Get Mystery Box with random crypto!

ዉስብስቡ የሃገራችን የ ፖለቲካ እጅ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ___ የሃገራች | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ማያ/መነጽር

ዉስብስቡ የሃገራችን የ ፖለቲካ እጅ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ___
የሃገራችንን የኢትዮጵያን የፕለቲካ ሁኔታ መረዳት የሚችል አስተዋይ የሆነና አረቆ ማሰብ የሚችል ሰው ብቻ ነው።በዓለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ የተወሳሰበ የተወሳሰበ ፖለቲካ አለ ብሎ ደፍሮ ለመናገር ያዳግታል።ይህ የተወሳሰበ የፖለቲካ ርዕዮተዓለም በምዕራባዊያንና በዐረቦች የሞት ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ነው።ለዚህም ነው የሃገራችን መሪዎች ኢትዮጵያን እየመሯት ኢትዮጵያዊነትን እንደመርገም ጨርቅ የሚጸየፉት። በዚህ ዘመን ኦርቶዶክሳዊነትናኢትዮጵያዊነት በፖለቲካኞቻችን ዘንድ የተጠሉና የተወገዙ ናቸው። ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አስቀድሞ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ማሽመድመድና መጣል እንደሚያስፈልግ ሁሉም ይሰማሙበታል።ምናልባት 2 ወይ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች ካልሆኑ በስተቀር የተቀሩት ሁሉም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ማጥፋት ነው ዓላማቸው።ለዚህ እኮ ነው ኦርቶዶክሱ በየቦታው ሲታረድና ሲፈናቀል ትንፍሽ የማይሉት።የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ እስትራቴጂ ቢኖራቸውም እንኳ ኦርቶዶክስን በመጥላት ይሰማማሉ።ኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ ግን ይህንን ሴራ ስላልተረዳ የገዳዮቹ ተባበሪ ሆኖ ቀጥሏል፣የመከራ ጽዋ እየተጎነጨ ይገኛል።ፖለቲካው ላይ ላዩ ሲታይ የብሔር ይመስላል ነገር ግን የመጨረሻ ግቡ የሃይማኖት መንግሥት ለመመስረት ነው።አሁን ሥልጣኑን የተቆናጠጠው ገዢው ፓርቲ ሕዝባዊ ሳይሆን ሃይማኖታዊ( የፕሮቴስታንቶችና የእሰላሞች) መንግሥት መሆኑን አራት ዓመት ሙሉ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ እያደረሰ ባለው መከራ መረዳት ይቻላል።በኦርቶዶክሳዊያን ላይ አዋጅ አውጆ ለማጥፋት ስለማይሆንለት ፣የሕዝቡም ቁጣ ስለሚያስፈራው የክርስትናው እንብርት የሆኑትን የ አማራውና የትግሬው ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ እርሰበርሱ እንዲጠፋፋ የማድረግን ስትራቴጂ ነው እየተጠቀመ ያለው።አማራውና ትግሬውን ካዳከመ በኋላ በሌሎች ስፍራዎች ላይ ያሉትን ኦርቶዶክሳዊያንን በግድም ቢሆን ሃይማኖታቸውን እንዲክዱ ለማድረግ ምንም አይከብደውም።የትግራይ ኦርቶዶክሳዊያን ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ተለይተው በረሀብ፣በችግር እንዲራቆቱ ተፈርዶባቸዋል ።የአማራውን ኦርቶዶክስ በገዛ ክልሉ በአራቱም አቅጣጫ ከበባ ዉስጥ እንዲገባና እንዲጨፈጨፍ እያደረገው ነው በሌሎች ክልሎችም እንደ እባብ እየተፈለገ እንዲቀጠቀጥና ዘሩ ከምድር እንዲጠፋ እየተደረገ ነው።መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ ለ መናገር በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው ጦርነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የማጥፋት ጦርነት ነው።በሰሜኑ ሁለቱን ክልሎች አውድሟል አሁንም ሠራዊቱን ልኮ ሰሜን ሸዋን እያወደመ ነው።በኦሮሚያ ሺዎችን እያረደ ነው።በደቡብ የፕሮቴስታንቲዝም እምነት ተከታዮች ሠራዊት ኦርቶዶክስ የሆነውን እያጸዱት ነው፣በምሥራቅ በግድ ማዕተባቸውን እንዲበጥሱና እንዲሰልሙ እያደረገ ነው።በምዕራብም ወከባው ግድያው፣መፈናቀሉ፣የሃብት ዉድመቱ አለ።ይህንን ሥውርና ጠመዝማዛ የሃገራችንን ፖለቲካ የተረዱ ኦርቶዶክሳዊያን ጥቂቶች ናቸው።አሁን እየሆነ ባለው ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ እንደ ቱርክ ኦርቶዶክሳዊያን ከመኖር ወደ አለመኖር መምጣታችን አይቀሬ ነው።ባለፈው ከቤተ መንግሥቱ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ ቤት በድብቅ ሾልኮ የወጣው"ጽንፈኝነት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን" የሚለው ሰነድ የዚሁ ማሳያ ነው፣ መንግሥት ኦርቶዶክስን ለማጥፋት መነሳቱን የሚያረጋግጥልን ነው።ከኦርቶዶክስ የጸዳች"አዲሲቷ ኢትዮጵያ" የምትባል ሃገር የመምሥረት ራዕይያቸውን ወደ ማሳካት እየተጓዙ ነው።ሞኙና ቅርብ አሳቢው ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ ግን ይህንን ዉስሰብ ፈተና በዉዳሴ ማርያም ብቻ የሚሸነፍ እየመሰለው ጮጋ ብሎ ተኝቷል።ነገሩ መች በዚህ ብቻ ሆነን።ጸሎት የሁሉም ነገር ቁልፍ እንደሆነ ቢታወቅም ዘመኑን መዋጀትና ፈተናዎችን እንደ አመጣጣቸው መመከት ግድ ይለናል። ያ ከ470 ጊዜ በላይ እግዚአብሔር ጋር የተናገረው ሙሴ እንኳ ኤሎፍላፊያንን ያሸነፈውና እሥራኤል ዘሥጋን ከባርነት ነጻ ያወጣቸው በጸሎት ብቻ ሳይሆን ተዋጊውን እግዚአብሔር ከፊቱ በማስቀደም ከእነሱ ጋር በመዋጋት ነው።እኛም ፖለቲካውን ርኩስ አድርገን መሸሽ ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚፈጥር መረዳት ያስፈልጋል፣ለፖለቲካ ያለን አማለካከታችንም ይሰተካከል።ለምን ከሩሲያ ቤተክርስቲያን አንማርም? የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኮሚኒስት መንግሥት ፈራርሳ ምዕመኖችዋም ለመጥፋት ተቃርበው አሁን እንደገና አቆጥቁጣ የሃገሪቱ 95%በላይ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ የሆነው ለፖለቲካ ያላቸው አመለካከት መልካም ስለነበርና ፖለቲካውንም ስለተቆጣጠሩትም ጭምር ነው። ሩሲያ ዛሬ የእነ አሜሪካን ፉከራና ድንፋታ የተቋቋመችው ጠንካራ ኦርቶዶክሳዊ መንግሥት ስላላት ነው።ልብ ያለው ልብ ይበል_። ችግሩ እኔና እናንተን እያደነቆሩን ያሉት አፈ_ጻዲቆች ኦርቶዶክሳዊያን ዲስኩረኞች ናቸው።እነርሱን አለመስማትና ኦርቶዶክሳዊ መብታችንን ለማስከበር በአንድነት መቆም ከሁላችንም የሚጠበቅ ነገር ነው።
#በአከባቢያችንመደራጀት!
#ቤተሰቦቻችንንማንቃት!
#መከላከል!
#መወያያት
#መደማማጥናተመሳሳይአጀንዳሊኖረንይገባል!
#7ቱየሞዐተዋህዶጥያቄዎችላይማተኮር!
#ሚድያንመቆጣጠር!
#ሐሰተኛመረጃዎችንመቃወምናማጋለጥ!