Get Mystery Box with random crypto!

አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ hakika1 — አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ hakika1 — አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
የሰርጥ አድራሻ: @hakika1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.15K
የሰርጥ መግለጫ

የሰው ልጅ ልብ ነው የገጣሚ ሀገር...!
@Run_Viva_Run

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-05 16:10:16 ርክም ራግ
""""""""""""""
አይገርምሽም እቴ
"ብልህ ሁን!" ብለውኝ የሚያስብ አርቆ፤
ሀሳቤ ሁሉ መጥቆ፤
አያያዜ ረቆ....!
ሄዶ ....
ሄዶ ....
ሄዶ ....
ቂላቂል ሆነና
ይህ አጉል ዕድሌ፥የተሰጠኝ ዕጣ፤
መልሶ አስታዘበኝ
የሩቁን ሳማትር፥የስር ስሩን ባጣ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)


@HAKiKA1
@HAKiKA1
325 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 08:29:24
እንኳንም ተመለስክ በላያ.....ሌላው ሌላ ነው!

@HAKiKA1
347 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 13:20:37
ጥበብ ስትነካህ
በረጅም ጣቶቿ ከበላይህ ግድም፤
ጠፍንጋ ስትይዝህ
በሀሳቧ ወሰን በ.ው.ድ.ም በግድም፤
ከሀገርህ በላይ
በሽውርር ልቦና ፖለቲካ አትወድም...

አዋ....

አፍ ብታሲዝ እንጂ
የጠመንጃ አፈሙዝ አፋችን ውስጥ ከታ፤
ብታሳስር እንጂ
በጫማ ተረከዝ ክንድን አስረግጣ፤
ፈቀቅ ለማታደርግ
ኑሮና አለምህን ቅንጣት ላታስለካ፤
አለችልኝ ብለህ
በዜግነት ክብር በሷ ላትመካ፤
ማሳፈን ነው እንጂ
ማስተንፈስ አታውቅም ይቺ ፖለቲካ..!

#ዝምአንልም
#FreeBelayBekeleWeya

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
714 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 12:56:00 አንቺን ለመርሳት
"""""""""""""""""""
ጥለሽኝ ከጠፋሽ
ከጠላሽኝ ኃላ ምን ያልሆንኩት አለ፤
ብዙ የለመደ
መከረኛ ልቤ ሰርክ አንቺን እያለ፤
ከነፍስያዬ ጥግ
ስቃይና ህመም እየጎነቆለ፤
ከእሸት እምነቴ
ረመጥ እሳትን እየፈለፈለ፤
እንቺ ከሄድሽ ኃላ ምን ያልሆነው አለ?

አንቺ ከሄድሽ ኃላ
ጥለሽኝ ከጠፋሽ ጊዜው ከነጎደ፤
መከረኛ ልቤ
እረሳሽ እያለ ብዙ ተላመደ፤
ሴቶችን ለመደ፥
ሲጋራን ወደደ፥
መጠጥን እያለ
ባሰኘሽው ሰዓት
ለትኩስ ስሜቱ ከጊዜ አረፈደ!

ግና አንቺ የለሽም
ሴቶቹን ብቀርብም እንዳንቺም አላገኝ፤
አልባብ እንሸት ብለው
ከደረት የነፉት ሽቶ ሰነፈጠኝ!
ኩላቸው አይደምቅም
ሊፒስቲክ ቢቀቡ ካንቺ በልጦ የነሱ፤
ጭራሽ ያስጠላሉ
አውሬ ያስንቃሉ መስለው ደም የላሱ፤
ያላንቺ ማን ሊገኝ ምድርን ቢያስሱ..

(ይገርምሻል ውዴ)

አሁን በቀደም ለት
ያስረሳኝ ይመስል እያጨስኩ ሲጋራ፤
አፌ በለሆሳስ
ስላንቺ ውዳሴ ከራሱ እያወራ!
ቁልቁል እየሄድኩኝ
ጭሱን ስተነፍስ የማጉ'ት ትምባሆ፤
ከሰተሽ ከፊቴ በጭስ አንቺን ስሎ!
ስትፍለቀለቂ፥
ስትፈነድቂ፥
ከኔ ስትቦርቂ!
ጣልኳት ሲጋራዬን በእግሬም እረገጥኳት፤
መች በሱስ አጥምዳኝ ያጨስኩት ለመርሳት!

(ይገርምሻል ውዴ)

አሁን በቀደም ለት
ዘው ብዬ ገባሁ ከገዳም ነሽ ጠላ፤
አንቅሬ ልተፋሽ
መለኪያ ጨብጬ ልጋት ካቲካላ!
መቼም እሳት አይደል
አረቄ አወጣጧ ሙያ የገዳምነሽ፤
ከራሴ እርቄ
በሁለት መለኪያ ከወኔዬ ስሸሽ!
ልቤን እየሞቃት
ነፍሴን እየሳትኩኝ አይኔ እየሰከረ
የአንድ ያንቺ ሲገርመኝ
አስር አንቺን አርጎ ያሳየኝ ጀመረ!
ወጣሁ ስደናበር
ብዙ ብትሆኚብኝ ከግድግዳው ሳፈጥ፤
የፍቅር አኩኩሉ
ካንቺ ተደብቆ ወዴትስ ሊመለጥ?

መች ሊያስጥለኝ ውዴ

መች ሊያስጥለኝ ውዴ
ድካም እንጂ ትርፉ ለሌላ መ.ጋ.በ.ዝ፤
ፍቅር ከገነነ
መች ይስጥላል ሌላ? መች ያስጥላል ግዑዝ?

አይሸሽግም ግዑዝ
ለነፍሴ ተልኮ የፍቅርሽ ጦስ እቴ
እጠብቀዋለሁ
ከልቤ እስኪያወጣሽ ዋሴ ሆኖ ሞቴ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
700 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 12:55:36
533 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 21:38:28
የክብ.....ካብ
"""""""''''''''''''''""
እንጀራችን ክቡ፥
ዕድላችን ክቡ፥
መንገዳችን ክቡ...
በመከበብ ዕጣ፥ዕድል ተለውሶ፤
ከቶ አይደርስም ያሉት
እየተቃበዘ ይመጣል መልሶ...

በል ስራህን መርምር
አላማህን መትር እጆችህን አጥና፤
አርምጃህ ሀቅ ይሁን
ከሰው ጫንቃ ውረድ ውልህ ይሁን ቀና...

ዕቅድህን እየው...

ዕቅድህን እየው
አይምሮህን ቃኘው
በማጥ አትዳክር ህልም አለምህ ጠቦ፤
ህይወት አዙሪት ነው
የግፍ እንባ እንደ እባብ ይመጣል ተስቦ...

ተው
ተው እስቲ እረፍ
ነፍስያህን በእውነት ግረፍ

አትድንም
አትተርፍም
ከህዝብ ዕንባ ከሰው ደም ጦስ፤
ቢታጠብስ መቼ ፀዳ
ከኢየሱስ ደም ያ ጲላጦስ?

አፅዳ...
ፈትግ....
አንፃ ሀሳብህ ህሊናህን ቃኘው፤
ባሰብከው ልክ ነው
የሰማይ ቤት ዕዳህ ፍርድህ የሚዳኘው....

አስብ አለምህን
አስብ ህይወትህን
አስብ እምነትህን
አስብ...
አስብ...
አስብ...
ከመኖርህ ጉድጓድ መልካምነት ሰብስብ...!
ሸፍን ገመናህን
ህሊናህን ገንባ በፍቅር ምሰሶ፤
የክብ ነው ነፍስህ
የሰራኸው ሁሉ ይደርሳል መልሶ!

#አስብ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
1.6K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 18:08:41
@HAKiKA1
616 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 14:12:44
#በቃ
#የዜግነት_ክብር
#ቀይ_አሻራ

share
ለወገኖቻችን ድምፅ እንሁን!

@HAKiKA1
799 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 08:17:21 (እኛ)

ለካብነው ፍቅራችን
አመል እያከፋን፤
ለቆለልነው እምነት
እልህ እያጋፋን፤
ለልብ ኪዳናችን
በጣም ተንቦራቆ
እውነት እየሰፋን፤
እንኳን መፈቃቀር
መጣላቱም ጠፋን!


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
815 viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), 05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 15:59:56
ሽውርር ተስፋ
"""""""""""""""""
ያለፈው ክፋት ነው
የሚመጣው እንጃ፤
ዛሬን መዳከር ነው
የሀገሬው ፍርጃ...

ትላንትም ግፍ ነበር
የህይወት ልቅምቅም፤
ከገር ፊታችን ላይ
እንባን የሚያስለቅም...

ይመሻል?..... አናውቅም
ይነጋል?.....አናውቅም፤
ተስፋችን ቢቀበር
አይገርምም አይደንቅም፤
አሁን ሰላም ካለ
ነገን አ'ናፍቅም...
.
እንግዲህ
.
ልቦናህን መርምር
እርምጃህ ቀስ በቀስ፤
ልቦናሽን እዪ
መንገድሽን ቀነስ፤
የቂም ሾተል ይዞ
"ነገን አንጋ" ብሎ
በፀሎት ጌታ ፊት የምን ማለቃቀስ?

አንቅረው ሴራህን
ሽልሽን አራግፊ ክፋት ይጨናገፍ፤
ይህንን አርጎ ነው
ለአዲስ ንጋት ጀንበር አጥብቆ መንሰፍሰፍ...
.
አልያማ
.
በሆድ ክፉ አርግዞ
የነገር ሽል ይዞ
ከነፍስና ስጋ ሳይጠፋ በቅጡ፤
ለፍቅርና ሰላም
በህልም ቅዠት አድረው
በተስፋ ዓለም ላይ ነገን ቢቋምጡ፤
የነገ ቀን ነግቶ
ማርያም ማርያም ቢባል የሰይጣን ነው ምጡ፤
ስህተት ነው ንጋቱ...!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
2.5K viewsአብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ), edited  12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ