Get Mystery Box with random crypto!

✞ትንሽ ዝምታ ✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamongog7 — ✞ትንሽ ዝምታ ✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamongog7 — ✞ትንሽ ዝምታ ✞
የሰርጥ አድራሻ: @hamongog7
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K
የሰርጥ መግለጫ

"ለመሆኑ አንተ ከሌላው እድትበልጥ ያደረገህ ማነው?ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ?ከተቀበልህ ታዲያ፣እንደተቀበልህ ለምን ትመካለህ?

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-22 07:59:06 #ድንግል_ሆይ የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል።

#ደንግል_ሆይ መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።

#ልዑሉን_የወለድሽ_ልዕልት_ሆይ የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ።

#ድንግል_ሆይ የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። #ትንሣኤሽን #የሚያምን ሁሉ #አሜን ይበል።

#ምልጃሽ #ኢትዮጵያን #ይታደግ። ለአለም ምህረት ይሁን ።

#Memhr_Abunu_Mamo
633 views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 22:18:32 ጸሎት ከውስጥ የሚመነጭ የልብ መቃተት ስለሆነ ቃላት ብቻ ሊገልጹት አቅም የላቸውም። በተመሰጠ ልብ ፣ በመንፈሳዊ ሀሳብ ፣ በተሰቀለ ኅሊና ወደ አምላካችን የምንነጠቅበትና ከፈጣሪያችን ጋር የምንነጋገርበት ስለሆነ ጸሎት ከቃላት በላይ ነው። በዝምታ እያለን በኅሌናችን ልንመሰጥ እንችላለን።

ጸሎት እግዚአብሔርን የናፈቀ ልብ ሲቃ ነውና ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ይለካበታል። ሰውና እግዚአብሔር መገናኘት የሚችለው በዚህ ዓይነት ከልብ ተፈንቅሎ የሚወጣ ጸሎት ስለሆነ ከዚህ መንፈሳዊ ሕብረት ውጪ ሆነው የሚጮኹት ጩኸት ረብ የለሽ የቃላት ጋጋታ ነው። እግዚአብሔር አምላክን የምትወድ ፣ የምታፈቅር ከሆነ ትጸልያለህ ፤ ከጸለይህ ደግሞ ፍቅረ እግዚአብሔር በውስጥህ ያድጋል። እስኪ በዚሁ ፍቅር የተቀጣጠለና ልብ የሚነካውን የዳዊትን ጸሎት አስተውል "አምላኬ አምላኬ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች ፤ ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች። መቼ እደርሳለሁ ? የአምላኬንስ ፊት መቼ አያለሁ።...." (መዝ. ፷፪፥፩)። ደረቅ መሬት በእውነት ዝናምን እንደምትናፍቅ እግዚአብሔርን መናፈቅና መጠማት ይህ አይለይም? እውነት ነው ፍጹም ይህ ነውና።

ብጹእ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
273 views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 23:16:13 እግዚአብሔር አለ! በዝምታ
እግዚአብሔር አለ!በቀና ልብ
እግዚአብሔር አለ!በስቃይ፣በደስታ

እግዚአብሔር አለ!ሁሌም አለ።ማየት የሚቻለው ማነው??ማነው እግዚአብሔርን በዝምታ ውስጥ ማየት የሚችለው??ማነው እሱ እስከሚናገር በፅናት የሚቆይ??ማነው ያ ፃድቅ ሰው እግዚአብሔር አምላኩን በትንሽ ዝምታ፣በሰፊው የሚያየው?

ትንሽ ዝምም እንበል።ቅዳሴውን በአርምሞ፣ፀሎቱን በርጋታ፣እንባችን በዝግታ፥ልመናችን በጥሞና፣ልግስናችን፣በድብቅ፣

ዝምም እንበል፣ፍቅራችን በልባችን፣
በደላችን፣ችግራችን፣ሀዘናችን፣ሁሉ በዝምታ ውስጥ እናሳልፈው።

እግዚአብሔር አለ በዝምታ
ውስጥ!!


ሱራፌል/
304 views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:11:50 ራሱን የሚቀጣ ጻድቅ ነው!
302 views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 10:44:09
እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ትባላለች። ይህም፡-

"ንጽሕት" ስንል፡-
ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር፣ ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከኃልዮ ንጽሕት ናት፡፡ "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ" ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል፡፡ (ተአምረ ማርያም)

"ጽንዕት" ስንል:-
ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ ጊዜ ጸኒስ ድኅረ ጸኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት ቅዱስ ያሬድ "ወትረ ድንግል ማርያም" ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ)

"ክብርት" ስንል፡-
ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው እመቤታችንን ግን የምናከብራት "የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና፡፡

"ልዩ" ስንል፡-
ከእርሷ በቀር እናት ሆና ድንግል እመቤት ሆና አገልጋይ የሆነች በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና፡፡

በዚህም እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ እንላታለን፡፡
607 views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 08:18:49 "#እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ"

አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው።

ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡

ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡

ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡

በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን!

(ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን)
840 views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 06:59:54 እንደ ጋኔን ቅናተኛ የለም፡፡ ቅናቱ ግን በሰው ልጆች ላይ እንጂ እርሱን በሚመስሉ አጋንንት ላይ አይደለም፡፡ ሰው ግን በገዛ ወንድሙ ላይ ይቀናል፤ በአጋንንት እንኳን በጭራሽ የማይደረግ በገዛ ቤተሰቡ ላይ ይቀናል፡፡ ታዲያ እንደዚህ ዓይነት ሰው እንዴት ይቅርታን ያገኛል? እንዴት ምሕረት ቸርነትን ያገኛል?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
576 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 00:18:10 ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን እኛ አየናቸውም አላየናቸውም በሕሊናቸው ጓዳ በልቡናቸው ሰሌዳ ላይ መንግሥተ እግዚአብሔርን መቅረፅ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ስንጠራቸው አቤት ስናዛቸው ወዴት የሚሉንን ሳይኾን ትዕግሥትን፣ ቸርነትን፣ በጎነትን፣ እምነትን፣ የውሃትን፣ ራስን መግዛትን፥ በአጭር ቃል የመንፈስ ፍሬዎችን ገንዘብ ያደረጉ ልጆችን ማሳደግ ነው (ገላ.5፡22-24)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት፥ ልጆቻችን የገዛ ክብራቸውን እንዲያውቁና በዚያ መሠረት እንዲያድጉ - ይኸውም የእግዚአብሔር ልጆች፣ ክርስቶስን የሚመስሉ፣ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ቅዱሳን እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው (ዘፍ.1፡26)፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት ልጆቻችን የእኛ ንብረት እንዲኾኑ ሳይኾን የእግዚአብሔር ልጆች እንዲኾኑ አድርጎ ማሳደግ ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እስራኤላውያንን ለክርስቶስ ያዘጋጃቸው እንደ ነበረ፥ እኛም በዚያ መንገድ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጆቸ እንዲኾኑ ማዘጋጀት ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ የሕፃናት አስተዳደግ ማለት የልጆቻችንን መጥፎ ጠባይ ከማራቅና እንዲታዘዙን ከማድረግ በላይ፥ እግዚአብሔርን በፍጹም ኃይላቸው እንዲወድዱ ማድረግ ነው፡፡ ቅዱሳንን እንዲያፈቅሩ፣ በቃል ኪዳናቸው ታምነው እነርሱን እንዲመስሉ ማድረግ ነው፡፡

#ትንሿ_ቤተ_ክርስቲያን፣ ገጽ 507-508
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
561 views21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:48:18 ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
475 views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 18:07:44 ሰው ሁን!

✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #ዶክተር (ሐኪም) አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #መሐንዲስ አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #መምህር አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #ፖለቲከኛ አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #ጋዜጠኛ አትሁን፡፡
✿ ሰው ከመሆንህ በፊት #መሪ፣ #መካሪ፣ #አውሪ፣ #ዘማሪ፣ #ጸሐፊ፣ #ለጣፊ፣ #ሰባኪ፣ #ሹመኛ፣ #ወገኛ.... ሌላም አትሁን፡፡

ዓለም፣ ኢትዮጵያ፣ ቤተ ክርስቲያንም ያጣችው ይህንን ሁሉ አይደለም፡፡ ሰው የሚሆንላትን እንጂ፡፡ ይልቁንስ ከሁሉ በፊት ሰው ሁን፡፡ ሰው መሆን ከእነዚህ ሁሉ የተሻለ ማንነት ነውና፡፡

"ሰብአዊነት የጎደለው ሙያ በመርዝ ዕቃ ላይ እንደተቀመጠ ጣፋጭ ምግብ ነው" ይላሉ አበው፡፡ የችግሮቻችን ሁሉ መነሻም ሰብአዊነት የጎደለው ግብራችን ነው፡፡

መጽሐፍስ ምን አለ? "ሰው ሁን፡፡" (1ነገ. 2፡3)

✿ሰው ለመሆን ያብቃን፡፡

(#ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
571 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ