Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና ጥቅሶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ gtem_na_tks — ግጥም እና ጥቅሶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ gtem_na_tks — ግጥም እና ጥቅሶች
የሰርጥ አድራሻ: @gtem_na_tks
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.87K
የሰርጥ መግለጫ

creator @henajs

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-11 21:34:59
አንዳንድ ጊዜ ልብ
ለዓይን የማይታዩትን ያያል

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
323 views £NƏ`"`"`"`"`"`, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 18:34:46 የሰማይ ቤት ግሮሰሪ
(አሱ እንደፃፈዉ)
.
.
"ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት!!!
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
..................................................
በር እንደከፈተች ፣ አብረው የሚወጡ
ከዋክብት ደሞ...
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋ ሚጠጡ!!!
*
በጣም የሰከረው...
ከሰማይ ፈጥፍጦ ፣ ራሱን ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ..
ማለት ነው የኛ እድል!!!
****
ተወርዋሪ ጠርሙስ ሊሆንም ይችላል!
ማን ያውቃል?

(( በላይ በቀለ ወያ ))

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
566 views £NƏ`"`"`"`"`"`, edited  15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 12:52:36
የራስ አለም ከንቱ

በራስ አለም ውስጥ ጠልቆ መዋኘት : ወዘ ቢሱን ህይወት ለመምራት ደፋ ቀና ያለች ህሊና ማሰብ ሲሰለቻት የምትወስነው ብቸኛ አማራጭ ነው!! አጠገብ ያለ ቁም ነገር ድምፅ ሲያሰማ በራስ አለም : ዙሪያ ገባውን ቀን ሳይል ለሊት ለመስረቅ የሚጣደፈው ኮቴ ሲያሰማ አሁንም በራስ አለም : ማስተዋል በራስ አለም ተቆጣጥራ ቸልታ ሲበዛ በራስ አለም

ይሄ የብቻ አለም ገላግሌ እየመሰለን በብዙ ተታለንበታል! ይሄ የራስ አለም ስታጠፋ አይቀጣህም ወይም አይመክርህም : ደስታህን ተደስተህ ባለምክንያቱን አታመሰግንበትም : አሁንም በራስህ አለም ሰምጠሀላ:: ከዚህ አለም እንድቶጣ ሀይለኛ ማዕበል አትጠብቅ ደስታህን ተደሰተው : መከራህን ተጋፈጠው : ከራስ አለም ውስጥ ያስቀመጥከውን የህሊናህን ጓዝ ጠቅልለህ ውጣ ተቀላቀለው ሁነታውን : ማዕበሉ ከሚያነቃህ በጊዜ ንቃበት : ያንተ አለም ከንቱ ለህይወትህ ማይቀርለት አለም ግን ዘላቂ:: የፈጠረህን ታመሰንግ ዘንድ ከንቱን ንቀህ ንቃ!!

@Tziom
@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
738 viewsZion, edited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 12:43:03 ባገሬ ሰማይ ስር
.
.
የሚሆነው ቀርቶ የማይሆነው ሆነ፣
ሰው ለራሱ ቀርቶ ለንዋይ ታመነ።
እልፍ አዕላፍ ጩኸት፣
እልፍ አዕላፍ ብሶት፣
ክፋት የወለደው የህሊና ዝቅጠት።
.
ባገሬ ሰማይ ስር
.
ተስፋን የቆረጠ የባከነ ወጣት፣
ስክነት የተለየው ዉል አልባ ማንነት፣
በአሉባልታ ወሬ ልቡ ተመርዞ፣
ማሞቅ የሚቀናው የነገር ጫፍ ይዞ፣
ስሜቱ የሚነዳው በሱሱ ደንዝዞ።
.
ባገሬ ሰማይ ስር
.
ሳቅን የናፈቁ የሚያነቡ እናቶች፣
የሚያቅፉት ያጡ ጨቅላ ህፃናቶች፣
በየሰርጡ ያሉ የጊዜ ቀማኞች፣
ዘርፈው የሚያድሩ የከበሩ ሌቦች።
.
ባገሬ ሰማይ ስር
.
ደሞ በዚኛዉ ፅንፍ፣
ደሞ በሌላው ጫፍ፣
.
ራሱን አዋርዶ ሀገሩን ያልጣለ፣
ክብሯን ያስከበረ አንዳንድ ሰው አለ።
.
ተሰቅላ ሲያያት ዉቢቷን ባንዲራ፣
እንባው የሚቀድመው ጸዳሏ ሲበራ፣
ደምስሶ የሚጥል የሙስናን ደባ፣
ጀግንነት በዉስጡ በደሙ የተጣባ።
.
ይህ ሁሉ ባገሬ ሲሆን እየታየ፣
እንክርዳድ ከስንዴ ፍፁም አልተለየ።
.
ራሱን ክዶ ለንዋይ የታመነዉም፣
ራሱን ጥሎ ክብሯን ያስከበረዉም፣
አብበዉ የተወለዱ የማህፀኗ ፍሬዎች።
የኢትዮጵያ ምድር ሁለት ገፅታዎች።
.
እናም ሀገሬ ሆይ!
.
የወላድ መካን እንዳትሆኚ ብርቱ ብርቱዉን ወለጂ፣፣
በልጆችሽ ክንድ ብርታት መቃረንን አስወግጂ፣
የብርሃን ቀንዲል ሆነሽ ለዘለዓለም አብሪ፣
በፍቅርሽ መሬት ላይ መፋቀርን ዝሪ።

10/03/15
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ(@ediwub)
@topazionnn
@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
674 views£di, 09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 12:27:51
አንዳንድ ጊዜ ህይወት
የምትፈልገውን አሰጥህም
ስለማይገባህ አይደለም
የበለጠ ስለሚገባህ እንጂ

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
649 views £NƏ`"`"`"`"`"`, edited  09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 23:08:44
አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እንደሚያደርጉብኝ ላደርግባቸው እፈልጋለሁ
ነገር ግን አልችልም
ምክንያቱም ይህ የእኔ ባህሪ አይደለም

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
938 views £NƏ`"`"`"`"`"`, edited  20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 20:37:31
ሁሉንም ነገር በጥሩ ልብ አድርጉ
በምላሹም ምንም ነገር አትጠብቁ
እናም በጭራሽ አታፍሩም

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.2K views £NƏ`"`"`"`"`"`, edited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 20:19:38 በእምነት ብቻ አጠብቅ ተስፋህን
ጨምር አስተውሎት
አደለምና እምነት፡ ፍላጎት

በምርጫህ እንዳትስት
የአምላክ ፈቃድ ነውና መሆን ያለበት
ብልሀት አክልበት
እምነት ያለእውቀት
ነውና ሞኝነት

@henajs
@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.1K views £NƏ`"`"`"`"`"`, edited  17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:31:38 # ቃልህ

ወዴት ነው ያለው ከሀሣቤ የራቀው
ከልቤ ገስግሶ ጠልቆ የመሸገው
ሄዶ በኖ የጠፋው ቃልህ ላይመለስ
ተንዶ ፈሶብኝ ያለው አልታፈስ

ቆርቁሮኛል ህይወት በርትቷል ህመሙ
ያልተጓዘ ቃልኪዳን ፀንቶብኝ ሸክሙ
ማይተው ሆኖብኝ አጥቻለው መላ
እኔጋ ትርጉሙ ፅኑ ነው መኃላ

ጠፍቷል እኮ መኖር ቃልን ካኖርክበት
የማይድነው ልቤ አንተን ካመነበት
አልመለስ ብሏል ቀልቤ ከሄደበት
ለጐደለ አካሌ ልቤን መልስለት

ፂዮን ምትኩ

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.1K viewsZion, edited  16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:24:27 የፍቅራችን ቅኔ

በፍቅር ሰሌዳ በመዋደድ ቅኔ፣
የኔ ልብ ባንተ ያንተም ልብ በኔ።
የነፍስያችን ወግ ካሳባችን ሰርፆ፣
በልባችን ሀዉልት ፍቅራችን ተቀርፆ።
ደምህና ደሜ ፍፁም ተዋህዶ፣
ባንደበት ሊገለፅ በቃላት ተጋምዶ።
ቀና ብለህ እያት ዉቢቷን ጨረቃ፣
የብርሃን ዝናር በወገቧ ታጥቃ።
ተስፋ ልታድል ጽልመት ለጋረደዉ፣
በትዝታ ጋሪ ሞሽራ ልትሸኘዉ።
ያቺ ዉብ ጨረቃ ምስክር ትሁንህ፣
በሷ ብርሃን የኔ መልክ ይታይህ።
ከዋክብትን ስታይ ከደጃፉ ቆመህ፣
በአንተ ብርሃን ድምቀቴ ይታወስህ።
የኔና አንተ ፍቅር በወርቅ ይመሰላል፣
ካፈር ተደባልቆ ከሳት ይፈተናል።
ከጭቃዉ ይጠራል ነበልባሉን አልፎ፣
ከነፍስ ተራቆ ከህሊና ገዝፎ።

ዔደን(@ediwub)
@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.0K views£di, edited  16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ