Get Mystery Box with random crypto!

✞ትንሽ ዝምታ ✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamongog7 — ✞ትንሽ ዝምታ ✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamongog7 — ✞ትንሽ ዝምታ ✞
የሰርጥ አድራሻ: @hamongog7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K
የሰርጥ መግለጫ

"ለመሆኑ አንተ ከሌላው እድትበልጥ ያደረገህ ማነው?ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ?ከተቀበልህ ታዲያ፣እንደተቀበልህ ለምን ትመካለህ?

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-24 18:05:08 የዚህ ዓለም ሰዎች "ፍሩን፣ አክብሩን፣ አመስግኑን" ብለው ደጅ ይጠናሉን? እንዲህ ቢያደርጉስ ሰው ሁሉ የሚስቅባቸው የሚሳለቅባቸው አይደለምን?

ታድያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "(ክርስቲያን) ምስጋናው ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም" (ሮሜ.2፥29) ብሎ አስተምሮን ሳለ ክርስቲያኖች ነን የምንል እኛ ለምንድነው ሰዎች እንዲያደንቁን የምንፈልገው? ለምንድነው ከእግዚአብሔር ይልቅ ከሰዎች ምስጋናን የምንሻው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
376 views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:36:09 የአባ ዘወንጌል የትንቢት እውነታዎች
የኖኅ መርከብ መድረሻ
የትንቢቱ ፍፃሜዎች
የ666 ደባ በኢትዮጵያ ላይ
,መጽመፈ ሔኖክ
የዕፀ መሰወር ጥናታዊ ፁፍ
ታቦተ ፅዮን
ነጋዴው ታምሪን

open.........open .........open
Open........"open .........open
Open.........open...........open
Open........open............open

እርሶም በዚህ ዙሪያ እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
"ትምህርቱን በናታኒም ቲዩብ ይከታተሉ"።


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘

የተወደዳችሁ የተዋሕዶ ልጆች ዛሬ የማስተዋውቃችሁ ናታኒም ቲዩብን ነው! በናታኑም ቲዩብ የተለያዩ የአውደ ምሕረት ትምህርቶችን፣ስብከቶችን እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬዎችን የምታገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ስለሆነም ሰብስክራይብ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታችሁን የበለጠ እንድታጎለብቱ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እጠይቃችኋለሁ ።
ናታኒም ቲዩብ ሼር ሰብስክራይብ አድረጋችሁ ቻናላችናን ተቀላቀሉ "
ሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌

█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░►OPEN ▒▓█
12 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 22:38:40 "ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
220 views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:49:36 "የኖኅ መርከብ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ሆኖም ቤተክርስቲያን ከኖኅ መርከብ እጅግ ትለያለች፡፡ ወደ መርከቡ የገባ ዶሮ ሲወጣም ዶሮ ነው፡፡ ተኩላውም ከመርከቡ ሲወጣ ተኩላ ነው፡፡ ከቤተክርስቲያን ግን ዶሮ ገብቶ ርግብ ሆኖ ይወጣል፡፡ ተኩላውም በግ ሆኖ ይወጣል፡፡ ቤተክርስቲያን ኃጢአተኞችን ተቀብላ ጻድቃን አድርጋ የምታወጣ መርከብ ናት’’
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
272 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 22:30:06 ተወዳጆች ሆይ! ትዘምራላችሁ፡፡ [ከጸሎታቱ ትሳተፋላችሁ፡፡ ቅዳሴውን አስቀድሳችሁ] እምነታችሁን ትመሰክራላችሁ፡፡ ይህን ኹሉ አድርጋችሁ ስታበቁ ግን አትቆርቡም፡፡ ለምን? ከሰማያዊው ማዕድ የማትሳተፉት ለምንድን ነው? አንዳንዶቻችሁ፡- “እኔ ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ ልቆርብ አይገባኝም” ብላችኋል፡፡ እንዴ! እንደዚህ’ማ ካላችሁ ከመዝሙሩም፣ ከጸሎታቱም፣ ከቅዳሴውም ልትሳተፉ አይገባችሁማ!

እስኪ ንገሩኝ! የንጉሥ ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ መላእክት “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ የሚያመሰግኑት የሚያገለግሉትም ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ ንጉሡ በፊታችሁ አለ፡፡ ታዲያ እናንተ እንዲሁ ቁልጭልጭ እያላችሁ ትቆማላችሁን? ልብሳችሁ አድፎ ተዳድፎም ሳለ ምንም እንዳልተፈጠረ ኾናችሁ ወደ ቤታችሁ ትመለሳላችሁን?

ወደ መንግሥተ ሰማያት፣ ወደ ሰማያዊው ንጉሥ ማዕድ ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠርቶን ሳለ ተዘጋጅተን እንደ መቅረብ ወደ ኋላ እንላለንን? እንደዚህ የምናደርግ ከኾነ ታዲያ ተስፋ ድኅነታችን ምንድን ነው?

“መቅረብ ያልቻልኩት’ኮ” ብለን ደካማ መኾናችንን እንደ ሰበብ ማቅረብ አንችልም፡፡ ተፈጥሮአችንን እንደ ምክንያት ማቅረብ አንችልም፡፡ እንዳንቀርብ የሚያደርገን ደካማ መኾናችን አይደለም፡፡ አዎን ከሰማያዊው ማዕድ እንዳንሳተፍ የሚያደርገን እንዲሁ ሳንዘጋጅ ልል ዘሊላን ኾነን መቅረባችን እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት አይደለም፡፡

ስለዚህ እማልዳችኋለሁ! [ንስሐ ገብተን እንደ ቸርነቱም ተዘጋጅተን] በፍርሐትና በረዓድ ኾነን [በግድ] እንቅረብ እንጂ “ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ” ብለን አንራቅ፡፡ [ከኃጢአት ኹሉ የሚያነጻን የክርስቶስ ደም እንጂ ኃጢአተኛ ነኝና አይገባኝም ብለን መራቃችን አይደለምና፡፡] ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ በድፍረት ወደ እርሱ መቅረብ ይቻለን ዘንድ ዛሬ በፍርሐትና በረዓድ ኾነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ ያኔ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” ከሚላቸው ጋር ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በመንግሥተ ሰማያት ይኾን ዘንድ ዛሬ ወደ ሰማያዊው ማዕድ እንቅረብ፡፡

(በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው)
523 views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 06:02:22 ዝም ብላቹ አመስግኑት

አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር ለማመስገን አንድ የተለየ ምክንያት ይፈልጋሉ፤ እንደነዚ አይነት ሰዎች የብርሀንን መልካምነት ለመናገር ጭለማ እስኪመጣ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፤ ወዳጆቼ እግዚአብሔር ለማመስገን ምክንያት አትፈልጉ፣ ቢሆንላቹም ባይሆንላቹም፣ ቢሳካላቹም ባይሳካላቹም፣ ሁኔታዎች ቢመቻቹም ባይመቻቹም ጌታን ማመስገን አታቋርጡ፤ እግዚአብሔር 24 ሰዓት ካለ እንከን የሚያመሰግኑት መልአክቶች አሉት ቢሆንም ግን ከኛ ከልጆቹ የምስጋናን ቃል መቀበል ይፈልጋል፤ ስለዚህ እርሱ ምስጋናን ከኛ ከፈለገ አንደበቶቻችንን ለምስጋና እንክፈትለት።
549 viewsedited  03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 06:02:22 “ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።”
— ሮሜ 8፥6
452 views03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 06:02:22 #ልብ_ብለው_ያንብቡ

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ ለንስሓ ልጁ በሰርጓ ቀን መገኘት ባለመቻሉ የላከላት ደብዳቤ

“ልጄ! ለሰርግሽ የነፍስ አባትሽ እኔ ጐርጐርዮስ ይህን ግጥም ስጦታ አድርጌ ልኬልሻለሁ፡፡ አባት ለሚወዳት ልጁ ሊሰጣት የሚችለው የተሻለው ምክርም ይህ እንደ ኾነ አምናለሁ፡፡

“ኦሎምፒያታ ሆይ፥ እውነተኛ ክርስቲያን ለመኾን ያለሽን ፍላጎት ዐውቃለሁና በደንብ አድምጪኝ! እውነተኛ ክርስቲያን እንዲሁ መኾንን የሚመኝ ብቻ ሳይኾን እንደዚያ ለመኾን ሊጥር ይገባዋል፡፡

“ከኹሉም በላይ፥ እግዚአብሔርን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ከእርሱ ቀጥሎም በቅዱስ ወንጌል እንደ ታዘዘው እንደ ጌታችንና መድኃኒታችን [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርገሽ ባልሽን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ስለዚህ እጠይቅሻለሁ! ጌታዋንና ፈጣሪዋን [ኢየሱስ ክርስቶስን] የማታከብርና የማትወድ ሴት በዚህ መንገድ ባልዋን እንዴት አድርጋ ልታከብረውና ልትወደው ትችላለች?

“በጋብቻሽ ውስጥ የትዳር አጋርሽ ይኾን ዘንድ እግዚአብሔር መርጦ ለሰጠሽ ባል ያለሽ መውደድ፣ ስሜትና ፍቅር እጅግ ኃያል ሊኾን ይገባዋል፡፡ ይህ ሰው አሁን የሕይወትሽ ዓይን፣ የልብሽም ደስታ ነውና፡፡

“እግዚአብሔርን እንደምትወጂው፥ ባልሽንም ያለ ቅድመ ኹኔታ ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ አንቺ ሴት እንደ ኾንሽና ታላቅ የኾነ ዓላማና ግብ እንዳለሽ፥ ኾኖም ዓላማሽና ግብሽ የቤትሽ ራስ ሊኾን ከሚገባው ባልሽ የተለየ እንደ ኾነ ዕወቂ፤ ተረጂም፡፡ ባንቺ ዕድሜ ላይ ያሉት አንዳንዶች ኹለቱም ፆታዎች እኩል [ራስ ናቸው] ብለው የሚሰብኩትን አትስሚ፤ የጋብቻንም ግዴታ [ወይም ዋና ዓላማ] አስቢ፡፡ እነዚህን ግዴታዎች [ወይም ዓላማዎች] ስታውቂ የቤተሰብሽን ተግባራት ለማከናወን እንደ ምን ያለ ትዕግሥትና ጽናት እንደሚያስፈልግሽ ታውቂያለሽና፡፡ እንደ ሚስት እጅግ ጥንካሬን ገንዘብ የምታደርጊውም በዚህ መንገድ ነው፡፡

“ወንዶች እንዴት በቀላሉ የሚቈጡ መኾናቸውን በርግጥ ልታውቂ ይገባሻል፡፡ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም እንደ በረኻ አንበሳ ይኾናሉ፡፡ እንግዲህ ሚስት ጸንታ ልትቆምና የነፍስ ልዕልናዋን ልታሳይ የሚገባት በዚህች ቅጽበት ነው፡፡ አንበሳን የማስለመድ ሥራ መሥራት አለብሽ፡፡ አንበሳን የሚያስለምድ ሰው አንበሳ ሲያገሳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝም ጸጥ ይላል፡፡ በጸጥታውና በርጋታውም የአንበሳውን ቊጣ ይቈጣጠራል፡፡ በርጋታና በለሆሳስ ኾኖ ያናግረዋል፤ ይደባብሰዋል፤ በቀስታ ያሻሸዋል፤ በጥቂት በጥቂቱም አንበሳው ቊጣውን ይተዋል፡፡

“ባልሽ ስሕተት ሲሠራ በፍጹም ልትነቅፊው፣ ልትንቂው ወይም ልታስነውሪው አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ መሥራት ያለበትን ነገር ባይሠራና ከዚሁ የተነሣም ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ቢኾን፣ ወይም እጅግ የምትፈልጊውና አግባብ ነው ብለሽ የምታስቢውን ባያደርግ እንኳን ባልሽን መናቅ ከአንቺ ልታርቂ ይገባል፡፡ ክፉዎች አጋንንት ዘወትር ቤታችሁን ለማፍረስና የጥንዶች መንፈሳዊ አንድነትን ለመበተን እንደሚሞክሩ ዕወቂ፡፡”

( #ከገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ከትንሿ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ የተወሰደ)
450 views03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 06:02:22 ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን እኛ አየናቸውም አላየናቸውም በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ላይ መንግሥተ እግዚአብሔርን መቅረፅ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ስንጠራቸው አቤት ስናዛቸው ወዴት የሚሉንን ሳይኾን ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ እምነትን፣ የውሃትን፣ ራስን መግዛትን፥ በአጭር ቃል የመንፈስ ፍሬዎችን ገንዘብ ያደረጉ ልጆችን ማሳደግ ነው (ገላ.5፡22-24)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን የገዛ ክብራቸውን እንዲያውቁና በዚያ መሠረት እንዲያድጉ - ይኸውም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ክርስቶስን የሚመስሉ፣ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ቅዱሳን እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው (ዘፍ.1፡26)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የእኛ ንብረት እንዲኾኑ ሳይኾን የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እስራኤላውያንን ለክርስቶስ ያዘጋጃቸው እንደ ነበረ፥ እኛም በዚያ መንገድ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጆቸ እንዲኾኑ ማዘጋጀት ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት የልጆቻችንን መጥፎ ጠባይ ከማራቅና እንዲታዘዙን ከማድረግ በላይ፥ እግዚአብሔርን በፍጹም ኃይላቸው እንዲወድዱ ማድረግ ነው፡፡ ቅዱሳንን እንዲያፈቅሩ፣ በቃል ኪዳናቸው ታምነው እነርሱን እንዲመስሉ ማድረግ ነው፡፡

ትንሿ ቤተ ክርስቲያን፣ ገጽ 507-508
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
587 viewsedited  03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ