Get Mystery Box with random crypto!

ikhlas Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube I
የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube
የሰርጥ አድራሻ: @ikhlasstudents
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.73K
የሰርጥ መግለጫ

በዱንያም በአሄራም አላህ ስኬታማ ከሚሆኑ ሰዎች ያድርገን
@ikhlasstudents
አስታየት ካላችሁ @muaz_mb ሊያገኙን ይችላሉ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 75

2022-08-31 19:14:31
#ሚስተር_ሀራም የመጨረሻው ክፍል
18

#የሚለቀቀው__ግሩፓችን_ላይ (Add Member) ሁላችሁም የተቻላችሁን ያህል Add Member ይለቀቃል

ጀማው እንተባበር ዛሬ #6000 እንለፍ

#Add_Member_ለማድረግ

@ikhlasTubeGroup
@ikhlasTubeGroup
@ikhlasTubeGroup

      
2.5K viewsMᴜᴀᴢ, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 16:23:02 መልሱን ዛሬ ማታ እነግራቹሀለሁ

እስካሁን አንድ እህታችን ነው የመለሰችው
2.9K viewsMᴜᴀᴢ, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 22:11:44
አሳተፊ ጥያቄ
1.7K viewsMᴜᴀᴢ, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:02:41
የመጨረሻዉ መጨረሻ ክፍል

@ikhlasstudents
2.3K viewsMᴜᴀᴢ, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:27:35 "ሚስተር ሀራም"
(ኑዕማን ኢድሪስ)

የመጨረሻዉ ክፍል
ክፍል_⓱_ይቀጥላል.......
  ⊶⊷⊶⊷❍⊶⊷⊶⊷

... ሁለት ሳምንት ሙሉ ሄለንን አላገኛትም። ስትደዉልለት ስልክ አላነሳላትም። የላከችለትን መልእክትም አትመልስለትም። ያስቀየማትን ለመካስ የእራት ግብዣዉን ተቀብሏታል። ዱባይ ያለችዉ ከሪማ ገንዘቡን የምትልክለት ትንሽ ጊዜ ስለሚቆይ ከሄለን ጋር ከስከዛሬዉ ይበልጥ አሁን ተቀራርቦ የሚፈልገዉን ነገር ማግኘት አለበት። ሰሚር ብዙ አይነት አማራጮችን ይዞ ነዉ የሚጓዘዉ።

... ከምሽቱ አንድ ሰአት ሆኗል። ከሄለን ጋር የእራት ቀጠሮ ስለያዘ እየተቻኮለ ነዉ ከቤት የወጣዉ። ጓደኛዋን ልታስተዋዉቀዉ እንደሆነ ስላልነገረችዉ ከሷ ጋር የማደሩን ፕሮግራም አስቦበታል። ከተቀጣጠሩበት ሆቴል ሲገባ ሄለን ብቻዋን ተቀምጣለች። ያለወትሮዋ ለስላሳ መጠጥ ስትጎነጭ ተመለከታት። ፈገግ እያለ ወደሷ ተራመደ። "ሄይ ሄሉ .." ብሎ በተቀመጠችበት በስሱ ጉንጯን ስሟት ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ።
"ዛሬ የማስተዋዉቅህ ሰዉ አለ" አለችዉና ፈገግ አለች። ልቡን ፍርሀት ወረረዉ። ግራና ቀኙን መልከት ካለ በኃላ "ማንን ነዉ የምታስተዋዉቂኝ ሄሉ?" ብሎ ጠየቃት። ኢማን እንዳትሆን በልቡ መጸለይ ጀመረ።
"ያዉ መጣ" አለችና በጣቷ ወደ'ሱ ኃላ ጠቆመች። አቡበከር እነሱ ወደተቀመጡበት ወንበር እየመጣ ነበር። ሰሚር ወደኃላዉ ዘወር ብሎ ተመለከተ። ነሽዳዉን ስፖንሰር ያደረገለት አቡኪ ነዉ። ሚገባበት ጠፋዉ። ተነስቶ እንዳይሰወር አቡበከር ጋር ተያይተዋል።
"ሰላም እንዴት ናችሁ" አላቸዉ። ሰሚር ሚናገረዉ ነገር ጠፋዉ። ምን ብሎ እንደሚመልስ ተደናገረዉ።
"ሰላም አቡኪ ተዋወቁ ጓደኛዬ ሰሚር ነዉ!" አለች ሄለን። ፊቱ በሀፍረት ተሸማቀቀ። አቡበከር ጋር ይተዋወቃሉ። ስፖንሰር እንዲሆነዉ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ከቢሮዉ ደጅ ጠንቷል። ዛሬ ግን እኩይ ባህሪዉን አወቀበት። አቡበከር ብቻ ሳይሆን ኢማንም መስማቷ አይቀርም። ተሸማቀቀ።

...

ነሽዳዉን ደጋግማ ታዳምጣለች። እያንዳንዷን የግጥም ስንኞች በመሸምደድ ላይ ነች። በፌስቡክ የሚናፈሰዉ ወሬ ሁሉ ስለ አዲሱ ነሽዳ ነዉ። በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አግኝቷል። የሰሚር ፍቅረኛ በመሆኗ እድለኝነት ተሰማት። ፌስቡክ ገባችና "በጽኑ ቃል የተገነባ እዉነተኛ ፍቅር...!" ከሚል ጥቅስ ጋር ከሰሚር ጋር አንድ ላይ የተነሱትን ፎቶ በገጿ ለቀቀችዉ።

...

አቡበከርና ሄለን ፊት ቃል ማዉጣት ተሳነዉ። ዱዳ ሆነ። ለሚጠየቀዉ ጥያቄ መልስ ሲሰጥ እየንተተባተበ ነዉ። ተዋዉቀዉ ትንሽ ከተጨዋወቱ በኃላ አቡበከር ወደ ሄለን ዞሮ ፈቃድ ጠየቀ።
"ሄሉ ጓደኛሽን ብቻዉን ላናግረዉ ፈልጌ ነበር..." ሲላት ሁለቱንም ተራ በተራ ተመለከተቻቸዉ። ሰሚር ምንም ማለት አልቻለም። አቡኪ ቀጠል አደረገና "... ቅር አይልሽማ ሄሉ" ብሎ በአይኖቹ ተማጸናት። የሚያወሩት በሀይማኖታዊ ጉዳይ ዙሪያ ስለሆነ እንድትሰማቸዉ አልፈለገም።
"አሺ እናንተን ደስ እንዳላችሁ" ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ ተሰናብታቸዉ ሄደች።
"እሺ ሰሚር..." አለና ወደ ዋናዉ ጉዳይ ሊገባ ተንደረደረ። "ሁለታችም ወጣቶች ነን እንግባባለን ብዬ አስባለሁ።..." ብሎት በአትኩሮት ተመለከተዉ። ሰሚር አንገቱን ወደ ላይና ወደ ታች ከመነቅነቅ ዉጭ ምንም አልመለሰም።
"ይገባኛል ሰሚር አንተ ዲንህን ለመኻደም ደፋ ቀና የምትል ወጣት ነህ። ብዙ መልካም ነገሮችም ይኖሩሃል። ነገር ግን ወጣትነትህ ተፈታትኖህ ወይም ትንሽዬ ገንዘብ ፈልገህ ማይጠቅሙህ ሰዎች ዙሪያ ነዉ ያለኸዉ። ያዉም ዱንያ አኼራህን ሊያበላሹ ከሚችሉ ሰዎች ዙሪያ...." ሰሚር የአቡበከርን ምክር ከልቡ እያዳመጠዉ ነበር። በዙሪያዉ ያሉ መልካም የሚባሉ ሰዎች ሰሚርን ከመስደብና ከማዋረድ ዉጭ ልብን ሰርስሮ በሚገባ ምክር የገሰጸዉ የለም። አብዛኞቹ "ሚስተር ሀራም ... ሚስተር ሀራም " እያሉ የሚሰራዉን መጥፎ ስራ እያወቁ ባላየ ያልፉታል። አቡበከር ግን ያን አልፈቀደም።

... ከአቡበከር ጋር ከተለያየ በኃላ የነገረዉን ምክሮች ሁሉ ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነ። ነገር ግን ያንቺን የመሰለች ልእልት ልጅ ዝም ብሎ ሊተዋት አልፈቀደም። "አቡበከር የሄለን ፍቅረኛ እንደሆንኩ አዉቋል። በቅርቡ ደግሞ ኢማን መስማቷ አይቀርም። ስለዚህ በቅርቡ ከሷ ጋር ያለኝን ነገር መጨረስ አለብኝ። ቢያንስ አንድ ሌሊት አብሪያት ላሳልፍ ይገባል።...." ብሎ ወሰነ።
"ሄሎ ኢሙ" ደወለላት።
"ወይዬ ሀቢቢ...
...

ሰሚርና እሷ አንድ ላይ የተነሱትን ፎቶ ከለቀቀች በኃላ በዉስጥ ሚሴጅ ብዙ መልእክቶች ይገቡላት ጀመር። ሰሚር ከደወለላት በኃላ ፌስቡክ ላይ ስለለቀቀችዉ ፎቶ አልነገረችዉም።

"ሚስተር ሀራምን ታዉቂዋለሽ እንዴ?" ፤ "ከባሌ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምንድን ነዉ?" ፤ "አሰላሙአለይኩም የኔ ቆንጆ .. ፈሚስተር ሀራም ሌባ ነዉ! አደራሽን ተጠንቀቂ"... የድምጽና የጽሁፍ መልእክቶች ነጎዱ። ኢማን ብዙም አልተገረመችም። እስካሁን በነበራቸዉ ግኑኝነት ይሄ ነገር እንደሚከሰት ቀድሞ ስላወቀ አዘጋጅቷት ነበር። ሁሉንም መልእክቶች እያየች ባላየ አለፈቻቸዉ።

...

ሁሉንም ቀድሞ በያዘዉ ክፍል አልጋ ላይ ጋደም ብሎ በተደጋጋሚ ሰአቱን ይመለከታል። ኢማን ጋር ከከንፈር በዘለለ ከብረ ንጽህናዋን ሊያሳጣት ነዉ። ቀድመዉ ስላወሩበት ፈቃደኛ ሆናለች። ከሄለን ጋር የምታወራዉና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምታያቸዉ ነገሮች የኢማንን ፍጹም ማንነት ቀይረዋታል። ከተቀጣጠሩበት ሰአት ትንሽ ስትቆይበት ስልኩን ከኪሱ አወጣና መደወል ጀመረ።
"ሄሎ ኢሙ የት ደረስሽ?" ብሎ ጠየቃት። እስከምትደረስ ተቻኩሏል። ያንን ዉብ ገላ እንዳሻዉ እስኪንቦራቦርበት ቋምጧል። ዉብ ከንፈሯን እየሳመ ማራኪ የሆነዉን ገላ እስከሚደባብሰዉ አጣድፎታል።
"እየመጣሁ ነዉ ሰሙሪ.."
"እየጠበቅኩሽ ነዉ የኔ ቆንጆ ... ፍጠኚ"


  ክፍል_⓲_ይቀጥላል.......
  ⊶⊷⊶⊷❍⊶⊷⊶⊷ የመጨረሻዉ መጨረሻ ክፍል ይቀጥላል....

@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
2.5K viewsMᴜᴀᴢ, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:19:21
ክፍል 17

የመጨረሻው ክፍል እንደሆነ ያውቃሉ
2.3K viewsMᴜᴀᴢ, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:22:42
ውበቷ ሲረግፍ አረጀሽ ብሎ አልተዋትም
ጤንነቱን ሲያጣም በሽተኛ ብላ አለተወችውም።

هكذا كان الحب في زمن أجدادنا
ፍቅር በአያቶቻችን ጊዜ እንዲህ ነበር

ፍቅር ሰባኪ

@ikhlasstudents
3.3K viewsMᴜᴀᴢ, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:56:46 #ሚስተር_ሀራም

#የሚለቀቀው__ግሩፓችን_ላይ (Add Member) ሁላችሁም የተቻላችሁን ያህል Add Member ይለቀቃል

#Add_Member_ለማድረግ

@ikhlasTubeGroup
@ikhlasTubeGroup
@ikhlasTubeGroup

      
3.1K viewsMᴜᴀᴢ, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:35:18 ° እኛ ሙስሊሞች ምድር ስትጠበን ፣ ሰማይ የሚሰፋን ህዝቦች ነን፤


° አላህ ለ ሰው ልጅ « ከ ደም ስሩ የቀረብን ነን » እያለ እንዴት ተስፋ እንቆርጣለን ???


° ሁላችንም እጆቻችንን ወደ አላህ እንዘርጋ ፣ መፈትሄንም ከባለቤቱ እንፈልግ

@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
3.0K viewsMᴜᴀᴢ, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:27:30
ሰዎች ልብህን ሊሰብሩት ሊያስከፉህ ሊያስቀይሙህ ይችላሉ፤ ታግሰህ ካለፍካቸው ፍቅር ገብቶሀል ማለት ነው። ፍቅር የገባውሰው ይቅር ይላል እንጂ እድሉን ሲያገኝ አይበቀልም፤ ከተበቀለ ደግሞ መቼም ሰላም አይሰማውም።

ወዳጄ በፍቅር ካላመንክ ትለፋለህ የትም አትደርስም! ታገኛለህ አትረካም! ትዘራለህ አታጭድም! ብታጭድም አንተ አትበላውም! ፍቅር ሁሌም ያሸንፋል!


@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
3.5K viewsMᴜᴀᴢ, 19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ