Get Mystery Box with random crypto!

እንደምን አረፈዳችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በጣም ደስ የሚል ቀን ነው።አንድ የተቀደሰውና የተባረከው | የመንፈስ ፍሬዎች ❤️ 🕊 🙏

እንደምን አረፈዳችሁ ወዳጆቼ
ዛሬ በጣም ደስ የሚል ቀን ነው።አንድ የተቀደሰውና የተባረከው የሰንበት ቀን ነው።ሁለት ደግሞ በጣም የምንወደው በየአመቱ ጓግተን የምንጠብቀው ጾመ ፍልሰታ የጀመረበት ቀን ነው

እንኳን አደረሳችሁ እግዚአብሔር አምላክ ፆሙን አስፈፅሞን ለበዓለ ዕርገቷ ያድርሰን

ፆሙን በፍቅር ልብ በተዋበ ትህትና በንፁህ ህሊና እናሳልፈው ዘንድ ተመኘሁ

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ነገር ልንገራችሁ ያው በፆም ሰዓት ዘፈን ማዳመጥና ሌሎችም አለማዊ ተግባራት ከፆም ጋር በቀጥታ የሚጋጩትን በሙሉ ባለማድረግ ለእግዚአብሔር ያለንን መታዘዝና ለእመቤታችን ያለንን ፍቅር እንግለጽ!
በተለይም እስቲ እንደ ቻሌንጅም አድርጉትና ይቺን15 ቀን ዘፈን በዞረበት አትዙሩ ከዛ ምን እንደምትሆኑ እዩት ልንገራችሁ ምንም አትሆኑም ግን በሱ ምትክ ዘፈን ዘፈን ሲላችሁ መዝሙር ክፈቱና አመስግኑ እባካችሁ ከዛ ውጪ ከሰው ጋርም ክፉ ላለመነጋገር እራሳችሁ ጠብቁት እላለሁ!
እስቲ ምን ታስባላችሁ?comment ወይም በ reaction አሳዩኝ
መልካም ፆም!

እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
የእመ ብርሀን ምልጃዋ አይለየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!

የአብስራ ተስፋዬ
@yeabm

Join and share
@Etelawyan3
@Etelawyan
@Etelawyan