Get Mystery Box with random crypto!

Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ

የቴሌግራም ቻናል አርማ harehebu — Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ H
የቴሌግራም ቻናል አርማ harehebu — Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ
የሰርጥ አድራሻ: @harehebu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.42K
የሰርጥ መግለጫ

This is official Telegram canal of Harari Regional Health Bureau. this page delivers News, Health related information and vacancy announcements on daily basis.

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 16:30:10 የጆሮ ማሳከክ ምክንያቶች በጥቂቱ

ጆሮ ለመስማት የሚያገለግለን የሰውነታችን ክፍል ነው ከዚህም ባለፈ ጆሮ ሚዛንን ለመጠበቅም ጠቀሜታ አለው። ጆሮ በተለያየ ምክንያት ሲጎዳ ከሚከሰቱ ምልክቶች አንዱ የማሳአክ ስሜት ነው።

የጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችን ማወቅ በቶሎ መፍሄዎቻቸውን እንድንፈልግ ይረዳናል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችም ናቸው።

* የጆሮ ኩክ መከማቸት

የጆሮ ኩክ (Earwax) የምንለው ሰውነታችን የሞቱ ሴሎችንና ቆሻሻዎችን የሚያጸዳበት መንገድ ሲሆን በብዛት በሚገኝበት ወቅት ግን የማሳከክ ስሜትን ይፈጥራል።

ጆሮን ለማጽዳት መሞከር ኩክ ይበልጥ ወደ ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ ይህን ከማድረግ ይቆጠቡ። ወደ ሀኪም በመሄድ ከታዪና ትክክለኛ ምክንያቱ የኩክ መጠራቀም ሆኖ ከተገኘ በጠብታ መድሀኒት ወይንም በህክምና ባለሞያ እርዳታ እንዲወጣ ይደረጋል።

*ኢንፌክሽን

የጆሮ ማሳከክ አንዳንዴ ደግሞ የ ኢንፌክሽን መኖር ምልክት ይሆናል። ጉንፋንን ወይንም ቶንሲልን የሚያስከትሉ ባክቴርያና ቫይረስ በደም ተዘዋውረው ወደ ጆሮ በመሄድ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ያደርጋሉ።

ውሀ ዋና የሚዋኙ ሰዎችም ውሃው በጆሮ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ እና ተፈጥሮአዊ የሆነውን ጀርሞችን የመከላከል አቅም በእርጥበት ምክንያት እንዲያጣ ስለሚያድርግ ሌላው የ ኢንፌክሽን መንስኤ ተደርጎ ይወሰዳል።

የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ ወደ ሀኪም በመሄድ ጸረ ባክቴርያ የሆኑ የጆሮ መድሀኒቶችን መጠቀም ተገቢ ነው።

*የቆዳ አለርጂ

በጆሮዎ ውጨኛው ክፍል የሚገኘው ቆዳዎ በአለርጂ ምክንያት የማሳከክ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል።

የመዋቢያ ቅባቶች ወይንም ቁሳቁሶች አለርጂን ሊይስከትሉ ይችላሉ። የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ አለርጂው የተከሰተበትን ምክንያት ተከታትሎ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዛም መጠቀም ማቆም ተገቢ ነው።

*ጆሮን በሹል እና ጎጂ ሊሆኑ በሚችሉ እንደ ጸጉር ሻጤ፣ አግራፍ፣ የክብሪት እንጨት በመሳሰሉት ማጽዳት የጆሮ ቆዳን ለመሰንጠቅ ስለሚችል ለኢንፌክሽን ይዳርጋል ከዚህም ባለፈ የጆሮን ውስጣዊ ክፍል በመጉዳት የመስማት ችሎታችንን ሊያሳጣን ይችላል።
ጤና ይስጥልኝ
ምንጭ:_(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም )
ተጨማሪ ምክሮችን •ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ቻናላችንን ሊንክ በመጫን የኛ ቤተሰብ ይሁኑ
የዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ዕለታዊ የጤና መረጃዎችን ይከታተሉ:
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Harari-Regional-Health-Bureau-
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/channel/UCBRny-Jdx95iwwWOiFDlM7w
ቴሌግራም፦ https://t.me/HaReHeBu
ትዊተር፦ https://twitter.com/BureauHarari/st
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
114 views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:29:56
107 views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:29:49 በህዝብ መገልገያ እና መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ ትንባሆ የማጨስ ክልከላ መመሪያ ተግባራዊነቱ ላይ ጠንካራ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሆና ተገለጸ።

የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ የትንባሆ ቁጥጥር መመሪያ አተገባበር ዙሪያ ከ Management Science For Health Tobacco Policy Action Fund for Africa (TOPAFA) Project ዳሬክተር እና ሌሎች አባላቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

በእለቱም በክልሉ የትንባሆ ቁጥጥር መመሪያ አተገባበር ተዘዋውረው ተጎብኝቷል።

ማይክል እክፓ የTobacco Policy Action Fund for Africa (TOPAFA) ዳይሬክተሩ እንዳሉት በህዝብ መገልገያ እና መሰብሰቢያ ቦታዎች ትንባሆ የማጨስ ክልከላ መመሪያ በሐረሪ ክልል እና በሌሎች ክልሎች ተፈፃሚ በማድረግ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብሏል።

በቀጣይም ከተቆጣጣሪ ባለስልጣን ጋር በጋራ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው በህዝብ መገልገያ እና መሰብሰቢያ ቦታዎች ትንባሆ የማጨስ ክልከላን ማስታወቂያዎችን በማስቀመጥ መመሪያውን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍትሂ ማህዲ በበኩላቸው ትንባሆ ተጠቃሚ ግለሰቦች የግል ጤንነታቸውን ከመጉዳት ባሻገር በዙሪያቸው የሚገኙ ቤተሰቦችና አካባቢ ማህበረሰብ ላይ ቀላልና ከባድ የጤና ጉዳቶችን ያስከትላል ብሏል።

ህብረተሰቡ በየአካባቢው የትንባሆና አደንዛዥ እጽ ክልከላን ተግባራዊ ለማድረግ በሚሰራውን ስራ ላይ በጋራ መስራት እንደሚገባው አስታውቀዋል።

በክልሉ ክልከላውን ተግባራዊ ለማድረግ ግንዛቤ ማሳደግ እና የማስተማር ስራ እና ህገ ወጥ የትንባሆ ምርት ቁጥጥርን ከባለድርሻ አካለት ጋር እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የክልሉ ጤና ቢሮ  የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረመዳን ኢብራሂም ናቸው።

ትንባሆን ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የክልሉ ህብረተሰብ ከተቆጣጣሪ ክፍሉ ጋር በቅንጅት እየሰራ የለውን አጠናክሮ መቀጠል እንደለበት አያይዘው ገልጸዋል።
159 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:29:46
135 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:31:59 እርግዝና እና እናትነት
ምግብ እና እርግዝና
ለእርጉዝ እናቶች ጠቃሚ ሀሳብ
አሁንም ሆነ በወደፊት ህይወቱ ለልጅሽ ጤናማ አካላዊና አእምሮአዊ እድገት የተመጣጠነ ምግብ አስፈላጊ ነው፡፡
ስለዚህ በእርግዝናሽ ወቅት ምግብሽ የሚከተሉትን ምግቦች እና ንጥረ ነገሮች ቢያካትት መልካም ነው፡፡
ኦሜጋ-3
በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ በምግብሽ ውስጥ ዓሣ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በተለይ የዓሳ ዘይት ምንጭ የሆኑ ዓሦችን፡፡
ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች
በየቀኑ ቪታሚን ዲ (5 µg) ለመውሰድ ሞክሪ፡፡ በቪታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን ተመገቢ፡፡ ዓሣ፣ እንቁላል ወይም በቪታሚን ዲ ተጠናክሮ የተዘጋጀ ወተት ጠጪ፡፡ ለመጀመሪያዎቹ 12 የእርግዝና ሳምንታት ፎሊክ አሲድ (400 µg) በየቀኑ ብትወስጂ መልካም ነው፡፡
ካልሲየም
በቀን ሶስት ጊዜ ወተትና የወተት ውጤቶችን በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በየቀኑ ወተት፣ አይብና እርጎ ጥቂት-ጥቂት ሶስት ጊዜ ውሰጂ፡፡
ብረት (Iron)
በብረት ማዕድን የበለፀጉ ምግቦችን በቀን 2 ጊዜ በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በብረት የበለፀጉ ምግቦች ውስጥ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል፣ ባቄላና አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች ይካተታሉ፡፡
ጣፋጮች
ጣፋጭ የበዛባቸውን ምግቦችና መጠጦች አልፎ-አልፎ በተለየ አጋጣሚ ብቻ ተመገቢ፡፡ ለምሳሌ በሳምንት ሁለቴ፡፡
አትክልትና ፍራፍሬ
በቀን ውስጥ ለ5 ጊዜ ያህል ከምግብሽ ጋር አትክልትና ፍራ-ፍራፍሬ ለመመገብ ሞክሪ፡፡
ተጨማሪ ምክሮችን •ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ቻናላችንን ሊንክ በመጫን የኛ ቤተሰብ ይሁኑ
የዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ዕለታዊ የጤና መረጃዎችን ይከታተሉ:
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Harari-Regional-Health-Bureau-
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/channel/UCBRny-Jdx95iwwWOiFDlM7w
ቴሌግራም፦ https://t.me/HaReHeBu
ትዊተር፦ https://twitter.com/BureauHarari/st
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
178 views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:31:54
148 views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:10:57 የ2014 ዓ.ም የጤና መረጃ ስርዓት እቅድ ግምገማ ተካሄደ።
የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ከክልሉ ጤና ተቋማትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የ2014 ዓ.ም የጤና የመረጃ ስረዓት ስራን ገምግመዋል።
በመድረኩ የክልሉ ጤና ተቋማትና አጠቃላይ የክልሉ የ2014 ዓ.ም የመረጃ ስርዓት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በመረጃ ስርዓት የተሻሻሉ ስራዎች ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በበጀት አመቱ በጤና ተቋመት የመረጃ ስርዓትን ይበልጥ ለማጠናክር የሰለጠና ሰዉ ሀይል ለማፍራት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ፣የኔትዎርክና መብረት ዝርጋታ እና የተለያዩ የግብዓት ድጋፎችን ተደርገዋል።
የመረጃ ስርዓትን የማጥራት እንዲሁም የመረጃ ቋትን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል።
በዘርፋ አሁንም የመረጃን አያያዝና አላላክ እንዲሁም መረጃን መሠረት ያደረጉ ስራዎች ከመስራት አንፃር ውስንነቶች አሉ ተብሏል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ ወቅቱን የጠበቀ ክትትልና ድጋፍ ፣ የግብረ መልስ የመስጠት ልምድን መዳበር እና ምርጥ ተሞክሮዎችን የማስፋት ስራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በጤናዉ ዘረፍ ሁለንተናዊ ለዉጥ ለማምጣት የመረጃ ስረዓት መጠቀም ይገባል ያሉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኋላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ ናቸው።
ስራን ለነገ የማሳደርና በስራ ላይ የሚፈጠርን ግዴለሽነት ማስወገድ እንደሚገባ ገልጸው መረጃን በስራ ላይ መጠቀም ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።
በስራ ላይ ያሉ ውስንነቶች በመቅረፍ እንዲሁም በቅንጅት አሰራሮችን በማስፋት የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በክልሉ ጤና ቢሮ የእቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ አብዱሰመድ አሊ መረጃን መሠረት ያደረጉ ዉሳኔ የመጠቀም በህልን በማደበር የሚፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት በትኩረት መሠራት አለበት ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፤የወረዳ የጤና ፅ/ቤት እና የጤና ጣቢያ ሀላፊዎች፤የጤና መረጃ ስርዓት በለሞያዎችና DHA/DUP አሰተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
224 views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:10:37
202 views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:42:05
የነፃ የህክምናና የምርመራ አገልግሎት ምክኒያት በማድረግ ለማረሚያ ቤት ኮሚሽን የህግ ታራሚዎች አልባሳት ድጋፍ ተደረገ።
በዛሬው እለት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን እና በሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል።
225 viewsedited  15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:29:26

የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ቻናላችንን ሊንክ በመጫን የኛ ቤተሰብ ይሁኑ
የዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ዕለታዊ የጤና መረጃዎችን ይከታተሉ:
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/Harari-Regional-Health-Bureau-
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/channel/UCBRny-Jdx95iwwWOiFDlM7w
ቴሌግራም፦ https://t.me/HaReHeBu
ትዊተር፦ https://twitter.com/BureauHarari/st
101 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ