2022-09-01 13:03:36
ለአማራ ህዝብ የተከፈለ ዋጋ!!!
የአማራ ካድሬዎች ለህውሓት በሚያሸረግዱበት ወቅት የመግስት አሰራር ትክክል አይደለም በማለቱ ከአመራርነት ታግዶ ነበር። አብይ ወደ ስልጣን ሲመጣ በአዴን የቀድሞ የቁርጥ ልጆችን ወደ አመራር እመልሳለሁ ባለው መሰረት አቶ ዮሃንስ ቧያለው ወደ አመራርነት መጡ።
የኦሮሞ ብልጽግና የበላይነቱን እና ተረኝነቱን ሲጀምር ፊት ለፊት ትክክል አይደለም በማለት መቃወም ጀመሩ። በመጨረሻ በአብይ መሩ ቡድን የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው አቶ ዮሐንስ ቧያለው መንግስታዊ በደል ተፈጸመበት።
መንግስታዊ ስርዓቱ የአማርና የኢትዮጵያን ህዝብ ለጭፍጨፋ እና ለውድመት ዳርጓል በማለት እና ተረኛውን ስርዓት በማውገዙ ምክንያት በደሉ እንደተፈጸመበት ለማረጋገጥ ችለናል።
ፋኖነት በሚለው መጸሃፍ ላይ ስለ ጥቁር ክላሽ ባደረጉት ንግግር ከፍተኛ አመራሩ አቶ ዮሐንስ እንዲታፈን ቢወስኑም ያለመከሰስ መብት እንዳለው ስለተገነዘቡ ለግዜው እንደተውት ሰምተናል።
በደል 1: ሞጋች እና ትክክል ያልሆ ስራን ፊት ለፊት ስለሚቃወም የአብይ መንግሰት አቶ ዮሃንስን ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አባረረው።
በደል 2: በአዲስ መልክ በብቃት ቢያደራጅም የውጭ ጉዳይ ጥናት በዳይሬክተርነትን ስልጣን ነጥቆ ደመወዝ ፣ መኪና እና ጥቅማጥቅሙን አገደበት። ጥበቃዎቹን አንስተው በደህንነት ስጋት ውስጥ ጣሉት።
በደል 3: ወደ ውጭ ጉዞ ለማድረግ ኤርፖርት ቢገኝም አቶ ተመስገን የሚመራው የደህንነቱ ቢሮ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕዛዝ በማስተላለፋቸው ከኤርፖርት ነሀሴ 25/2014 ዓ.ም አስመለሱት። ወደ ቤቱ ሲመለስ የመጨረሻውን በደል ፈጸሙበት።
በደል 4: የመኖሪያ ቤቱን አሽገው ልጆችን ሜዳ ላይ ጥለው አገኛቸው። ይህም የተፈጸመው በከፍተኛ አመራሩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ነው። ቤቱ በግሉ ያገኝው የመንግሰት ቤቶች አስተዳደር ነው። ውል ይዞ ክራይ የሚከፍልበት ሲሆን፣ አመራር በመሆኑ የተሰጠው እንዳልሆነ አረጋግጠናል ።
የትግራይ የቀድሞ ጀነራሎች፣ እነ ጃዋር መሃመድ፣ የኦነግ መሪዎች እነ ዳውድ ኢብሳ፣ እነ ሌንጮ ለታ፣ እነ ዲማ ነገዎ ቤትና መኪና አጃቢ ተመድቦላቸው በሚንቀሳቀሱበት ሀገር የአማራን ታጋይ ቅስም ለመስበር የብልጽግና መንግሰት የፈጸመው ሴራ ነው።
አማራ የቁርጥ ቀን ታጋይ ልጆችህን ታደግ!!!
1.2K views10:03