Get Mystery Box with random crypto!

ታሪክና ፍልስፍና

የቴሌግራም ቻናል አርማ hisandphilo — ታሪክና ፍልስፍና
የቴሌግራም ቻናል አርማ hisandphilo — ታሪክና ፍልስፍና
የሰርጥ አድራሻ: @hisandphilo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

Africa magazine
https://t.me/ IXNVK1XhMpczMTE0
To get magazines @Africanmagazinebot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-22 00:17:13 ሁላችንም ግድ የሚሉን ብዙ ጉዳዮች ስለአሉብን በሰዓት ተገኝ እንጂ ሰወችን አታስጠብቅ

በመመገቢያ ሰዓት ላይ አሁኑኑ የእጅ ስልክህን አስቀምጥ

የሆነ ቦታ ልጆችህን፣እንግዳ ወይም የቤት እንስሳ ይዘህ ከመምጣትህ በፊት አስፈቅድ

ሰወችን ስትገናኝ እጆቻቸዉን ሳታጠብቅ ጨብጥና ቀጥ ብለህ በመቆም አይን አይናቸዉን እያየህ ሰላም በላቸዉ

ከመግባትህ በፊት አንኳኳ ማንም ሰዉ ብርግድ አርገዉ ሲገቡበት አይወድም

አገልግሎት ለሚሰጡህ ሠራተኞችም ሆነ የሥራ አጋሮችህ ጋር በሚኖርህ ግንኙነት እነሱ አሉም አላሉ አንተ ፈገግታ አሳይ

በማህበራዊ ሚዲያ የሰወችን መረጃ ከመልቀቅህ በፊት ፍቃደኝነታቸዉን ጠይቅ ሁሉም ሰዉ እንዳንተ በየገፁ መታየትን ካለመፈለጉም በላይ አንተ ሪፖርተር አይደለህም።

524 viewsMY Struggle, 21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 17:03:21 "ሰው ሆዱን ብቻ የሚርበው ከሆነ መሶብ ነው አእምሮው አዲስ ነገር የሚራብ ግን ፈላስፋ ነዉ
ማደግ የሚፈልግ ማሰብ አያቆምም።"

ቢልልኝ ሀብታሙ
656 viewsMY Struggle, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 22:47:59 ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ችግሮችን ማስወገድ ተማር!!

ጥበብ ሕይወትን የምንቀዝፍባቸው ክህሎቶች መለኪያ ነው። ችግሮችን አስቀድሞ መከላከል ከተፈጠሩ በኋላ ከመፍታት የተሻለ ጥበብን ይጠይቃል፡፡እውነታው ሕይወት ከባድ መሆኗ ነው፡፡ ችግሮች በሁሉም አቅጣጫ በየጊዜው ይተኮሱብሃል፡፡ እጣ ፈንታ መርገጫህ ስር ጉድጓዶችን ልትቆፍርብህ ወይም መሿለኪያዎችህን ልትዘጋብህ ትችላለች። ይህንን መቀየር አትችልም፡፡ አስቀድሞ አደጋ ያለው የት ጋር እንደሆነ ከተረዳህ ግን ወዳንተ እንዳይመጣ ለማጠር እድል ይኖርሃል፡፡ በዚህ መንገድ መሰናክሎችን ሁሉ ማስወገድ ትችላለህ፡፡ ይህንን ሀሳብ አልበርት አንስታይን እንዲህ ያስቀምጠዋል፡፡ “ጎበዝ ሰው ችግሮችን ይፈታል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ችግሮችን ያስወግዳል፡፡”

ችግሩ ችግሮችን ማስወገድም የሚወደስ ነገር አለመሆኑ ነው፡፡ ሁለት ፊልሞችን አስብ፡፡
1.በመጀመሪያው ፊልም ውስጥ አንድ መርከብ ከበረዶ ክምር ጋር መጠነኛ ግጭት ይገጥመዋል፡፡ መርከቡም ይሰምጣል። በዚህ ጊዜ የመርከቧ ካፒቴን ራስ ወዳድነት በሌለበት መልኩ ራሱን አበርትቶ ተሳፋሪዎቹን ሁሉ ከመስመጥ ይታደጋቸዋል፡፡ መርከቧ ለዘለዓለሙ ከመሰወሯ ከደቂቃዎች በፊት ሁሉንም ተጓዦች በማዳን ከጀልባው ላይ ዘሎ ወደ ሕይወት አድኑ ቦቴ ውስጥ በመግባት የመጨረሻው ሰው ነበር።

2.በሁለተኛው ፊልም ውስጥ ደግሞ እንዲህ ሆነ፡፡ መርከበኛው መርከቧ ከበረዶ ክምሩ ጋር ከመጋጨቷ በፊት አስተውሎ በቂ ርቀት ላይ እንድትቆም አደረጋት፡፡

የትኛውን ፊልም ለማየት የበለጠ ትከፍላለህ?በእርግጠኝነት የመጀመሪያውን ፊልም፡፡ ሌላ ጥያቄ ደግሞ ላንሳልህ፡፡ አንተ በመርከቧ ውስጥ ተጓዥ ብትሆን ኖሮ በየትኛው ፊልም ሁኔታ ውስጥ መሆንን ትመርጣለህ? ያለ ምንም ጥርጥር ሁለተኛው ፊልምን።

እነዚህ ምሳሌዎች እውነተኛ ገጠመኞች ናቸው ብለን እናስብ፡፡ ቀጥሎ ምን ይፈጠራል? የመጀመሪያው ፊልም ውስጥ ያለው ካፒቴን የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ይጋበዛል። ምናልባት መርከበኛነቱን ትቶ አነቃቂ ንግግሮችን እያደረገ ሕይወቱን መምራት ሊጀምር ይችላል። መንገድም በስሙ ሊሰየምለት ይችላል፡፡ ልጆቹም (ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ) በአባታቸው ይኮራሉ፡፡ የሁለተኛው ፊልም ውስጥ የሳልነው ካፒቴንስ? ከስራው በጡረታ እስኪገለል ድረስ ችግሮች እንዳይከሰቱ በቅድመ ጥንቃቄ የመርከበኝነት ስራውን ይሰራል። መርሁም “ከ20 ጫማ እርቀት ላይ ልታልፈው የምትፈራውን ነገር በ500 ጫማ እርቀህ እለፈው” የሚለው የቻርሊ ሙገር የሕይወት መርህ ይሆናል፡፡

እንግዲህ ተመልከት፡- የሁለተኛው ፊልም ካፒቴን ከመጀመሪያው ፊልም ካፒቴን በሚታይ መልኩ የሚሻል ቢሆንም እኛ የምናከብረውና የምናደንቀው ግን የመጀመሪያውን ፊልም ካፒቴን ነው፡፡ ለምን? በቅድመ ጥንቃቄ የሚመጣ ስኬት ለውጪው ዓለም እይታ የሚጋለጥ አይሆንም፡፡

ጋዜጠኞች አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳይመጡ ካረጉ በሳል ሰዎች ይልቅ ችገሮችን የቀለበሱ የሥራ መሪዎችን ነው የሚያሞካሹት ።የቅድመ ጥንቃቄ ስኬቶች ለውጪው ዓለም የማይታዩ ባለመሆናቸው ምክንያት ሳይታዩና ሳይወደሱ ይኖራሉ፡፡ የእንደዚህ አይነት ስኬቶት ባለቤቶችን ጥበብ የሚያውቁት በእሱ ዙሪያ ያሉ የቡድኑ አባላት ብቻ ናቸው። እነሱም ቢሆን በተወሰኑ መልኩ ቢያውቁት ነው፡፡

የአንተስ ሕይወት? አመንክም አላመንክም ከስኬቶችህ ሁሉ 50% የሚሆኑት የቅድመ መከላከል ጥንቃቄህ ውጤቶች ናቸው፡፡ ሁላችንም እንደምናደርገው ሁሉ አንተም አንዳንድ ነገሮችን በንዝህላልነት ልታደርግ ትችላለህ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖም ግን ስህተቶችን ላለመስራት ሁልጊዜም ትጠነቀቃለህ፡፡ በአርቆ · አሳቢነት ያስወገድካቸውን በስራህ፣ በትዳርህ፣ በትምህርትህ ወይም በሌላ የሕይወትህ ዘርፍ ሊገጥሙህ የነበሩ ችግሮችን አስብ፡፡

ጥንቃቄ (prevention) ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ቅድመ ጥንቃቄ በባህሪው ቀድሞ ማየት (imagination) ይጠይቃል ቀድሞ መረዳትና የሚመጣውን መገመት ደግሞ ብዙውን ጊዜ አዛብተን የምንረዳቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህ አዲስ ሀሳብ አያመጣልንም፡፡ በዓይነ ህሊና ማየት (imagination) ማለት የመጨረሻው ፍትሃዊ ነገር ሆኖ እስክናይ ድረስ ሊሆኑ የሚችሉት ነገሮች ውጤቶችና የመፈጠር እድላቸውን ሁሉ እንዲያስብ አዕምሯችንን ማሰራት ማለት ነው፡፡ ስለሆነም አስቀድሞ ማየትና መገመት ከባድ ስራ ነው።

በተለይ ጉዳዩ ስለአደገኛ ችግሮች ሲሆን ደግሞ ቀድሞ የመገመት ሥራ የበለጠ ፈታኝ ይሆናል፡፡ ሊመጡ እድል ባላቸው ችግሮች ላይ ሁሉ እየተጠነቀቅክ መኖር ይጠበቅብሃል? ይህስ ሁልጊዜ የተጨናነቀ ሰው ሆነህ እንድትኖር አያደርግህም? ተሞክሮዎች የሚያሳዩት እንደዚያ እንዳልሆነ ነው፡፡ ቻርሊ ሙገር እንዲህ ይላል “በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የሚመጠብኝን አደጋዎች ስገምት ኖሬያለሁ፡፡ ሁልጊዜ ይሄንን እያሰብኩ፣ አደጋዎች ከመጡም እንዴት መመከት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩ መኖሬ ደስተኛ እንዳልሆን አላደረገኝም፡፡”

ሮልፍ ዶልቢ
The art of good life

ነሀሴ 10/2014 ከምሽቱ 4:47
Join us
Share it
786 viewsMY Struggle, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 20:36:47 ከአንበሳ መንጋጋ ጅብ አይነጥቅም ስጋ



ስጋው ከመንጋጋ ሲወጣ በግድ እያየኸኝ ሰላም በለኝ .....ኮንቴ በምትፈልገው መንገድ የምትፈልገውን ማግኘትን አስተምረክኛል።።#respect
790 viewsMY Struggle, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 02:36:46 "The simple things are also the most extraordinary things, and only the wise can see them."
— Paulo Coelho, The Alchemist
832 viewsMY Struggle, 23:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 22:32:38 https://m.youtube.com/channel/UCc9YHIoCAWDPJE3RwNCkUeA


ይህንን ቻናል ሰብስክሪፕሽን ይግጩት።ብዙ ነገሮችን ይዞ እየመጣላችሁ ነው።።ብዙ አዳዲስ ነገሮችን......
https://m.youtube.com/channel/UCc9YHIoCAWDPJE3RwNCkUeA
840 viewsMY Struggle, 19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 06:58:41 ሁሌም በአዕምሮአችን ውስጥ ሊቀመጡ የሚገቡ 3ቱ የህይወት መርህዎች

1. እጅግ በተናደድክበት ሰአት መልስ አትመልስ

2. እጅግ በከፋህ ሰአት ውሳኔ አታስተላልፍ

3. እጅግ በተደሰትክበት ሰአት ቃል አትግባ
807 viewsMY Struggle, 03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 21:49:32
#Wanted #ይፈለጋሉ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ አይተንፍስ እንደሻው ስለሺ እና ያቤል መንገሻ የተባሉ ግለሰቦችን (በፎቶ ከላይ ይታያሉ) በወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ብሏል።

ፖሊስ እነዚህን 2 ግለሰቦች የሚፈልጋቸው #በከባድ_የማጭበርበር ወንጀል መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቦቹን ያየ አልያም ያሉበትን የሚያውቅ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30 በ01115309047 / 01111711206 እና በማንኛውም ሰዓት በ0111119475 / 0111711012 በመደወል እንዲያሳውቀው የጠየቀው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
810 viewsMY Struggle, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:35:48 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደሚሉት ኢራን በከፍተኛ ሁኔታ በሞት የመቅጣት ዘመቻ ላይ ናት። በሐምሌ ወር የመጨረሻ ሳምንት ብቻ 32 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል። ከነዚህ ውስጥ ሦስት ሴቶች ባሎቻቸቸውን ገድለዋል በሚል በስቅላት የተቀጡ ናቸው።
“ኢራን ውስጥ በግድያ ወንጀል ለተከሰሱ የእስራት ቅጣት የለም። ይቅርታ ማድረግ ወይም መግደል ነው ያለው አማራጭ” በማለት በአሜሪካ ተቀማጭነቱን ያደረገው አብዶራህማን ቦሩማንድ ማዕከል የተሰኘው የኢራን የሰብአዊ መብት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሮያ ቦሩማንድ ያስረዳሉ።
ምንም እንኳን ከኢራን በበለጠ የሞት ቅጣት ቁጥር ያለባቸው አገራት ቢኖሩም በዓለም ላይ ካሉ አገራት ሴቶችን በሞት በመቅጣት የሚወዳደራት አገር እንደሌለ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዓመታዊ አሃዛዊ መረጃ ያሳያል። ታዲያ ኢራን በዚህ ደረጃ ለምን ሴቶችን በሞት ትቀጣለች?
የሞት ፍርድ
ባለፈው ሳምንት በስቅላት ከተገደሉት ሦስት ሴቶች በተጨማሪ ሌሎች ስድስት ደግሞ በዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ መገደላቸውን የአብዶራህማን ቦሩማንድ ማዕከል መረጃ ያሳያል።
እውነት ነው በኢራን ውስጥ የሞት ቅጣት የሚፈጸመው በአብዛኛው በወንዶች ላይ ነው። ነገር ግን ከፍተኛ ቁጥር ባለው ቅጣት ላይ የዘጠኙ ሴቶች መጨመር አሃዙን ከፍ ያደርገዋል።
“ከ2000 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 233 የሴቶች የሞት ቅጣት መዝግበናል” ሲሉ ቦሩማንድ ለቢቢሲ አስታውቀዋል።
ሙሉውን ለማንበብ፦https://bbc.in/3JCYzD9
818 viewsMY Struggle, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:42:28
ይህን እያየህ ካላመሰገንክ...
732 viewsMY Struggle, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ