Get Mystery Box with random crypto!

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ halal_fonqaa — ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ ʜ
የቴሌግራም ቻናል አርማ halal_fonqaa — ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ
የሰርጥ አድራሻ: @halal_fonqaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.56K
የሰርጥ መግለጫ

የአላህ እዝናት ሠላም ፍቅር አንድነት በሁላችሁም ለይ ይወራድ !!
ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን
ይህ Channel የናንተ Channel ነው!! ስለ ዲነቻን የምናውቅበት ቤታችን ነው።
🌺 የነቢያት ታሪክ 🌺
🌺አስገራሚ መልዕክቶች🌺
🌺ጣፋጭ እውነተኛ ታሪኮች🌺
ኢስሊምነን 💓 የመሰለ ምን አለ!
🚩 አስተማሪ እና አዝናኝ ገጠመኝ እዚ ይገኛል።
💌 @Damme_man

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-07 08:28:07
886 views♡—Ⓛ——ⓐ——ⓜ——ⓡ——ⓔ—♡, 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:50:28 #አፍላ ፍቅር

ፀሃፊ ካሊድ(kalido ye umi)

Part ➊

ካኪ.. ካኪ.. መስገጃ አንድ አንድ ብር እ ካኪ. ነው
አቦ አታዝገኝ ባክህ
ሶፊ.... ብዬ ንግግሬን ሳልጨርስ

ዛሬ እንዴት አባትህ ልትሸጥ ነው ዝናቡም አላቆመ። አለችኝ በቀኝ እጇ የያዘችውን የቡና መቁያ ከብረትምጣዱ ላይ የተዘሩትን በከፊል ወደ ቀይነት እንደመለወጥ ያሉትን ቡናዎች ወደ ቀኝ ወደ ግራ ወደ ፊት መልሳ ወደኋላ እየሳበቻቸው በጭሱ ሳይቀር ቤቱን እያናወጠችው ያለችው ከልቤ የምወዳት እናቴ፡ ቤቱን በሚያውድ የእጣን መአዛ ማፈኑንም አልዘነጋች።

በግራ እጇ አባዬ በፍጥነት ቡናውን ጠጥቶ ለተርሃዊ ወደ መስጂድ እንዲወጣ በማሰብ የካርቶን ብጣሽ በእጇ አኑራ በደከመ ጉልበቷ እሳቱን ማራገብም ይዛለች

ታላቋ እህቴ "ሶፊ" ግን ዛሬ ያለወትሮዋ አንገቷን ወደ መሬት አቀርቅራለች አባዬ ከጀርባው የተንጋለለውን ወፍራም ትራስ ተደግፎ በእጁ በያዛት ተስቢህ አላህን ያወሳል

የእህቴ "ሶፊ" ዝምታ ግን ያልተለመደ ስለሆነብኝ

ሶፊሻዬ ብዬ ጀርባዋን ብዛት ባላቸው ለመስገጃነት በሚያገለግሉት ካኪዎች መታ አደረኳት። ለትንኮሳዬ ምላሽ ይሆናል ብዬ ያሰብኩት እንደሁሌውም በእቅፏ ውስጥ ገብቼ ምንጣፉ ላይ በሳቅ እያንፈራፈረችኝ ትላፋኛለች የሚል ቢሆንም የጠበኩት ሳይሆን ቀርቶ በምትኩ አንዳች ጥፊ አናወጠኝ

የጥፊው ከነጎድጎድ የማይተናነስ ድምፅ ከገባሁበት የትዝታ መርከብ ያለ አንዳች እርጋታ አወጣኝ ከትውስታው እንደመባነን እያልኩ፡

ሶፊ... ሶፊ.. ከዛ ምሽት ጀምሮ የት ገባች?
ስል እራሴን ጠየኩ እነሆ የዘንድሮው እረመዳን እሷን ካየሁ ድፍን አስር አመት ሞላ። ኡፍ...... ስል ግርምታ በተሞላበት ሁኔታ በረዥሙ ከተነፈስኩ በኋላ
ሶፊ.. አልኩ በሰመመንና በሲቃ በታጀበ ድምፅ አይኖቼን በአንድ አቅጣጫ ላይ ተክዬ።
ለክፋቱ ከአፌ የወጣቸው ቃል ወደ እማዬ ጆሮ ሰተት ብላ ገባች

ምን አልክ?
እማዬ ነበረች ጠያቂዋ፡
ለምን እንደሆነ ግልጽ ብለው ነገራቶች ባይታዩኝም በሶፊ ዙሪያ አንዳች ነገር በእማዬና በአባዬ በኩል ሚስጥር ሆኖ እንዳልቀረ ይሰማኛል፡ ብዙውን ጊዜ ከአባዬ በተለየ መልኩ ስለእህቴ ሶፊ መሰወር ምክንያት ጥያቄ ቢጤ ሳነሳ እማዬን ማንገሽገሹ አይቀሬ ነው።
እኔም እማዬ ትጓዳለች በሚል ነገሩን በቸልታ አልፎ ሶፊን ለመርሳት ከመሞከር ይልቅ ጥያቄዬን በውስጤ እያብላላሁና እያመላለስኩ መቆየቱን አማራጫ ሳላረግ የቀረው አይመስለኝም።

ለአሆኗ ከእማዬ ለመጣችው ጥያቄ ዝምታን መረጥኩ፡ እማዬም ነገሩ ሳይገባት ቀርቶ አይደለም ጥያቄ ያነሳቸው ብቻ የተፈዘረውን ዝምታ ተንተርሳ ከባድ በሆነ ግልምጫ ከእግሬ እሰከ ፀጉሬ ጫፍ ከተመለከተችኝ በኋላ የሳሎኑን በር ከፍታ ወደ ውጭ ወጣች።

በዚህች አስርት አመታት ውስጥ የአባቴ መሞት፣ በፊት የነበርንበት መኖሪያችን በልማት ምክንያት ፈርሶ ተቀያሪ የጋራ መኖሪያ ቤት ከከተማ ውጭ ማግኘታችን
ከሶፊ መሰወር በኋላ በህይወታችን አዲስ ከተከሰቱ ነገራቶች ውስጥ ዋንኛዎቹ ናቸው ፡

ግን በእነዚህ ጥቂት ለማለት በሚከብዱ አመታት ውስጥ ወደ ቀድሞ ሰፈራችን ሶፊ እኛን ፍለጋ መታ ቢሆንስ? ስል አሁንም ዞሬ ለእራሴ ጥያቄን ፈጠርኩ፡ብቻ ውጥንቅጡ የወጣ መላቅጡን ያጣ ለመፍታት አስቸጋሪ የሆነ የተጠላለፈ ነገር አለ።

hanann
አቡኪ "አትገባም"?

ከጎኔ ያስቀመጥኳትን ስልክ አንስቼ የተቀበለችውን መልህክት አየሁኝ
ሀናን ናት

ሀናን በቅርቡ.....

Part 2 ይቀጥላል ....

ሶፊ ማናትስ የትናትስ?????
1.1K views♡—ⓐ——ⓕ——ⓡ——ⓐ——ⓓ—♡, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:20:21 የነገውን የሀሙስ ፃም እንዳያመልጠን እንፁመው። ብዙ መልካም ነገሮችን አቅፎ የያዘ ነው።

①) ነብዩ ሲፃሙት የነበረ የውዱ ነብያችን ሱና ነው
②) ስራዎች ወደ አላህ የሚወጣበት ቀንም ጭምር ነውና ስራችን ፃመኛ ሆነን አላህ ዘንድ እንዲቀርብልን የሚያደርግ ነው።
③) ይህ ቀን ደግሞ እጅግ ውድ በሆኑት የዙልሂጃ አስር ቀናቶች ውስጥ መገኘቱ ሌላው መለያ ነው።
④) በዙልሂጃ የሚፃም ሱና ፃም ከሌላ ጊዜ ከሚፃመው የበለጠና የላቀ አጅር ስለሚያስገኝ
⑤) ከነገ ወዳ እለተ ጅሙአ የአረፋ ፃም ነው። ነብያችን ጅሙአን ብቻ ነጥሎ መፃምን ከልክለዋል። ጅሙአን መነጠልን ሳይሆን አረፋ ፃም በጅሙአ ቀን ስለተከሰተ መፃሙ የሚቻል ቢሆንም አንዳንድ ኡለማዎች ለጥንቃቄ ሀሙስንም ብንጨምር ብለዋልና ይህም ሌላ መለያ ነው።

https://t.me/+TP5jske0s3YUPUXE
@Halal_Fonqaa

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

♡————————♡
ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ ♡ ♡ ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ
1.1K views♡—ⓐ——ⓕ——ⓡ——ⓐ——ⓓ—♡, 18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 22:03:08 እማ
ቃላት ቢደረደር በብዙ ጋጋታ
መቸ ይገልፀዋል የናትን ዉለታ
የናትን ዉለታ እንዴት ችየ ላዉራዉ
የሁሉም ተምሳሌት መሆኖን አቃለሁ
ሀዘኖን አርቀህ ደስታዋን አብዛላት ብየ እየተማፀንኩ
ከዛ ከጭንቁ ቀን ከዉልደቷ ጀመርኩ
ስትወልድ ያለዉ ስቃይ እንዴት ይገለፃል
ከሀሊቁ በቀር ማንስ ያቅላታል
ያየችዉስ ስቃይ በምንስ ይተካል
ከወለደች በላይ ጭንቀቱ ይብሳል
ከመዉለዷ በፊት ካለዉም ይለያል
እሷ ሳትበላ ልጇን ታበላለች
አልበላም ሲላትም በጣም ታስባለች
ለምን ይሆን ብላ ከባዱን ታዝናለች
ከታመመ ደግሞ እንቅልፏን ታጣለች
በሀሳብ ተጠምዳ ብትሰለሰላለች
እስከሚያድጉ ድረስ በጭንቀት ታያለች

እሰይ አደጉልኝ ነፍስም አወቁልኝ
ስራ ስለያዙ ሀሳቤን አረፍኩኝ
ብላ ሳትጨርስ ምነዉ አመሸብኝ
ምን ነክቶብኝ ይሆን ልጀ የቀረብኝ..
.
.
ከመዉለዷ በፊት የጀመረ ስቃይ
ማብቂያዉ ቢሆን እንጂ እዱንያን ስትለይ
ሌላም ማብቂያ የለዉ
አላህ ያሳምረዉ
ደርቦ ደራርቦ ጀዘዋን ይክፈለዉ!

#ላይክ_ይደረግ
#ከወደዱት_ደግሞ_ለሚወዱት_ያጋሩ


https://t.me/+TP5jske0s3YUPUXE
@Halal_Fonqaa

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

♡————————♡
ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ ♡ ♡ ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ
1.4K views♡—ⓐ——ⓕ——ⓡ——ⓐ——ⓓ—♡, edited  19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:18:16
ሁቢዎቼ ኢስላማዊ አዳብ የተወዛ የፍቅር እግጅ መሰጭ ትምህርት ሰጭ ቢሆን እስ??
Anonymous Poll
94%
6%
98 voters1.3K views♡—ⓐ——ⓕ——ⓡ——ⓐ——ⓓ—♡, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:25:32 •• መጨከን አቃተኝ ••

.
ፍቅሯ አሳመመኝ ልክ እንደ በሽታ
እየዋለ ሲያድር በኔ ላይ በረታ፤
የልቤን መጨነቅ የሚሰማኝ ኣጣው
እሷን በመውደዴ እኔ ተንገላታው፤
መከራ ስቃዬን በውስጤ አምቄ
ብቻዬን ሜዳ ላይ ቀረውኝ ወድቄ።

ስለሷ ላላስብ ብሞክር ብሞክር
ውስጤን ላሳምነው እራሴን ባማክር
ብለፋ ብጥርም አልሆንልህ አለኝ
እሷን አለማሰብ ሞቴ መስሎ ታየኝ፤
ስሜቴን ቀርቤ ውስጤን እንዳልነግራት
የውነቴን እንደሆን እሷን የወደድኳት
መጨቅጨቅ መሰለኝ ሰጋው እንዳላጣት
ፊቷን እንዳትነሳኝ ላዓይን አኳ አንዳላያት…
አርፌ መቀመጥ እየቻልኩ እርቂያት
ይበልጥ እንዳትሸሸኝ ማናገር ፈራዋት።

እርግት ያለች ነች እጅግ የምታምር
የፊቷ ፈገግታ ቀልብን የሚሰውር፤
እንደፅጌሬዳ የሚያምረው ከንፈሯ
ጥርት ያለው ዓይኗ ልክ እንደምንጭ ውሃ
በተለይ ፀጉሯን ስትለቀው ወደታች
ውበቷን አጉልቶት ጭራሽ ታፈዛለች።

መላ ቁመናዋ በጥበብ ታንፆ
ተዘርዝሮ እንዳያልቅ በቃላት ተገልፆ!!
ስለውበቷ መዓት ሁልጊዜ እያለምኩ
ሲመሽም ሲነጋም ስለሷ እያሰብኩ
ለካስ ቆይቻለው ካባከነኝ ፍቅሯ
ልቤ ውስጥ ጠልቆ ነፍሱን ከዘራ፤
እንዳልተዋት ነገር መጨከን አቃተኝ
ካለችበት አርገጥ ሂድ አያት አያለኝ
ስለሷ ሳላልም መዋል የሚያቅተኝ
ለካስ የሷ ፍቅር እያደር እየዋል
ቀስ በቀስ አድክሞ አሸንፎኝ ኖሯል።

ጤነኛ መስላለው ባካል ለሚያየኝ ሰው
የውስጤን በሽታ እኔ ነኝ የማውቀው፤
ድንገት የሚጨንቀኝ ሆዴን የሚብሰኝ
ከሰው ጋር መጫወት መሄድ የሚያስጠላኝ
ፍቅሯ ውስጤ ሰርፆ ግራ መጋባቴን
ስለሷ እያሰብኩ እራሴን ማጣቴን
አልገባትም መሰል በሷ መጨነቄ
ምን አንዳስጨከናት አኔ ምን አውቄ።

ልረሳት ሞከርኩኝ ከልቤ ላወጣት
ስለሷ ላላስብ ዳግመኛ ላላያት፤
ለካስ አትረሳም ከልብም አቶጣ
ብፈልግ ባስፈልግ ለሷ እንከን ታጣ፤
ልጠላትም ሞከርኩ መጥፎዋን ፈልጌ
ከርስቷ ላባራት ከልቤ ዳር ግርጌ፤
በምን አሳብቤ እንደምንስ ልጥላት!?
እንዲው በደፈናው ያለምንም ምክንያት፤
የማትጠላ አርጎ ፈጣሪ ፈጥሯት
በሷ የሚጨክን አጣውኝ ጉልበት።

ሳላያት ሰንብቼ ባዓይኔ ብትሄድም
ለብቻዬን ፍቅሯን አስታቅፋኝ ብትቀርም፤
ስቃዬ ቢጠና ከልቤ አፍቅርያት
እድሌ ጠሞብኝ ሳላገኝም ባጣት፤
የሚወዳት ልቤ ቅስሙ ቢሰባበር
እንደናፈቀችኝ ሳላገኛት ብትቀር፤
ቢመስላትም የቀልድ ፍቅሬን ባትረዳው
ክፉዋን አልስማ ጦሷን ለኔ ያርገው።
እውነተኛው ፍቅሬ መስሎም ባይታያት፣
እኔ ከልቤ ነው እሷን የወደድኳት ።


https://t.me/+TP5jske0s3YUPUXE
@Halal_Fonqaa

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

♡————————♡
ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ ♡ ♡ ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ
1.4K views♡—ⓐ——ⓕ——ⓡ——ⓐ——ⓓ—♡, edited  14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:03:32 ➥ፍቅር የራሱ የሆነ ውበትና ዜማ አለው
ያፈቀረ እንጂ ማንም የማይሰማውღ
............. ..............

⇘ፍቅር እንደ ጦርነት ነው፤ ለመጀመር
ቀላል ነው፤ ግን ለመጨረስ በጣም
አስቸጋሪ ነው።

❝ዓይኖቼን ጨፍኜ አንቺን አስባለሁ፤
ዓይኖቼን ገልጨ አንቺን አስባለሁ፤
አንቺም እያሰብሽኝ እንደሆነ
ማወቅ እፈልጋለሁ።❞

➦አምነህ ልብህን ለሰጠኸው ከዛም
በከዳህ ሰው ላይ ፈፅሞ እንዳታዝን፤
ምክንያቱም ሰውየው አንተን ሳይሆን
እራሱን ነውና የከዳው፡:

⇘ፍቅር ምን እንደሆነ ስታውቅ ነው
ለዋጋው መስዋዕት የምትከፍለው።


https://t.me/+TP5jske0s3YUPUXE
@Halal_Fonqaa

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

♡————————♡
ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ ♡ ♡ ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ
1.2K views♡—ⓐ——ⓕ——ⓡ——ⓐ——ⓓ—♡, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:46:58
#ኢስላማዊ_ጥቅሶች


https://t.me/+TP5jske0s3YUPUXE
@Halal_Fonqaa

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

♡————————♡
ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ ♡ ♡ ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ
1.2K views♡—Ⓛ——ⓐ——ⓜ——ⓡ——ⓔ—♡, 07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:46:55
#ኢስላማዊ_ጥቅሶች


https://t.me/+TP5jske0s3YUPUXE
@Halal_Fonqaa

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

♡————————♡
ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ ♡ ♡ ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ
1.1K views♡—Ⓛ——ⓐ——ⓜ——ⓡ——ⓔ—♡, 07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:46:21
#ኢስላማዊ_ጥቅሶች


https://t.me/+TP5jske0s3YUPUXE
@Halal_Fonqaa

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

♡————————♡
ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ ♡ ♡ ⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡⅡ
1.0K views♡—Ⓛ——ⓐ——ⓜ——ⓡ——ⓔ—♡, 07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ