት ጥንቃቄ እናድርግ እንምከር
እኛ ቤት የሚለውጥና መልካም የሚያደርግ ትምህርትና ስብከት ጠፍቶ ነው?
ስልጠና የሚሰጥ አንደበተ ርቱዕ ስልጠና ሰጪ ስለሌለን ነው አንድ ፓስተር ፍለጋ ይሄ ሁሉ ሽር ጉድ?
የሃይማኖታዊ ፖለቲካ አጀንዳ ኮሽ ባለ ቁጥር እንደ አንበሳ እያጋሳን የምንነሳ አገልጋዮች በዚህ ጉዳይ ለምን ዝም አልን?
ለምን ግንዛቤና ምክር አንሰጥም?
ወጣት እኮ ነው እየተነጠቅን ያለው?
ትውልድ እኮ ነው የምንገብረው?
መንፈሳውያን ማህበራትና ተቋማትም ብትሆኑ አሁኑኑ ግንዛቤ ፍጠሩ
ነገ አልሰማሁም ነበር የበላይ አካል ችግር ነው የእነ አገሌ እጅ አለበት የሚል እሮሮ ማንንም አይጠቅምም
እኔ ግን እላለሁ የመልካም ወጣት ስልጠናን ለመሳተፍ የገባ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስነቱን ለመጣል ልምምድ እያደረገ ስለሆነ በየትኛውም መስፈርት ኦርቶዶክስ ነህ አልለውም።
Zelalem Hasebe