Get Mystery Box with random crypto!

( ባልጀራህ ቤት እግርህን አታብዛ፣ምስጢርን ታወጣለህና፣ሀሜትን ትናፍቃለህና፣በአእምሮ ያለውን ሀሳብ | ✞ትንሽ ዝምታ ✞

( ባልጀራህ ቤት እግርህን አታብዛ፣ምስጢርን ታወጣለህና፣ሀሜትን ትናፍቃለህና፣በአእምሮ ያለውን ሀሳብ ሁሉ፣ለባልጀራህ አታጋራ፣እውቅትህን ጥቂት በጥቂት አከማቸው፥ያከማቸኸውን እውቀት ግን መልሶ አንተን እንዳይደረምስህ ተጠንቀቅ።

ትንሽ ቃል ተናገር፣ብዙ ቃልን አድምጥ፣በሰዎች ዘንድ ፍቅርን ስጥ፣አህዛብን፣መናፍቃንን በሙሉ ልብህ አትመናቸው። ልባቸው ደንዳና ነውና....

አዋቂ ለመምሰል የምታደርገው፣ከንቱ ጥረት፣ከንቱነትህ አላዋቂ እንዳያደርግህ ተጠንቀቅ።

ከሁሉም በፊት የምታውቀው፣ሀይማኖትና፣እምነትህን ባለአዋቂነትህ እንዳይነጥኩህ.....የእግዚአብሔርን ቃል መርምረህ....ተቀበል፣

መመርመር ወደ ጥበብ የምትገባበት በር ነውና....ጥበብን ባገኘህ ጊዜ.....እግዚአብሔርን መፍራትህን በጥበብህና ባንተ ልብ ውስጥ ፀንቶ ይቀመጥ።

በሀይማኖትህን፣ሲነቅፉት ባየህም፣በሰማህም ጊዜ.... ስሜታዊነትን አስቀምጠህ፣በመረመርከው እውቀት ልክ፣ያለህን እውቀት መስክር።ዋጋህ ትልቅ ነውና።

@hamongog7
@hamongog7

Surafel
T