Get Mystery Box with random crypto!

ከተቻለን በክርስትና ሚዛን፣ ከወረደ በተፈጥሮአዊ ሰውነት ልኬት፣ ካልሆነ ኃላፊነት እንደሚሰማውና በ | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ማያ/መነጽር

ከተቻለን በክርስትና ሚዛን፣ ከወረደ በተፈጥሮአዊ ሰውነት ልኬት፣ ካልሆነ ኃላፊነት እንደሚሰማውና በሕግ የዜግነት ግዴታ እንዳለበት ሰው በመቆም ጥፋትን እንከላከል!

በአገራችን እየተካሄደ ካለው አንፃር “ከሆነው ይልቅ ሊሆን ያለው የበለጠ ያሳስባል!”
ሰሞኑን እየሆኑና እየተሰሙ ያሉ ነገሮች የብልጽግና መንግሥት ህልውናውን ለመመሥረት ያቀደው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መቃብር ላይ መሆኑን የበለጠ ግልጽ ያደረገ ሆኗል፡፡ ለቤተ ክርስቲያኗ ህልውና የሚታገሉትን ማሰሩንና ማሳደዱን በአንድ በኩል፣ ቤተ ክርስቲያኗን የበለጠ ለማዳከምና ለማጥፋት የጀመረውን ሥራ ደግሞ በሌላ በኩል አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚያ ላይ ለሥልጣናቸዉም ሆነ በክልል ደረጃ ጥቃቅን አገር ለመፍጠር ሲሰሩ የኖሩ ቡድኖች አዳዲስ የብሔር ሲኖዶስ ለመመሥረት እየተጣደፉ ነው። ለዚህም ከጥንት ጀምሮ እንደተለመደው ውስጥ አዋቂ ዴማሳውያንን እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ይህ መንግሥት ነኝ የሚለው አካል እያደረገ ያለው ነገር እንደ ሕዝብና አገር ያለንን ህልውና ወደ ከባድ አደጋ እየገፋ ያለ የአጥፍቶ መጥፋት ድርጊት መሆኑን ቢያስተውል ተያይዞ ከመጥፋትን ሁላችንንም ሊታደግ የሚችል ሥራ መሥራት ይችላል። ይህን ካልፈቀደ ግን ውድቀቱ ለኢትዮጵያ ጠላቶች ብቻ ካልሆነ በስተቀር ለማናችንም የማይጠቅም መሆኑ ለአእምሮ መቃወስ ከደረሰባቸው ሕሙማን ካልሆነ በስተቀር ለማንኛውም ጤናማ ሰው ግልጥ ነው። በመሆኑም የመንግሥትን ሥልጣን ይዘው የአገርና የሕዝብ ደኅንነት ከማስጠበቅ በተቃራኒ ቆመው ፖለቲካን በቁማርና በብልጠት ስሌት ብቻ የሚተረጉሙ መሪዎች ቆም ብለው በማሰብ ከባሰ ጥፋት መመለስ እንደሚቻል ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

በሌላ በኩል ክርስቲያኖችና ጤናማ ዜጎች (ሰውነትንና ሕሊናን ያልካዱ) አሁን እየታየ ያለው ዴማሳዊነት መምህሩን ቅዱስ ጳውሎስን ትቶ የከተማ ድሎትን የመረጠውን፣ ቀጥሎ መምህሩን እየተከታተለ ያሳደደውን በዚያን ዘመኑ ዴማስ ልክ ብቻ የሚታዩ አይደሉም። የአሁኖቹ ከክርስቲያናዊ አገልግሎት ወደኃላ ከመመለስ በተጨማሪ ለአፅራረ ቤተክርስቲያን ጋር ሥልጣንና መዋቅር እየተጋሩ ለዘለቄታዊ ጥፋት የሚሠሩ የውስጥና የውጭ ሠራተኞች ከፍተኛ ምእመናን የመከፋፈልና ግራ የማጋባት ሚና አላቸው። ሕዝቡ ይህን ተገንዝቦ ራሱን ከጭፍን ተከታይነት በመጠበቅ ዋና የሕልውና አጀንዳዎቹን ከሚያረሳሱ አሰላለፎች መጠበቅ ይኖርበታል። አዳዲሶቹ ዴማሶች ከሰውነትም፣ ከዜግነትም በወረደ ፍጹም ክሕደት ውስጥ የገቡና አንዳንድ የዋሐን እና ነፋስ ወደ ነፈሰበት የሚንገዋለሉ ወገኖችን በማሰልጠን፣ በመደለልና በማሰማራት የክርስቲያኖችን መሠረታዊ የአጀንዳ እንደሚያደናቅፉ ተገንዝበን በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ በአንድነት እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።