Get Mystery Box with random crypto!

ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yecrstosbet — ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yecrstosbet — ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰርጥ አድራሻ: @yecrstosbet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 646
የሰርጥ መግለጫ

"ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀል ላይ ሞቶ
የአምላክችንን ቤት አንተዉም ከቶ"
@yecrstosbetgp
ለማንኛውም አስታያየት ለመስጠት ከፈለጉ በዚህ ያናግሩን👇👇👇👇
@zemichale7

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-19 16:24:23 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን

@yecrstosbet
174 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 19:17:11 የድኾች መከታ

" በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። መዝሙረ ዳዊት 91 : 7

     በምድራችን ላይ ስልጣን ያላቸው፣ ባለጠጋ የሆኑ ከበርቴዎች ገንዘባቸውን በሚያምኑት ባንክ ያስቀምጣሉ፤ ግቢያቸውን በኤሌክትሪክ አጥር ያሳጥራሉ፣ ቤታቸውን በሰረገላ ቁልፍ ይቆልፋሉ፣ በሼፐርድ ውሻ ይጠበቃሉ፣ ንቁ ዘበኛ ይቀጥራሉ ከዛም አልፎ የጎልያድ ታናሽ ወንድም በሚመስሉ ጋርዶች ይከበባሉ። ለምን ቢባል ያላቸው ሀብትና ስልጣን ጠላት ስለሚያበዛባቸው ነው።

   የሚገቡበት ቤት ደረጃውን የጠበቀ ነው የሚያዙት ምግብ ቀድሞ ተቀምሶ ነው የሚሰጣቸው። መንገድ ቢሄዱም ከነርሱ በቀር ማንም ላያልፍ ተዘግቶላቸው ነው። ይህ ሁሉ ጥንቃቄ የሚደረግው ለሀገሪቱ አስፈላጊና ዓይን ናቸው ተብሎ ስለታመነባቸው ነው። እነዚህ ጋርዶች በእነርሱ አቅም ሊመክቱት የሚችሉትን ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለውም ቢሆን ይከላከላሉ። አንድ የማይችሉት የማይመክት ጠላት አላቸው እርሱም ሞት ነው። ሞትን የማያስቀሩ ጋርዶች ጥቂት እንኳ የማይታገሉት ጋርዶች ናቸው።

ወዳጆቼ እኔና እናንተ ይሄ ሁሉ ጠባቂ የሌለን ደግሞም ያለጭንቀት የምንወጣውና የምንገባው ጠላት ስለሌለን ይመስላችኋል? ያውም በግራ ሺህ በቀኝ አስር ሺህ በድምሩ አስራ አንድ ሺህ ጠላት ነው ያለብን። እግዚአብሔር ይመስገን እነዚህን ሁሉ ጠላቶች ሳናይ አይቶልን ሳንበረግግ አስበርግጎ ድል የሚነሳልን የሚጠብቀን ቅዱስ እግዚአብሄር ነው። እግዚአብሄር መልካም ነው ሳናይ የተወረወሩትን መክቶልናል እያየን የተሰነዘረብንንም ጉልበት ሆኖን አልፈነዋል።

     እንኳን አስራ አንድ ሺህ ጠላት ይቅርና አንድ ጠላትም ብዙ ያውካል። እግዚአብሔር ግን ለአንዱም ብቻችንን አልተወንም።  ክብር ይግባው።
254 views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 15:50:47
310 views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 19:59:35 እግዚአብሔር የሰውን አላፊነት ለራሱ ሰጠ ።

እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"
574 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 12:51:59
472 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-11 20:13:21 ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል ! ።

የክርስቲያን ግቡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል ነው ። ይህ ማለት እርሱ በምድር ሲኖር በቅድስና ፣ በፍቅር ፣ በይቅርታ ፣ በበጎነት ፣ በቸርነት .... ያለ ኃጢአት እንደ ተመላለሰ እርሱን እየመሰሉ በኑሮውና በትምህርቱ አብነቱን መከተል ማለት ነው ። ሐዋርያው ዮሐንስ እንዴት በክርስትና ሕይወት መመላለስ እንዳለብን እና እርሱን ስለ መምሰል ሲናገር "ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤
በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል" 1ኛ ዮሐንስ 2 ፥ 5-6 ።

በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአኗኗራችን ልንመስለው እንደሚገባን ያሳስበናል ። ማንኛውም ሰው ክርስቶስን መሆን በፍጹም አይችልም አልተፈቀደለትም ። ግን እሱን መምሰል ይችላል ፤ ምክንያቱም ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሎናል “እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥1 ።

መምሰል ሲባል ክርስቶስ ኃጢአትን ተጠይፎ ጽድቅን እንደወደደ እኛም ኃጢአትን ጠልተን ጽድቅን መራብ አለብን ማለት ነው ። ትልቁ ነገር ክርስቲያን መሆን ሳይሆን ክርስትናን መኖር ነው ። ለምሳሌ ክርስቲያን ነኝ እያልን ግን የክርስቶስ ሕይወት በክርስትናችን ውስጥ ከሌለ መዳረሻው የማይታወቅ ጉዞን እንደ ማጓዝ ማለት ነው ። እሱን የሚመስል ኑሮን ከኖርን ግን የማያሳፍር እና ተስፋ ያለውን ጉዞ እንጓዛለን ።
734 views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 20:15:44
413 views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 20:45:17 ትልቁ_እግዚአብሔር_ሰው_አክባሪ_ነው

እግዚአብሔር ሰውን ያከብራል ። ከእሱ በላይ ማንም የለም ግን ትሁት ነው ። ትንሽ ስልጣን ያላቸው ሰዎች አጋጥመዋችሁ አያውቅም ? ምድርን የጨበጡ ይመስላቸዋል ፣ ካለ እነሱ የኛን ጉዳይ ማንም ሊፈታ እንደማይችል ነው የሚያስቡት ፣ ከተናገርናቸው "ዋ እሰራልሀለሁ" ይሉናል ። ትንሿ ስልጣን ሰውን ለመናቅ ምክንያት ትሆነናለች ። አይ እኛ ።

እግዚአብሔርን ግን ማን ይመስለዋል ? ስልጣኑን በፍቅር ያጠረ ። የፈጠራቸውን የልጆቹን ጩኽት እያባበል የሚሰማ ። ምንም ማድረግ እየቻለ ምንም ያላደረገ ። ስልጣንን መቀማት እየቻለ ሌላ ስልጣንን የሚሰጥ ። ወይ ፍረድ ወይ ውረድ እየተባለ ። የለክም እንተ እያልነው ። ይገርማል ሁሉን ቻይ ዝም ሲል ።

@yecrstosbet
@yecrstosbet
397 views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 16:52:30 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

#ኢየሱስ_ክርስቶስ_ያዘኝ

      በህፃንነትህ ስምዖን ታቀፈህ፤ ቅድስት እናትህ ማርያም አዘለችህ አንተ ደግሞ እኔ ኪሎዬ ሳይሆን ኃጢአቴ የሚከብደውን አዘልከኝ፣ ለስላሳው ገላዬን ሳይሆን በክፋት የሻከረውን ማንነቴን አቀፍከው። እንደኔ ዓይነት ብዙ አለ እንዳንተ አይነት ግን ማንም የለምና ቻልከኝ።

       ያለ ልክ ዝቅ ዝቅ ብትልም ያለ ልክ ከፍ ከፍ ብለኻል። በሰው ብትገፋም በአባትህ ከብረኻል።  ልትጥለኝ ሳይሆን ልትደግፈኝ ይዘኸኛል። ልታወርደኝ ሳይሆን ልታከብረኝ ወደላይ ከፍ ከፍ አርገኸኛል። ለጊዜው አይደለም ለዘላለም ያዝከኝ። መንግስትህን የሚገረስስ፣ ስልጣንህን የሚጋፋ እስኪመጣ ሳይሆን ማንም ከእጅህ ላይፈለቅቀኝ አጥብቀህ ያዝከኝ። እንደኔ ዓይነት ብዙ አለ እንዳንተ ግን በአገር በምድሩም አይገኝም።

        የመድኃኒቴ ቀንድ፣ የመዳኔ ዓርማ፣ የቆምኩብህ ዓለት፣ የተደገፍኩብህ ምርኩዝ፣ የተማረኩልህ ፍቅር፣ ያጌጥኩብህ ውበቴ፣ ኢየሱስ ስልህ ልጄ ብለህ በስስት የምትጠራኝ የዘላለሜ አምላክ ክበርልኝ። ስለወደድከኝ እወድኃለሁ!!!
471 views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 21:06:47
440 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ