Get Mystery Box with random crypto!

ጠቃሚ ታሪኮች እና ምክሮች @tesh_m

የቴሌግራም ቻናል አርማ tesh_m — ጠቃሚ ታሪኮች እና ምክሮች @tesh_m
የቴሌግራም ቻናል አርማ tesh_m — ጠቃሚ ታሪኮች እና ምክሮች @tesh_m
የሰርጥ አድራሻ: @tesh_m
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 217
የሰርጥ መግለጫ

ልዩ ልዩ መሰናዶዎች በዚህ ቻናል ያገኛሉ
📖 ወግ እና መጣጥፎች
📖 ከመጻሕፍት እፍታ
📖 ትረካዎች
📖 የአባቶች ብሒል እና
📖 ብዙ ኪነ ጥበባዊ መሰናዶ በጽሑፍ እና በድምጽ ይቀርብላችኋል

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-22 11:27:54 ለመላው ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳቹ መልካም የስቅለት በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

መልካም በዓል
433 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 10:02:11
744 views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 09:28:22 https://www.linkedin.com/posts/mekedelamekuria_communicator-leader-storytelling-ugcPost-6912234317125496832-sEEn?utm_source=linkedin_share&utm_medium=member_desktop_web
631 views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 07:20:33
መሸበርና መፍራት የነገን ችግር አያስወግድልንም ይልቁኑስ የዛሬን ደስታ
ያሳጣናል።

ሕይወት፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች ፡፡ የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው፡፡

ሰዉ የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቈየት፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር ነው…፡፡

በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡

ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

ሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰደ

@tesh_m
@tesh_m
512 viewsedited  04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 07:20:08
"Holding a grudge Doesn't make you strong; It makes you bitter. Forgiveness doesn't make you weak it sets you free" #forgive

ሁሌም በደልን ሳስብ አንድ ነገር ይመጣብኛል ፤ በአንድ ክፉ ሰው ስራ ስንት መልካም ሰዎች እድል ይከለከላሉ? በአንድ ሌባ ሰው ምክንያት ስንት ታማኞች እንደሌባ ይቆጠራሉ? በአንድ ከዳተኛ ምክንያት ስንት እውነተኛ አፍቃሪዎች እድል ሳይሰጣቸው ይገፋሉ? ....ምክንያቱም ይቅር ማለት ስለሚከብደን።

ይቅር ስንል ከበደሉን ሰዎች ይልቅ ቅልል የሚለን እኛን ነው። የተበደልነውን እያሰብን አቀርቅረን የምንኖር ከሆነ፤ ቁስላችንን ሊጠግኑ የሚችሉ፤ እንባችንን ሊያብሱ የሚችሉ፤ ካጎነበስንበት ቀና ሊያደርጉን የሚችሉ ሰዎች በአጠገባችን ሲያልፉ አናያቸውም። ይቅር ስንል ግን በሰው ልጆች ተስፋ አንቆርጥም።

ይህች አለም ክፉዎችንም ደጎችንም አሰባጥራ ይዛለች። በመጥፎ ሰዎች ስራ ግን ደጎች እንደሌሉ ይቆጠራሉ፤ ምክንያቱም መልካም ሰዎች በቂመኛ ሰው አይን ውስጥ ስለማይገቡ ነው። የበደሉንን እያሰብንን የሚክሱንን ባናርቃቸው መልካም ነው!!!

ይቅር በማለት እራሳችንን ነጻ እናውጣ!!!

ሚስጥረ አደራው


@tesh_m
@tesh_m
480 viewsedited  04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 09:04:22
Kleptomania
ይሄ ህመም የተለያየ እቃዎችን ለመስረቅ ያለ የውስጥ ግፊትና ያንንም በተደጋጋሚ መተግበር ስሜቱንም መቆጣጠር ሲያቅት ነው።
የሚሰርቁትን ዕቃ ወይ ጭራሹኑ የማይፈልጉት ወይ የማያስፈልጋቸው ይሆናል።
ነገርግን ዕቃውን ለመስረቅ ያላቸው የውስጥ ግፊትን መቆጣጠር አይችሉም። ከቁጥጥራቸው ውጭ ነው።
ክሊፕቶሜኒያ ስሜትን የመቆጣጠር እክል ውስጥ ካሉ ህመሞች ውስጥ ይመደባል።
ሁሌም ከሰረቁ በኋላ የጥፋተኝነት ስሜት እንደሚሰማቸው ይገልፃሉ።
ይሄ ህመም ያለባቸው ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም አሊያም በጓደኛ ተፅዕኖ ወይ ዘራፊ ሆነው ሳይሆን ለመስረቅ ያላቸው ፍላጎትና ስሜት ሃይለኛና ሊያቁሙት የማይችሉት ስለሆነ ነው።
ምልክቶች
ከመስረቃቸው በፊት ከፍተኛ የሆነ የውጥረት ስሜት ሲኖራቸው ከሰረቁ በኋላ እርካታ ደስታ ያገኛሉ (ለቅፅበት ቢሆንም)
የታቀደበት ስርቆት አይደለም
ስርቆቱ በንዴት ወይ ሰው ለመበቀል አይደለም
የሚሰርቋቸው ዕቃዎች ባያስፈልጓቸውም ለመስረቅ ያላቸውን ስሜት አይቋቋሙትም (አንሳው አንሺው ብሎ የሚገፋፋው ከባድ ስሜት )
ከሰረቁ በኋላ ፀፀትና ጥፋተኝነት ስሜት
ከሰረቁ በኋላ በስራቸው ማፈር መሸማቀቅ እና እስራት መፍራት
ተደጋጋሚ የሆነ የመስረቅ ፍላጎት
ከጓደኛ ከቤተሰብ ሳይቀር መስረቅ
የሰረቁትን ዕቃ አይጠቀሙትም ወይ በሚስጥር ይመልሱታል ወይ ይለግሳሉ
የንግግር ህክምና በብዙ ያግዛል!
#ያለ_አዕምሮ_ጤና_ጤና_የለም!
ቃልኪዳን
@tesh_m
480 views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 17:06:20
[ Photo ]
ምን እንደ - ምልሽ ኣላውቅም ።
ምንም ማለት ኣለመቻሌ ግን ፡ እንደ እከክ ይበላኛል ።
ገና ለገና ስለመጣንበት መንገድ ፡ ስላጣነው ነገር ሳስብበው ፥ በመካከላችን የተሸጎጡ ግልብ ዓመታት ልበሉኝ የመድረሳቸውን ያኽል በቀረብን እላለኹ ። ላያስችለኝ • • •

አናንያ ተሾመ

@tesh_m
@tesh_m
407 views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 20:23:11
ጆሮ እንስጥ ... ትልቅ ስጦታ ነውና!

ህመማችን በዝቷል። መታመማችንን በግርግር ስለአለባበስነው አይሽርም። ድብርት .. ስራ አጥነት ... ዘረኝነት.. ክፋት ... ወርሰውናል። እልፎች ቀኑን በመባዘን ና በውሸት ፈገግታ አሣልፈው ምሽቱን ግን ከህመማቸው ጋር ይታገላሉ።

ደህና ነኝ ያለ ሁሉ ደህና አይደለም።

ዞር ብለን ዙርያችንን እንመልከት ። ቤተሰቦቻችንን ፣ ወዳጆቻችንን ፣ ባልደረቦቻችንን ... ምን ያህል ቀርበናቸዋል ? ጆሮስ ሰጥተናቸዋል? ወይስ እየተሸነጋገልን ነው?

የኛ ያልናቸው ሰዎች በከባድ የውስጥ ህመም ሲሰቃዩ መረዳት አቅቶን "አምሮብሀል ...አምሮብሻል " ብለን እየተሸነጋገልን ከሆነ ቆም ብለን ዙርያችንን እንቃኝ። ጆሮዋችንን የሚሹ አንደበቶች በዙርያችን አሉና።

ሠዎች ህመማቸውን ..መከፋታቸውን ሲያወሩን ትልቁ ስጦታ "ጆሮ መስጠት" ነው። ለሁሉም ነገር መምከር አይገባንም። ምክር ብለን የምንወረውረው ነገር በራሱ ተጨማሪ ህመም ሊሆንባቸው ይችላልና ።

ወትሮስ የእኔን ህመም እኔን ያልሆነ ሰው መች ይረዳዋል። ሁላችንም አለምን የምናያት ራሣችን ከቆምንበት ጥግ ነውና ለኛ የሠራ አስተሳሰብ ና መፍትሄ ሁሉ ለሌላው አይሰራም።

ጆሮ ግን እንስጥ። ሳይንሱም "አድማጭ ማግኘት " ለድብርት መፍትሄ ነው ። ሁላችንም ደግሞ ልናወራው የምንሻው እውነት ከአንደበታችን ጓዳ አለና ጆሮ እንሰጣጥ።

ቆም ብለን እናስብ!

በዙርያችን ላሉ ሁሉ ጆሮ እንስጥ!



#አንድ_ሀሣብ
ተስፋ ንዳ
481 views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-17 18:41:06
አብይ መሀመድ ይባላል የፌስቡክ አድራሻው ነው መረጃችሁን ይዛቹ ብታወሩት ያስተናግዳቹሃል።

https://www.facebook.com/100060854380986/posts/333443732027437/?app=fbl

በዚህ ሊንክ ማውራት ይቻላል
379 views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-17 07:18:47
ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ሳይኮአናሊሲስ
=========================
የሲግመን ፍሮይድ ሳይኮአናሊሲስ የሚያተኩረው 'ስውሩ አእምሯችን' ስሜታችንን፣ ሀሳቦቻችንን እና ፀባያችንን ከግንዛቤያችን ውጭ በሆነ መንገድ እንደሚቆጣጠር እና እንዳንገነዘበው በከፍተኛ ጉልበት ራሳችንን እንዴት እንደሚያሳምነን ነው። በተለይ ደግሞ የሴክስ እና የሀይለኝነት ውስጣዊ ግፊት ሳንገነዘበው ብዙ ባህሪያችንን እንደሚወስኑ ያምናል።

እንደ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ሳይኮአናሊሲስ ግን ሀሳባችን፣ ስሜቶቻችንና ፀባያችንን የሚወስነው በህፃንነት ከወላጆቻችን ጋር የነበረን ግንኙነት ነው። ወላጆቻችን ፍቅር ሳይሰጡን ከቀረን ከፍ ስንል "ፍቅር ብሎ ነገር የለም" ብለን 'ጠንካራ' ሆነን በስሜት ራሱን የቻለ(emotionally self-sufficient) እንሆናለን።

በህፃንነት ወላጆቻችን ያናደዱን ከነበረ ከፍ ስንል ንዴታችን ይቀጥላል ነገር ግን ሌላ ኢላማ ላይ ያነጣጥራል። በህፃንነት ወላጆቻችንን ወይም ፍቅራቸውን እናጣለን ብለን እንሰጋ ከነበረ ስናድግ ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች ያስጨንቁናል።

ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ሳይኮአናሊሲስ ታካሚዎች የናፍቆታቸውን፣ የንዴታቸውን፣ የጭንቀታቸውን ትክክለኛ ስር እንዲያገኙ መርዳት ነው። ስሩን ካገኙት በኃላ ስለራሳቸው እና ስለአለም ያላቸውን አተያይ ሙሉበሙሉ በመለወጥ (radical restructuring of working models) ደስተኛ መሆን ይችላሉ።

ሀሳቦቹ በ John Bowlby "Parent-Child attachment" ላይ የተመሰረቱ ናቸው

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
@tesh_m
@tesh_m
#share_and_join
382 viewsedited  04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ