Get Mystery Box with random crypto!

የመንፈስ ፍሬዎች ❤️ 🕊 🙏

የቴሌግራም ቻናል አርማ etelawyan3 — የመንፈስ ፍሬዎች ❤️ 🕊 🙏
የቴሌግራም ቻናል አርማ etelawyan3 — የመንፈስ ፍሬዎች ❤️ 🕊 🙏
የሰርጥ አድራሻ: @etelawyan3
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.51K
የሰርጥ መግለጫ

👉በዚህ ቻናል በቅዱሱ መፅሐፋችን ለይ 📖ገላ 5÷22 ሰፍረው ስለ ምናገኛቸው የመንፈስ ፍሬዎች ማለትም ስለ :-
❤️ፍቅር
😁ደስታ
🕊ሰላም
🙏ትዕግሥት
✋ቸርነት
😍በጎነት
✝እምነት
🤗የውሃት፥
🙊ራስን መግዛት
በፅሁፍ እንደሁም ደግሞ በድምፅ እንማማራለን እንዲሁም :-
🗣በተለየ ሁኔታ በተለየ ቀን የበደላችሁን እንዱሁም የበደላችሁትን ሰው በይቅርታ ልባችሁን ከጥላቻ ወደ ፍቅር ከጨለማ ወደ

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-08 11:59:04
ስለ እህቶቻችን ሰለ ሴት እንስቶቻችን ዝም አንልም

ሆዱን ከመረጠ ምሁር ለህሊናዉ የተገዛ መሀይም ይበልጣል ወዳጄ

እኛ እቤት ቁጭ ብለን በረደን በምንልበት ወቅት እራሳቸውን ለመቀየር ሲሉ በዚህ ክረምት ብርድና ዝናብ ሳይበግራቸው ለሚሰሩ እንዲሁም በባዕድ ሀገር ሆነው እድሜያቸውን ጊዜያቸውን ህይወታቸውን ሳይሰስቱ ደከመኝ ታከተኝ ሳይሉ ለእናት ለአባታቸው እንዲሁም ለእኛ ለወንድሞቻቸው ሲሉ ለሚታትሩ እህቶቻችን

በእውነት ስለ እውነት ለእነርሱ በምድራዊ ቃላት ከማመስገን በታላቅ ትህትና ከማክበር ባለፈ የምንቸራቸው ምንም አይነት ክፍያ ከእነርሱ አበርክቶት እነርሱ ለእኛ ካደረጉልን ከሆኑልን አንፃር የሚገባ ባይሆንም ሰው ነንና ከሚገባቸው በታች ቢሆንም በአቅማችን ልክ ማድረግ የምንችለው ቢያንስባቸውም ግን እነርሱ :-

በተፈጥሯቸው እናትነትን በሴትነት ውስጥ የታደሉ ናቸውን ደስ ተሰኝተው ይቀበሉናል ብቻ ግን እኛ ላልከፈልናችሁ ዋጋና ጊዜያችሁ የሰማይም የምድርም ገዢ የሆነው

ፈጣሪ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ ባላችሁበት ከክፉ ሁሉ ይሰውራችሁ በመንገዳችሁ ሁሉ እርሱ ይቅደም እንቅፋቱን ያንሳላችሁ ጎባጣውን ያቅናላችሁ ከቀኝና ከግራም እቅፍ ድግፍ አድርጎ በህይወታችሁ ዘመን ሁሉ ጤናችሁን ሰቷችሁ ሰላሙን አድሏችሁ ፍቅሩን እንደ ሸማ አልብሷችሁ የልባችሁን መሻት ይፈፅምላችሁ የቀደሙት አባቶቻችን እንደሚሉት ትልቁ ፀጋ የሰው ፍቅር ነውና ያያችሁ ሁሉ ይውደዳችሁ የወደዳችሁ ሁሉ ያክብራችሁ ይሄ የኔ የወንድማችሁ የአብስራ መልዕክት ነው ።

የአብስራ ተስፋዬ @yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
160 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, edited  08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 19:33:59 ለምሽታችሁ ማድመቂያ ለብርዱ ደግሞ ማሞቂያ

የማይሳሳት ማነው ? የማይሞከር አይደለምን ? የማይወድቅስ ማነው?የማይንቀሳቀስ አይደል ? መራመድ እስካለ መውደቅ አለ፣ማፍቀር እስካለ መጎዳት አለ፣መፈተን እስካለ መውደቅ አለ...ይህ የማይለወጥው የህይወት ህግ ነው!የውድቀት መድሀኒቱ ደግሞ መሞከር ነው።ብዙ መሞከርሽ ያለማቆምሽ እንጂ የማቆምሽ ምክንያት ሊሆን አይገባም።ምክንያቱም ያኔ መጀመሪያ ስትጀምሪው ከነበረሽ ብቃት አሁን ላይ ያለሽ ብቃት ይበልጣልና፣ደግመሽ ስትሞክሪው በቀላሉ ታሸንፊዋለሽ!ታዲያ ለምን ታቆሚያለሽ???
ከመውደቅ ይልቅ አስከፊው ወድቆ መቅረት ነው።በፍርሀት ታስሮ ምንም ካለመሞከር የበለጠ ሞት የለም!የአለም ሁኔታ በፍጥነት በሚቀያየርበት በዚህ ዘመን ሁለት ምርጫ ነው ያለው-ወይ ወደኋላ መሄድ ወይ ወደፊት መገስገስ።ባሉበት መቅረት የሚባል ነገር የለም!!!
ታዲያ የቱ ይሻልሻል??አዳዲስ ነገሮችን በመሞከር አደጋዎቹንም በመጋፈጥ ወደ ፊት መራመድ ወይስ በፍርሀት ታጥሮ ምንም ሳይሞክሩ ወደኋላ መመለስ!!ምርጫው ያንቺ ነው!!አንተንም ይመለከታል??!!!

ያማረ ምሽት ተመኘሁ

ጥበብ እግዚአብሔር ነው!

የአብስራ ተስፋዬ
@yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
111 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:12:01 እንደምን አረፈዳችሁ ወዳጆቼ
ዛሬ በጣም ደስ የሚል ቀን ነው።አንድ የተቀደሰውና የተባረከው የሰንበት ቀን ነው።ሁለት ደግሞ በጣም የምንወደው በየአመቱ ጓግተን የምንጠብቀው ጾመ ፍልሰታ የጀመረበት ቀን ነው

እንኳን አደረሳችሁ እግዚአብሔር አምላክ ፆሙን አስፈፅሞን ለበዓለ ዕርገቷ ያድርሰን

ፆሙን በፍቅር ልብ በተዋበ ትህትና በንፁህ ህሊና እናሳልፈው ዘንድ ተመኘሁ

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ነገር ልንገራችሁ ያው በፆም ሰዓት ዘፈን ማዳመጥና ሌሎችም አለማዊ ተግባራት ከፆም ጋር በቀጥታ የሚጋጩትን በሙሉ ባለማድረግ ለእግዚአብሔር ያለንን መታዘዝና ለእመቤታችን ያለንን ፍቅር እንግለጽ!
በተለይም እስቲ እንደ ቻሌንጅም አድርጉትና ይቺን15 ቀን ዘፈን በዞረበት አትዙሩ ከዛ ምን እንደምትሆኑ እዩት ልንገራችሁ ምንም አትሆኑም ግን በሱ ምትክ ዘፈን ዘፈን ሲላችሁ መዝሙር ክፈቱና አመስግኑ እባካችሁ ከዛ ውጪ ከሰው ጋርም ክፉ ላለመነጋገር እራሳችሁ ጠብቁት እላለሁ!
እስቲ ምን ታስባላችሁ?comment ወይም በ reaction አሳዩኝ
መልካም ፆም!

እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
የእመ ብርሀን ምልጃዋ አይለየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!

የአብስራ ተስፋዬ
@yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
118 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 12:42:07 የተዋሕዶ ልጆች የቻናሌ ቤሰቦች እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም
ፆመ ፍልሰታ ዓደረሳቹ ።

"አባ ጊዮርጊስ ሰጋስጫ" ይንዲህ ይላል
( ፅኑ ቁስል ያለፅኑ መድሐኒት አይድንም ስለዚህ የሐጥያቴ ቁስል ፅኑ እንደሆነ አውቆ ልጅሽ ለመድኀኒት አዋቂዋ ላንቺ ሰጥቶኝ ሄደ።)
ይላል ።

በዚህ ፆም ወቅት ሸክም የከበደው ጀልባ እንደሚሰጥም ሁሉ በሐጥያት ላለመስጠም ከምግብ ሸክም እራሳችንን በፆም ገተን ከፅድቅ ስራ ላለመራቆት በሱባኤ በፀሎት እየተጋን ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመድኀኒት ልጇ የከበደንን ታቀልልን ዘንድ በአማላጅነቷ እየለመንን ፆሙን እንጨርስ ዘንደ የእግዚአብሔር መልካም ፍቃዱ ይሁንልን አሜን ።

የአብስራ ተስፋዬ @yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
114 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 12:30:56 "በህይወት የሌሉ ሰዎች በህይወት ካሉት ሰዎች በላይ ብዙ አበቦችን ይቀበላሉ። ምክንያቱም ቅሬታ ከማመስገን በላይ ጠንካራ ነውና!" ታዲያ ዛሬ ማመስገን ያለብን ሰው ካለ ኋላ እንዳይረፍድብንና ቅሬታ ውስጥ እንዳንገባ አሁኑኑ ከልብ በመነጨ ሁኔታ ማመስገን ተገቢ ነው።
ያለበለዚያ ነገ ምን እንደሚፈጠር አናውቅምና አሁኑኑ የምንወዳቸው ሰዎች በህይወት እያሉ እናመስግን። በተለይ ብዙዎቻችን የቅርብ ቤተሰቦቻችንና ጓደኞቻችንን ሁሌ የምናጣቸው ስለማይመስለን በህይወት እያሉ አንዴ እንኳን ምስጋናችንንና ፍቅራችንን ሳንገልጽላቸው ህይወታቸው ያልፋል። ያኔ የልብ ስብራቱ ከባድ ነውና አሁኑኑ በጊዜያችን ተጠቅመን ለተደረገልን ነገር ሁሉ እናመስግን!

share በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ!

ቸሩን ሁሉ የምንሰማበት ቀን ያድርግልን!


የአብስራ ተስፋዬ
@yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
145 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 10:10:52 አይ ዘመን!

ሴቱ በቃና ወንዱ በምርቃና ያበዱበት ዘመን!!
ከመፃፍ ቅዱሱ ቃል ይልቅ ኮማንድ ፖስት ሚፈራበት ዘመን!!
ከሀይማኖት አባቶች ይልቅ ፌድራል ፖሊስ ሚፈራበት ዘመን!!
I phone መያዝ ዲግሪ ከመያዝ የተሻለ ተደርጎ ሚታሰብበት ዘመን!!
ልጅ ወላጅን መጦር ቀርቶ ወላጅ ልጆቹን የሚጦርበት ዘመን!!

ለሁላችንም ፈጣሪ ልቦናን ይስጠንና መልካሙን ለማድረግ ያብቃን

የአብስራ ተስፋዬ
@yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
164 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 13:19:14 "መስጠትን ተምሬያለው ተርፎኝ ሳይሆን ማጣትን ስለማውቀው ነው!" በእርግጠኝነት በአንድም በሌላም አጋጣሚ መራብን የማያውቅ ሰው የለም! የተራበን ሰው የሆነ ምግብ ስትሰጠው ምን ሊሰማው ይችላል? ብርዱ ያሰቃየውን ሰው ልብስ ስትደርብለት እንዴት አድርጎ ይደሰት! ታድያ የዚህ ደስታ ምንጭ ከመሆን በላይ በዚህ ምድር ምን ትልቅ ነገር ይገኛል! የተረፈህ ስለሆንክ ስለሞላህ አይደለም ግን ስለሚያስፈልጋቸው ጥቂቷን ስጥ እና ብዙ ተደሰት ወንድሜ እህቴ አንቺም ካለችሽ አጉርሺ ስለሚመልሱልሽ ሳይሆን ስለሚያስፈልጋቸው ነው!

በፍቅር የምታምሩበት በይቅርታ የምታሸበረቁበት ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ

የአብስራ ተስፋዬ
@yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
817 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 08:27:41 ሐሙስን እንዲህ ብንጀምርስ?

በመጀመሪያ ለዛሬዋ እለት ላደረሰን ለቸሩ ፈጣሪያችን ክብር ምስጋና ይገባዋል

እለታትን እያፈራረቀ በእድሜያችን ላይ እድሜ እየጨመረ ዛሬ ላይ አድርሶናል ነገንም በሱ ቸርነት እናያለን
ሁሉም እንደአቅሙ ለሰው ልጅ የሚበጅ መልካም ስራ ሰርቶ መዋል በቅን ልቦና በመነሳሳት እራስና ወገንን በመርዳት እየሰራን ብናልፍ ለራሳችን ክብር ለሀገር ኩራት በሆንን ነበር ነገር ግን ግዜው አልፈቀደም የፊጢኝ ወደሗላ አስሮ እየጎተተን ነው
በፈጣሪ ያችን ቸርነት ሁሉም በግዜው ያልፋልና በግዜያችንም በተሰጠን እለት ያቅማችንን መልካም አድርገን እንለፍ ።

እንኳን ለዛሬዋ እልት በሰላም በጤና አደረሰን እያልኩ ሳምንቱ ;-
የታመመ የሚድንበት
ያጣ የሚያገኝበት
ያዘነ የሚፅናነበት
የተራበ የሚጠግብበት
የተጠማ ጠጥቶ የሚረካበት
ፍቅር ያጣ ፍቅር የሚያገኝበት
የታሰረ የሚፈታበት
ፍትህ ያጣ ትክክለኛ ፍርድ የሚያገኝበት መልካም ደስ የሚል ጊዜ ሳምንት እንዲሆንልን እመኛለሁ እግዚአብሔር ይጠብቀን ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ ሰናይ ቀን ወዳጆቼ

የአብስራ ተስፋዬ
@yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan
177 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 16:37:32 መኖር

የመኖር ውሉ በራስ ታዛ መድመቅ ብቻ አይደለም… የሌሎችንም ማገር ማጥበቅ እንጂ…

በበጎ ቃል – የታመመ ልብ ትፈውሳለህ ፣ የጎበጠ ሞራል ታቀናለህ … በፍቅር ኃይል – ቂም በቀል ትሽራለህ፣ ጥላቻን ትንዳለህ … ሰው ነህና ብዙ የምትሰጠው ይኖርሃል…

በደንብ ይደመጥ ታተርፉበታላችሁ

የአብስራ ተስፋዬ
@Yeabm

••••••፨፨ ፨፨•••••••
@Etelawyan
@Etelawyan3
••••••፨፨ ፨፨•••••••
776 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 15:17:36 "እንደ ፍቃድህ ይሁን"

አዎ! የትም መሔድ አይጠበቅብህም ፤ ስለሁሉም ነገር ፈጣሪህን አማክር ፤ አምላክህን ተማፀን ። እርሱ በጊዜው ውብና ድንቅ አድርጎ በሚሰራው ነገር አንዳች ጥርጣሬ እንዳይገባህ ። አምላክ አንዳነተ አንተ ላይ ለመጨከን አይቸኩልም ። ነገር ግን የተሻልክ እንድትሆን የሚያስተምርህንና የሚያጠነክርህን መንገድ ይመርጥልሃል ። በዛ ውጥ ይሰራሃል ፣ ፈልገህ እንድታገኘው መንገድ ይከፍትልሃል ፣ ትዕግሥትን እንድትለማመድ ፣ ፅናትን እንድትኖረው ፣ እምነትህን እንድትተገብረው ያደርግሃል ። ችኮላህን ቀንስ ፣ ሁሉን አበጃጅቶ ፣ አስተካክሎ እስኪሰጥህ አንተም ጊዜ መስጠቱን እወቅበት ። በጎ ፣ መልካምና ፍፁሙን ስጦታውን መቀበል ከፈለክ ታገስ ፤ ፅናት ይኑርህ ፤ እመነው ።



የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm

•••••፨፨ ፨፨•••••••
@Etelawyan
@Etelawyan3
••••••፨፨ ፨፨•••••••
175 views𝕪𝕖"𝕒𝕓"𝕤𝕣𝕒 𝖙𝖊𝖘𝖋𝖆𝖞𝖊, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ