Get Mystery Box with random crypto!

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ hakika1 — አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ hakika1 — አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የሰርጥ አድራሻ: @hakika1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.15K
የሰርጥ መግለጫ

የሰው ልጅ ልብ ነው የገጣሚ ሀገር...!
@Run_Viva_Run

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-20 12:55:28
የክፍ ክፍ ጉዞ
""""""""""""""""
እያደር ከጠላኝ
አንጓጦ እየናቀ ቀረብኩ ያልኩት ጓዴ፤
ይሁና ልበለው
እስቲ ልተዛዘብ ካልሰመረው ገዴ!

በእጅብ ተሰብስበው
"ሂድ ከዚህ" እያሉ ቢተፉብኝ ምራቅ፤
ግድ የለም
ግድ የለም
እስቲ ከፊታቸው ከገፃቸው ልራቅ...

ልሂድ...

ብደምቅ ካላማርኩኝ
"ክ.ፍ" የሚለኝ በዝቶ፤
ባጌጥ ባልሸበርቅ
ባልል ሽቶ...ሽቶ...

ስስቅ ሰው ካስቀየምኩ
ሳለቅስ ሰው ከጠላኝ፤
ስሄድ ካልተናፈኩ
መቆም ፊት ካስነሳኝ...
ነገሬ ካልጣመ
አ.ል.ገ.ጠ.ም ካለ ሁሉ ነገር ጠሞ፤
ይቻል እንጂ ልቤ
ማነው ያሸነፈ ከዕድል ትግል ገጥሞ..?

ልሂድ..

ቅሌን ጨርቄን ሳልል እግር ወደመራኝ፤
ከአድማስ ወድያ ማዶ ዕድሌ ቢቀናኝ...
እዚህ አፍቅሩኝ ብዬ
ከሰው ልክተት እያልኩ ከቶ አልልም ሙጭጭ፤
እግዜርም ሲጣላ
በሰው ነው ሚቀጣው መች ይቆርጣል ልምጭ...

ልሂድ....

ቆሜ ከማያቸው
ተቃጥሎ ሲሞቁት እኔነቴ ነዶ፤
ይክሰኝ ይሆናል
የእግሬ ንቃቃት ከተሻገርኩ ማዶ!

ልሂድ...

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳ ስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
817 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 20:53:03
መልካም በዓል!

@HAKiKA1
@HAKiKA1
738 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 19:50:40
እውነት
""""""""
ውሸት
""""""""
ጎልያድን ያክል...ግዙፍ ተራራ ሰው፤
ዳዊት በወንጭፉ በጠጠር ቢያቀምሰው፤
መሬት ተከንብሎ ውድቀት ነው የተረፈው...
.
.
.
ተመልከት
.
.
.
እየው ይህን ጠጠር እየው ይህን ወንጭፍ፤
ተመልከት ዳዊትን አንድ ነገር ጨልፍ...
እየው ጎልያድን
ወድቆ ሲከነበል በፈጣሪ በትር፤
ልብ በል በሀሳብ አንድ ነገር መትር...
.
.
.
ተመልከት
.
.
.
ከዓለት የደደረ የውሸት ተራራ፤
በሀቂቃ ወንጭፍ እውነት ተወርውራ...
ኢምንቷን ከነካች
የሀሰቶችን ካብ የውሸትን አጥር፤
ዓለቱ ገሀ ነው ይናዳል በስንጥር..!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1
960 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 09:11:46 ልኬት
"""""""
በመለካት ዓለም
በመጠርጠር ቀለም
ውሃን ስትመረምር ሰምጠህ እንዳትቀልጥ፤
ጥልቀትን ስትለካ
በትርህን አንሳ በል ዘንግህን ቁረጥ!

ሰውንም እንደዛው

ከልቦናው ባህር
እየተንደፋደፍክ መሃል እንዳትገኝ፤
በትንሹ ቀርበህ
ከመሀል ለመቅዘፍ የዳር ዳሩን ተቀኝ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)


@HAKiKA1
2.4K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:32:02
ንቃት
"""""
የልብ መቅረዝ በርቶ
ነፍስ ሲኖር ለእምነት ቃል፤
በሺ እንቅልፍ መሀል
ልቡ ተቀስቅሶ አንድ ሰው ይነቃል!

ይነቃል...
ከሰመመን ሀሳብ እራሱን ያርቃል፤
የእውነት አታሞ ለዓለም ይደልቃል፤
ይነቃል...
ተስፋን ያ..ሰንቃል...!

ለአብነት

"ተመልከተው ኖህን"
የፈጣሪን ቁጣ ነቅቶ ቢጠረጥር፤
በኃጢያት ህላዌ
ዓለም ሲደነቁር፤
ጎንበስ ቀና ብሎ
መርከብ ሲቆረቁር...
ባበጃጀው መርከብ
ፍጥረትን ሲያሻግር
ወደመኖር ዓለም ጥፋትን ቀልብሶ፤
ግድ የለህም እመን
ንቃት ነው ምድርን ያቆማት መልሶ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
2.7K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 10:41:08 ያ ደሀ ያ የሀብታም ቤቱ ዘበኛ
ሲጠብቅ ቀንና ሌት እማይተኛ
ላስተዋለ ልብ ላለ ላወቀው
ያንን የሀብታም ቤት ሳይሆን ቃሉን ነው የጠበቀው።
.
.
.
@HAKiKA1
2.2K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 10:40:40
ሮፍናን ይለያል

ምርጥ ሀሳብን በሙዚቃ ይዞልን ቀርቧል።

"ቃል ነበር" የሚለው አንድ track ብቻ ትልቅ ሀሳብን ያሸክማል...
አድምጡት

@HAKiKA1
2.0K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:46:58
Lady Gaga - Venus Haejun Choreography

Join us


@Natanimaye
57 viewsMåki Mårli, 19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:21:33 100% አምኜበት እንድትቀላቀሉ የምጋብዛችሁ ምርጥ የግጥም ቻናል....ከታች ባለው ሊንክ join በማለት ወደ ስነ ፅሁፍ መንደሩ ይዝለቁ።

@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
119 views#Wërkñè @viva, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:01:15
አንዳንዴ በህይወት ጎዳና ቆመህ እራስህን ከመሞት አንግልም ተመልከተው.....ያኔ የዓለምን ፊትና ጀርባ ትመለከታለህ፤የነፍስህን ጓዳ ጎድጓዳ ትቃኘዋለህ።
አስብ!
አይጨልምብህም ፀሀይን በእጅህ ትታቀፋታለህ።

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
299 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ