Get Mystery Box with random crypto!

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ hakika1 — አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ hakika1 — አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የሰርጥ አድራሻ: @hakika1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.15K
የሰርጥ መግለጫ

የሰው ልጅ ልብ ነው የገጣሚ ሀገር...!
@Run_Viva_Run

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-22 06:32:04 TEDDY AFRO - ናዕት

የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባው ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት

እያመመው መጣ

@HAKiKA1
@HAKiKA1
697 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 08:48:55
ጥንድ ስሜት
""""""""""""""""
በትከሻዬ ዋልሽ
እንደ ለበስኩት ኮት፤
ዙሪያዬን አጀብሽኝ
ልክ እንደ መለኮት...
እልፍ ጀንበር አየሁ፥
ሰማያትን ቃኘሁ...
ነፍሴን ሞላት ሀሴት፥
ባደርግሽ የኔ ሴት...
ጨረቃንም ጨበጥኩ፥
ብዙ ኮከብ ቆጠርኩ...
ምድሬ አረገደች፥
ዙሪያዬ ተዋበች...
ሸብ እረቤ በዛ፥
ልቤ ልብ ገዛ...

እህህ...አሃሃ

ሸብ እረብ...

ሸብ እረብ...

ሸብ አረብ...

ከዛ

እረብ...

እረብ...

ሰከርኩኝ በፌሽታ፥
ወደኩኝ በደስታ፥
ህመሜ በረታ፥ጥፋት ሆነ ሲቃ፤
በጥንድ ስሜት ቆመን
ማፍቀርሽ ሲነኩት መውደዴ ሲያበቃ...
.
አይ እኔ
.
እኔ ሞኝ
እኔ ጅል
በይሆናል ምኞት
ሽቅብ ሽቅብ ሳስብ እኔነቴን ልኩል፤
ረብ አጣ እምነቴ ተበተንኩኝ ቁልቁል...

እኔ ሞኝ
እኔ ጅል
ሀሳብ ሳንጀላጅል
መንገድ ስገሰግስ ከአንገት አቀርቅሬ፤
በህይወት ፈረቃ ሆኜ ብስል ጥሬ፤
ዛሬ ሳቅ አሳቀኝ እንባዬን አቅርሬ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
1.0K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 23:33:38
ነፍስ ይማር

አቅም ያላቸው ብዙ መስራት የሚችሉ ድንገት በድንገት ሲለዩን ልብ ይሰብራል።

ዳዊት ነጋ(ወዛመይ)

@HAKiKA1
1.2K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:21:52
ኢ-ምኞት
"""""""""""
የሰው ልጅ ሲከፋው
ህልፈቱን ይመኛል፤
ኖሮ ያልተገኘ
ሞቶስ መች ይገኛል?

@HAKiKA1
1.1K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 14:21:32
"እሺ ከዚያስ ወዲያ?"
አለ ዘፋኝ
#ከዚያማ....
"""""""""""""""""""""""
ስንቆምም ተጎዳን
ስንሄድም ተጎዳን፤
ወጥቀነው ባዶ
ለባብሰንም እርቃን፤
እየጠጣን ጥማት
በልተንም ገረጣን፤
በቃል እምነት ፀንተን
እውነት አልተጠጋን፤
ላይሞላልን ለፋን
በሽንቁር ወንፊት ጋን!

እኛማ

ላናቆመው ዋጀን፥
ቀን እንደ እሳት ፈጀን...
በአንቺና በእኔነት፥
አልገፋም አብሮነት፥
አልጠመረም ጥምረት...

አልገጠመልንም
አልበጃጀልንም
ፍቅርና ደስታ አልሰመሩልንም
እስቲ ተራርቀን እንየው ሁሉንም...

#ከዚያ?....

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
1.1K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:32:55
የምስራች ኑሮ
""""""""""""""""""
ከሀሩር ከቁሩ፥
ለገላችን ጥሩ...
ለዓይናችን ቀና፥
መልካም መልካም ዜና፥ብስራት ሳናበስር፤
የምስራች ሲባል
ምስር ብሉ እንዳንል፥ተወደደ ምስር
.
እናም
.
ምስራች ባይኖርም
የምስራች ስልሽ
ምስር ብላ ብትይ፥አይችለውም ኪሴ፤
አፈር ብላ በይኝ
ጉድ ከምትጎትት
አፈር ይሻላታል፥መከረኛ ነፍሴ...
.
አዎ
.
የምስራች ስልሽ
አፈር ብላ በይኝ
እሱ ነው ቀሊሉ ለኑሮ ያልከበደው፤
ያልኩሽን ብለሽኝ
በይ መርቂኝና ሞቴን ልሰንደው፤
በሞት ነው እዚህ ሀገር
የኑሮ ብልሃት ዘዴ 'ሚለመደው!

... የምስራች ...

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)


@HAKiKA1
@HAKiKA1
1.0K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 14:52:36
ህይወት ያለብልሃት አያልቅም
""""""""""""""""""""""""""

እግሯን ወንጨፍ ወንጨፍ፥
እግሩን ሰንዘር ሰንዘር፥
ቀልብያቸው ብርር፥
ልቦናቸው ዘርዘር...

እጅጌውን ሰብሰብ፥
ቀሚሷን ከፍ ከፍ፥
እሮጠ እንደንፋስ፥
ከነፈች እንደነፍስ...

እልም ብንን አሉ
ሽው ሽው ፍንጥቅ፤
እኔን የገረመኝ
የዓላማቸው እብቅ፤
የእምነታቸው ልክ
የተስፋቸው ስንጥቅ...

ምንድነው?
.
.
ምንድነው?

ያሽቀዳደማቸው
ያስፈተለካቸው
ያስደነበራቸው የድብቅ ስር ጉዱ፤
ቢገባቸው ኖሮ
ተሯሩጠው ሳይሆን
በዝግታ ነበር የሚያልቀው መንገዱ..!

እንዲህ ነው
.
.
አንዳንድ ግዜ መኖር
በመሮጥ ላይገኝ በድካም ያርሳል፤
በአርምሞ ጥርጊያ
ቀንቶት ለተጓዘ
ከህይወት ስኬት ጫፍ ድክ ድክ ያደርሳል!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1‌‌
1.2K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ