Get Mystery Box with random crypto!

ikhlas Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube I
የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube
የሰርጥ አድራሻ: @ikhlasstudents
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.73K
የሰርጥ መግለጫ

በዱንያም በአሄራም አላህ ስኬታማ ከሚሆኑ ሰዎች ያድርገን
@ikhlasstudents
አስታየት ካላችሁ @muaz_mb ሊያገኙን ይችላሉ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 74

2022-09-01 22:45:11
''ዱንያ ''

ማራኪ የሆነ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ አሳዛኝ አስተማሪ የሆነ ታሪክ ትማሩበት ዘንድ እነሆ.....
በኢማን tube ተዘጋጅቶ የቀረበ።

አሁኑኑ OPEN የሚለውን በመጫን ያንብቡ።

Https://t.me/sineislam
Https://t.me/sineislam

የውሸት ማስታወቂያ አይደለም
605 viewsMᴜᴀᴢ, 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:43:08 ማሻአሏህ ጀግኖች የግሩፑን አባላት ከ 5500 ለማሳለፍ አቅደን ተሳክቷል አልሀምዱሊላህ በድጋሚ ጉዟችንን ወደ 6000የዛሬ ምሽት እቅዳችን ይሄ ነው አዲስ ገቢዎች የግሩፑን አላማ ወደ ዋናው ቻናላችን በመግባት ማንበብ ትችላላችሁ @ikhlasstudents

#አድ
#አድድ
#ድድድ
#አድድድ
#አድድድድ
#አድድድድድ
#አድድድድድድ
#አድድድድድድድ
#አድድድድድድድድ

      ያጀመዓ አድ እያደረጋችሁ ወደ መልካም ተጣሩ ባረከሏሁ ፊኩም


وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?



@ikhlasTubeGroup
@ikhlasTubeGroup
865 viewsMᴜᴀᴢ, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:20:21
☆ ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት።☆

አል-ኢምራን [ 3:185]

@ikhlasstudents
1.3K viewsMᴜᴀᴢ, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:36:04
ሚስቱን ስለ ሁለተኛ ሚስት
ማግባት ለማስረዳት ሲሞክር
ምግቡን በዚህ መልክ አቀረበችለት ።

Te » @ikhlasstudents ㋡
1.9K viewsMᴜᴀᴢ, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:55:14
ስልኮች በገመድ ታስረው
በነበረበት ጊዜ ሰዎች ነፃ ነበሩ
ይባላል ።

Te » @ikhlasstudents ㋡
2.5K viewsMᴜᴀᴢ, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 05:19:42 #የፈጅር አየር ለምንድነው
ከሌሎች ጊዜ የበለጠ ንፁህ
የምትሆነው? ተብለው ሲጠየቁ‥
መናፍቃን ስለማይገኙባት ነው ።
ብለው መለሱ

Te » @ikhlasstudents ㋡
259 viewsMᴜᴀᴢ, 02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:49:48 ብረዉ ተሳሳቁ።

ሚስተር ሀራም ወደ ሚስተር ሀላልነት....

ኑዕማን ኢድሪስ

══════ •『 ♡ 』• ══════
                   #ተፈፀመ
══════ •『 ♡ 』• ══════

አስታየታችሁን C̆̈ŏ̈m̆̈m̆̈ĕ̈n̆̈t̆̈ ላይ መግለፅ ይቻላል

@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
2.0K viewsMᴜᴀᴢ, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:49:29 "ሚስተር ሀራም"
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ክፍል አስራ ስምንት (18)
የመጨረሻዉ መጨረሻ

... ሄለን ትምህርትና ስራ ስለሚደራረብባት ፌስ ቡክ የመግባት ልብድ የላትም። ዛሬ ግን የፌስቡኩን አለም ገረፍ ገረፍ እያደረገች እየጎበኘችዉ ነዉ። ድንገት ግን ከአንድ ፎቶ ላይ አይኖቿ ተተከሉ። ምታየዉን ማመን አቃታት። ኢማንና ሰሚር አንድ ላይ ፎቶ ተነስተዉ። የተነሱበትን ቦታ ታዉቀዋለች። ኢማን የለበሰችዉን ልብስ አስታወሰች። 'ይሄን ልብስ የለበሰችዉ ፒያሳ ሄጄ ያገኘኃት ቀን ነዉ። አዎ ትምህርት ያስመዘገብኳት ቀን፤ የሰሚርንም መኪና ዉጭ ላይ አይቼዋለሁ' አለች። ወደ ኃላ ተጉዛ ለማስታወስ እየሞከረች። ሁሉም ነገር እንደገና ተገለጠላት። 'ስደዉልለት ዉስጥ ሆኖ ነዉ የዋሸኝ ማለት ነዉ።' ይበልጥ ተበሳጨች። 'ይሄ የተረገመ እሷንም ሊጫወትባት ነዉ!' በማለት ከፌስቡክ ወጣችና ወደ ኢማን ስልክ መደወል ጀመረች።

ኢማን ከቤት ከወጣች በኃላ የታክሲ ወረፋ የመጠበቂያ ጊዜ አልነበራትም። በጣም ቸኩላለች። ከተደረደሩት ላዳዎች ዉስጥ ለአንዱ ሾፌር የምትሄድበትን ነግራዉ መንገድ ጀምረዋል። ሀሳቧ ሁላ ወደ ፊት ተራምዳ ሰሚርን እንዴት እንደምታቅፈዉ፤ በምን አይነት ሁኔታ እንደምትስመዉ... ሄለን የምትነግራትን፤ ስትቋምጥለት የነበረዉን.. 'ምመኛቸዉን ነገሮች ሁሉ ዛሬ እዉን አደርጋለሁ።' በማለት አሰበች። ከአዲስ አበባ ወጥታ ክፍለ ሀገር እንደሚጓዝ ሰዉ መንገዱ ራቀባት። መንገድ ተዘጋግቶ የትራፊክ ጭንቅንቅ ነበር። መታገስ አልቻለችም። ማረሳሻ እንዲሆነኝ ብላ በማሰብ ስልኳን ከፖርሳዋ አወጣችና የኢንተርኔት ዳታ ከፈተች። የተጠራቀሙ የድምጽና የጽሁፍ መልእክቶች ወደ ስልኳ ይገቡ ጀመር። መልእክት ከላኩላት ሰዎች አብዛኞቹን የምታዉቃቸዉ ሲሆን የተወሰኑትን አታዉቃቸዉም። በመጀመሪያ የከፈተችዉ አንሷር የሸዋዉ ከሚል አካዉንት የተላከላትን መልእክት ነበር። ሰላምታ አላስቀደመም ቀጥታ ወደ መልእክቱ ነዉ የገባዉ። "ሚጠቅምሽን ልንገርሽ እህቴ! ሚስተር ሀራም የብዙ ሴቶች እንባ አለበት። ሚጠቅምሽ አይነት ሰዉ አይደለም። ላንቺዉ ብዬ ነዉ። ራቂዉ ..." ይላል። ማታ ስትሰማቸዉ ከነበሩት መልእክቶች ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም 'ሚስተር ሀራም' የሚለዉ ስያሜ መደጋገሙ ግን ትንሽ አሳሰባት። 'ሚስተር ሀራም ለምን አሉት?'። ሁለተኛዉ ከሀያት ሁሴን የተላኩላት የድምጽና የህጻን ልጅ ፎቶ የያዘ መልእክት ነበር። የድምጽ ማዳመጫ ኤርፎኗን ጆሮዋ ላይ አድርጋ መልእክቱን ከፈተችዉ። "... አሰላሙ አለይኩም እህቴ እንዴት ነሽ?..." ብላ ጀመረች.. መልእክቱን የላከችዉ ሀያት። እንባ እየተናነቃት እንደምታወራ ከድምጿ በሚወጣዉ ሲቃ ያስታዉቅባታል። ሁኔታዋን የተረዳችዉ ኢማን መልእክቱን ለማዳመጥ ይበልጥ ጓጓች። "... እንዴት ነሽ እህቴ? ሰሚር ጋር ጓደኝነት እንደጀመራችሁ ፌስቡክ ላይ የለቀቅሽዉን ፎቶ ተመለከትኩ። እህቴ! እኔ ሰሚርን በጣም ነዉ የማፈቅረዉ ከሁለት አመት በላይ በፍቅረኝነት አብረን ቆይተናል። ነገር ግን ሀገር ቤት መጥቼ ክብሬን አሳልፌ ከሰጠሁት በኃላ ራቀኝ። በግንኙነታችን ወቅት በጣም አፈቅረዉ ስለነበር ምንም አልተጠነቀቅኩም ነበር። ይህ የምታይዉ ከሱ የወለድኩት ነዉ። ስም አላወጣሁላትም። አባቱ ሰሚር እስኪያወጣለት እየጠበቅኩ ነዉ።....." ሙሉ ሰዉነቷ በቅጽበት ተቀያየረ። አይኖቿ ደም ለበሱ፤ ፊቷ በቁጣ ተነፋፋ። ወደታች ወረድ አለችና ልጁን በትኩረት ተመለከተችዉ። የአፍንጫዉ ሰልካካነት፤ ግንባሩ፤ አይኖቹ ሁሉ ነገሩ ሰሚርን ነዉ የሚስለዉ። ሰዉነቷ ይበልጥ ተርበተበተ። ሳታስበዉ ካአንደበቷ 'ሚስተር ሀራም' ብላ ድምጽ አወጣች። ሾፌሩ ወደ ኃላ ሳይዞር "ጠራሽኝ" አላት። አይኖቿ እንባ እያዘሉ ነበር። "አዎ እዚህ አዉርደኝ!" አለችና ሂሳብ ከፖርሳዋ ማዉጣት ጀመረች።
ከመኪናዉ ስትወርድ ሰማይና ምድሩ ተደበላለቁባት። ወዴት እንደምትሄድ ተደናገራት። "አምቢያዉ ሙርሰሉ ሁሉ ኡመቶ ባረገን ሲሉ በእዝነቱ እኔን መርጦኝ ሲያድለኝ ያንቱ አረገኝ..." ። ከአንዱ ህንጻ ጥላ ስር ከተጠለለች በኃላ ነበር ስልኳ እየጠራ እንደሆነ የሰማችዉ። ስልኳን አንስታ ወደ ጆሮዋ ስታስጠጋዉ እንደገደል ማሚት የሚያስተጋባ ድምጽ ተሰማት። "ኢማን የት ነሽ?" አለቻት ሄለን። እንባ ቀደማት፤ ሲቃ አነቃት የት እንዳለች፤ ምኑ ጋር እንደወረደች አታዉቀዉም። በጆሮዋ የሰማችዉ መልእክት፤ በአይኗ ያየችዉ የህጻን ልጅ ፎቶ ሙሉ አካቷን አራደዉ።
"ኢሙ ሰሚር ጋር እንዳትሄጂ ይጎዳሻል" አለች ሄለን።
"ሄሉ... " ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች። መናገር አቃታት። የምታፈቅረዉና የምትወደዉ ልጅ ከሌላ ሴት ልጅ አለዉ። የሚነግሯትን ነገር ሁሉ ችላ ብላ አልፋ ነበር። እዚህ ላይ ግን አልቻለችም። አቃታት። እንደምንም እየተነፋረቀችም ቢሆን ያለችበትን ቦታ ነገረቻት።
"ተረጋጊ ኢሙ መጣሁልሽ!" ብላት ስልኩ ተዘጋ።

........
ከአንድ አመት በኃላ

........
... ኢማን፤ አቡበከርና ሰሚር ሆነዉ ቦሌ አየር ማረፋያ ከዱባይ የሚመጣዉን አየር በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ። ሚስተር ሀራም በአቡበከርና በኢማን እገዛ ከነበረበት ማንነት ተላቆ በአቡበከር ድርጅት ዉስጥ የስራ መደብ ተሰጥቶት መስራት ጀምሯል። ለኢማንና ለአቡበከር የቅርብ ጓደኛቸዉም ሆኗል። ባደረሰባት ነገር ብትከፋም ሰሚርን ከመራቅ ይልቅ ይበልጥ ቀርባ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ የመመለሱ ምክንያት ሁነዋለች። አቡበከርም ሲረዳት ቆይቷል።

ከዱባይ የተነሳዉ አየር ቦሌ ኤርፖርት ሲያርፍ የሚመጡትን እንግዶች ለመቀበል የልብ ምቱ ጨመረ። ምንም እንኳ ይቅርታ ቢጠይቃትም በርሷ ላይ ያደረሰዉ በደል ትንሽ የሚባል አይደለም። ስለምታፈቅረዉ ገንዘቧንና ማንነቷን አሳልፋ የሰጠችዉን የልጁን እናት ሀያትንና አንድ አመት ያለፈዉን ልጁን ለመቀበል ቦሌ ኤርፖርት ተከስተዋል። መኪናቸዉ ዉስጥ ሆነዉ እየተጨዋወቱ ሄለን ለሰሚር ደወለችለት። ሊያነጋግረዉ የሚችለዉን ቁልፍ ተጫነና "ሄሎ ሂሉ" አላት። አሁንም ሄለን እየጮኸች ነዉ።

"ደሞ ሚስቴና ልጄ መጡ ብለህ እንዳዘጋኝ!" አለችዉ። አቡበከር ድርጅት ከገባ በኃላ በተለያዩ ጉዳዮች ከሄለን ጋር ስለሚያገናኘዉ ንጹህ ጓደኛሞች ሆነዋል። ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ተቀራርበዋል። በተደጋጋሚ 'ለሰርግህ እኔ ነኝ ሚዜህ የምሆነዉ' እያለች ትቀልድበታለች። በትንሹ ሳቅ አለና ቀና ሲል ሚያየዉን አቃተዉ። ሀያት ኒቃብ ለብሳ ህጻን ልጇን እንዳቀፈች በበሩ ስትወጣ ተመለከታት። ስልኩን ለአቡበከር ሰጠዉና እሷን ለመቀበል ከመኪናዉ ወርዶ ወደ በሩ አመራ። ኢማንም ፈጠን ብላ በመዉረድ ከኃላዉ ተከተለችዉ። ኢማን ለሀያት ጓደኛ ሆናታለች። "ልጁ ያለ አባት ማደግ የለበትም፤ እሷም ስለምታፈቅርህ ደስተኛ ታደርግሀለች።" ብላ ያሳመነችዉ ኢማን ናት። "... ሰሙሪ ገንዘባቸዉን የወሰድክባቸዉን ሴቶች እየሰራህ ትመልሳለህ። ደግሞ አቡኪም ያግዘሀል...!" ብላ ለባህሪዉ መለወጥ ትልቁን ሚና ተጫዉታለች።
ሄለን መልስ ስታጣ "ምን ይዘጋሃል?"ብላ በድጋሜ ጠየቀች።
"አቡኪ ነኝ ሄሉ"
"ኦዉ አለቃችን.... ያዘዝከኝን ፈጽሚያለሁ በጣም የሚያምር አዳራሽ ነዉ የተከራየሁት። ሁለት ጥንዶችን በደንብ ማስተናገድ ይችላል።" አለችዉ። አቡበከና ኢማን ፤ ሰሚር እና ሀያት በአንድ ቀን ዉስጥ አንድ አዳራሽ ላይ አብረዉ ሊሞሸሩ ዝግጅቶቻቸዉን ጀምረዋል።
"እንዴት እንደማመሰግንሽ አላዉቅም። የሆነ ቀን ግን እክስሻለሁ ሄሉ..." አላት።
"ሌላ ነገርማ አልፈልግም። ሙስሊም ሆኜ የሚስተር ሀራም ማለቴ የሚስተር ሀላል ሁለተኛ ሚስት መሆን ነዉ የምፈልገዉ!" አለችዉ። አ
2.1K viewsMᴜᴀᴢ, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:38:59 እሺ አሁን ሚስተር ሀራም የመጨረሻው መጨረሻ ይለቀቅ የሚል????

@ikhlasstudents
2.0K viewsMᴜᴀᴢ, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:32:51 ጥያቄውን በትክክል የመለሰችው እህታችን ኑሰይባ ናት ማሽ አላህ
@Nuseybah

መልሱ መቃብር ነው!!

ወንድ ልጅ መቃብር ቦታ ለመቅበር,ለመዘየር እና ሲምት ሊቀበር....ሴት ግን ለመቀበር ብቻ ነው የምትጠቀምበት መቃብርን .....ቦታው እንደሠው ስራ ብርሀን ወይም ጨለማ ነው...

ወንድ ልጅ መቃብር ቦታ ለመቅበር,ለመዘየር እና ሲምት ሊቀበር....ሴት ግን ለመቀበር ብቻ ነው የምትጠቀምበት መቃብርን ያው ሌላው ለሴቶች የተከለከለ ስለሆነ.....ቦታው እንደሠው ስራ ብርሀን ወይም ጨለማ ነው...ሲበላ የሚለው ቀብር ላይ ወይም በምተ ሠው አድርጉልን አብሉን ስጡን ማለት ሽርክ ነው ሀረም ነው...ቀብር እየዘየሩ ወይም ለምተ ሠው ዱዓ ቢያደርጉለት ወይም ቢያጠጡት በሚለው የተፈቀደ ሀላል ነው!!
2.1K viewsMᴜᴀᴢ, edited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ