Get Mystery Box with random crypto!

✞ትንሽ ዝምታ ✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamongog7 — ✞ትንሽ ዝምታ ✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamongog7 — ✞ትንሽ ዝምታ ✞
የሰርጥ አድራሻ: @hamongog7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K
የሰርጥ መግለጫ

"ለመሆኑ አንተ ከሌላው እድትበልጥ ያደረገህ ማነው?ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ?ከተቀበልህ ታዲያ፣እንደተቀበልህ ለምን ትመካለህ?

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 21:15:12 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






23 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:32:39 እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡
7 views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:12:51 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






34 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:18:06 ( ባልጀራህ ቤት እግርህን አታብዛ፣ምስጢርን ታወጣለህና፣ሀሜትን ትናፍቃለህና፣በአእምሮ ያለውን ሀሳብ ሁሉ፣ለባልጀራህ አታጋራ፣እውቅትህን ጥቂት በጥቂት አከማቸው፥ያከማቸኸውን እውቀት ግን መልሶ አንተን እንዳይደረምስህ ተጠንቀቅ።

ትንሽ ቃል ተናገር፣ብዙ ቃልን አድምጥ፣በሰዎች ዘንድ ፍቅርን ስጥ፣አህዛብን፣መናፍቃንን በሙሉ ልብህ አትመናቸው። ልባቸው ደንዳና ነውና....

አዋቂ ለመምሰል የምታደርገው፣ከንቱ ጥረት፣ከንቱነትህ አላዋቂ እንዳያደርግህ ተጠንቀቅ።

ከሁሉም በፊት የምታውቀው፣ሀይማኖትና፣እምነትህን ባለአዋቂነትህ እንዳይነጥኩህ.....የእግዚአብሔርን ቃል መርምረህ....ተቀበል፣

መመርመር ወደ ጥበብ የምትገባበት በር ነውና....ጥበብን ባገኘህ ጊዜ.....እግዚአብሔርን መፍራትህን በጥበብህና ባንተ ልብ ውስጥ ፀንቶ ይቀመጥ።

በሀይማኖትህን፣ሲነቅፉት ባየህም፣በሰማህም ጊዜ.... ስሜታዊነትን አስቀምጠህ፣በመረመርከው እውቀት ልክ፣ያለህን እውቀት መስክር።ዋጋህ ትልቅ ነውና።

@hamongog7
@hamongog7

Surafel
T
99 views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:36:54 #ከንስሐ_ርቀን_ይቅርታን_አናገኝም

ንስሐ ለተጠመቁ ሰዎች ከጥምቀት በኋላ የተሰጠች ሀብት ናት፡፡ ይህንንም የሚያስረዳ ነገር በጥምቀት ከእግዚአብሔር ከምትገኝ ልጅነት ሁለተኛ ማዕረግ ናት፡፡ በሃይማኖት ገንዘብ ያደረግነው የመንግስተ ሰማይ መያዣ ከናት፡፡

በንስሐ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቸርነት እናገኛለን፡፡ ንስሐ ለሚሿት ሰዎች የተከፈተች የይቅርታ በር ናት፡፡ በንስሐ በርነት ከፈጣሪ ወደሚገኝ ቸርነት እንቀርባለን፡፡ መከላከያ ከሚሆን ከንስሐ ርቀን ይቅርታን አናገኝም፡፡

አምላክ የጻፈው መጽሐፍ እንደተናገረ ሁላችን በድለናልና ያለ ዋጋ በይቅርታው ከኃጢአት እንነጻለን፡፡ ንስሐ እግዚአብሔርን በመፍራት፣ በሃይማኖትና በልቡና የምትገኝ ሁለተኛ ጸጋ ናት፡፡ ሀብታተ ምስጢራት ከሚገኙበት ከመንፈሳዊ ፍቅር እስክንደርስ ድረስ የሚጠብቀን መንፈሳዊ ዕውቀት ነው፡፡

(ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ)
126 views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:07:24 ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
119 views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:22:21 "መንፈሳዊ ጥበብን የምትወድ ነፍስ ዘወትር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡ ሰው ሆይ! ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርሱብህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያን ጊዜም ክፉው መልካም ይኾንልሃል፡፡

"እንዴት?" ብለህ የጠየቅኸኝ እንደኾነም፦ "በደል የሚፈፅመው ክፉ ነገር የሚቀበለው ሳይኾን ክፉ ነገር የሚያደርሰው ሰው ነውና" ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስልሃለሁ፡፡

ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
101 views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:59:00 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






131 views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 00:02:45 የሕይወትህን መንገድ ወደ እግዚአብሔር ብታደርግ ያን ጊዜ እውነተኛውን እረፍት ታገኛለህ።

አባ ሙሴ ጸሊም
134 views21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:23:18 "ድንግል ሆይ አትፍሪ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና...እነሆ ትፀንሻለሽ፣ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ...ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ።"

" እንደ ቃልህ ይሁንልኝ።"

ምን አይነት ንፅህናና ክብር፣ቃላት ከሚፅፍአቸው በላይ የሆነውን የድንግል ማርያም ትህትና መናገር የሚቻለው ማን ነው??

.. ድንግል ማርያም ልጇን ኢየሱስን ከመውለዷ በላይ ድንቅ ተአምር ምን አደረገች ቢሉ.... ከመልአኩ ብስራት .... ለተገኘው ቃል ... #በትልቅ_ልቦና_ትልቅ_ዝምታ በእርሷ ዘንድ ውስጥ ፀንቶ መቆየቱን ከተአምራት በላይ ተአምር ነው።

ይህን ብስራት ለተበሰረላት፣ሌላ ሴት ብትሆንስ?? ይህን ቃል ከልቦናዋና በማህፀኗ ትሸከም ይሆን??

በልቧ ትጠብቀው የነበረው ማህደር እውነት መሆኑን ስትሰማ...በታላቅ ዝምታ በልቧ መያዟን ሳስብ በራሱ እውነት ንፁህ ሴት ናት ብዬ ቃል ላጠረኝ ድንግል ሁሌም ክብርና ምስጋና ለእሷ እሰጣለሁኝ።

ድንግል ሆይ..ንፅህት ሆይ....በማህፀንሽ ከነበረው እሳት የበለጠ....የመልአኩን ብስራት ስትሰሚ የዝምታሽ ነበልባል...እንዴት ቻልሽው??አምላክ በውስጤ አለ፣ለማለት የሚያበቃ ቃል ከአንደበትሽ እንዴት ያዝሽው??

ክብርና ምስጋና ከተወደደው ልጅሽ ጋር!!

Surafel
T
163 views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ