Get Mystery Box with random crypto!

'ድንግል ሆይ አትፍሪ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና...እነሆ ትፀንሻለሽ፣ወንድ ልጅ | ✞ትንሽ ዝምታ ✞

"ድንግል ሆይ አትፍሪ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና...እነሆ ትፀንሻለሽ፣ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ...ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ።"

" እንደ ቃልህ ይሁንልኝ።"

ምን አይነት ንፅህናና ክብር፣ቃላት ከሚፅፍአቸው በላይ የሆነውን የድንግል ማርያም ትህትና መናገር የሚቻለው ማን ነው??

.. ድንግል ማርያም ልጇን ኢየሱስን ከመውለዷ በላይ ድንቅ ተአምር ምን አደረገች ቢሉ.... ከመልአኩ ብስራት .... ለተገኘው ቃል ... #በትልቅ_ልቦና_ትልቅ_ዝምታ በእርሷ ዘንድ ውስጥ ፀንቶ መቆየቱን ከተአምራት በላይ ተአምር ነው።

ይህን ብስራት ለተበሰረላት፣ሌላ ሴት ብትሆንስ?? ይህን ቃል ከልቦናዋና በማህፀኗ ትሸከም ይሆን??

በልቧ ትጠብቀው የነበረው ማህደር እውነት መሆኑን ስትሰማ...በታላቅ ዝምታ በልቧ መያዟን ሳስብ በራሱ እውነት ንፁህ ሴት ናት ብዬ ቃል ላጠረኝ ድንግል ሁሌም ክብርና ምስጋና ለእሷ እሰጣለሁኝ።

ድንግል ሆይ..ንፅህት ሆይ....በማህፀንሽ ከነበረው እሳት የበለጠ....የመልአኩን ብስራት ስትሰሚ የዝምታሽ ነበልባል...እንዴት ቻልሽው??አምላክ በውስጤ አለ፣ለማለት የሚያበቃ ቃል ከአንደበትሽ እንዴት ያዝሽው??

ክብርና ምስጋና ከተወደደው ልጅሽ ጋር!!

Surafel
T