Get Mystery Box with random crypto!

ቢላሉል ሀበሺይ || Bilalul habeshiy

የቴሌግራም ቻናል አርማ rediyelahuanhu — ቢላሉል ሀበሺይ || Bilalul habeshiy
የቴሌግራም ቻናል አርማ rediyelahuanhu — ቢላሉል ሀበሺይ || Bilalul habeshiy
የሰርጥ አድራሻ: @rediyelahuanhu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 831
የሰርጥ መግለጫ

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ weberekathu ውድ የ ቢላሉል ሀበሺይ || Bilalul habeshiy
ቻናል ቤተሰቦች እዚህ ቻናል ላይ፦
ቂሷ ✔
ሐዲስ✔
ኢስላማዊ ትምህርቶች ✔
እናም ሌሎችም... ይበልጥ ዉዱ ነቢያችንንﷺበሰፊው እንዘክርበታለን። ❤❤
ኢስላም የሚመለከት ነገር ሁሉ ይቀርብበታል።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 20:58:25 · •⊰✿ ✿⊱•
❀━┅┉┈ድንቅ ታሪክ ┈┉┅━❀

በሙሳ ዐለይሂ ሰላም ዘመን ነው....አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።

ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል...። እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ ሚስት ለባለቤትዋ፦"ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች።

እሱም፦"አዎን" ይላታል። "ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው።
ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም ቤት መሄድ ጀመሩ። ሙሳንም ዐለይሂ ሰላም
አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው።

ሙሳም ዐለይሂ ሰላም አላህን ለመኑላቸው። አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል ሀብታም አደርጋቸዋለሁ አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ።"ብሎ መለሰላቸው።

እሳቸውም ጥንዶቹ ጋ በመሄድ አላህ ዱዓቸውን ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው ሀብታምም እንደሚሆኑ ነግረዋቸው እናም ግን ለ አንድ አመት ብቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው። እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው። በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ።ማንም ከሚኖረው የተሻለ ኑሮ መኖርም ጀመሩ።

እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ ሚስት ለባሏ እንዲህ አለችው፦"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለ አንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን አንድ መልካም ስራ እንስራ" አለቺ ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል።

ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት ይገነቡና 7 በር አበጁለት። ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ። ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ ጠዋት ማታ ምግብ ይቀልቡ ጀመር...። በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ።

ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ። እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል። ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው ተጠምደዋል....

ሙሳም ዐለይሂ ሰላም ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦ "ያ ረብ ቃል የገበኽላቸው ለ አንድ አመት ሆኖ ሳለ እንዴት እስካሁን እልደኸዩም?"ብለው አላህን ጠየቁ። (እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን የአላህን ሂክማ ለማወቅ ነው የጠየቁት)

ቸር የሆነው አላህም፦ "ሙሳ ሆይ! ለነዚህ ጥንዶች ከፀጋ በሮቼ አንዲትን በር ስከፍትላቸው...እነሱ ደሞ 7 በር ከፍተው ባሪያዎቼን መቀለብ ጀመሩ። ሙሳ ሆይ! እነሱ ይሄን ሲያረጉ አይቼ የከፈትኩላቸውን በር መዝጋት ከበደኝ"አለው።

❀━┅┉┈ ሱብሀን አላህ ┈┉┅━❀

t.me/RediyelahuAnhu
144 viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:55:41 የዓባስያን ንጉስ የነበረው አቡ ጀዕፈር አል-መንሱር አንድ ግዜ ሻም ውስጥ ኹጥባ እያደረገ :

" እናንተ ሰዎች ሆይ አላህ በእኔ ምክንያት ለሰጣቹ ችሮታ ማመስገን ይገባቹሀል .. ይኸው እኔ ከነገስኩ ጀምሮ አላህ ከዚህ በፊት ይመጣባቹ የነበረውን ወረርሺኝ አስወግዶላቹሀል .." አላቸው ።

ከታዳሚው ውስጥ አንድ ባላገር : ( አላህ እኛ ላይ አንተንም ወረርሽኙንም አንድ ላይ ከመሰብሰብ የጠራ አዛኝና ቸር የሆነ ጌታ ነው ) አለው ።


አላህ በችሮታው ይየን ። ሙሲባዎችም አይሰባሰቡብን ።

t.me/RediyelahuAnhu
136 views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 18:34:46
'ሲዋክ' በርካታ ትላልቅ ጥቅሞች አሉት ከፊሎቹ ልሂቃን እስከ ሰባ አድርሰውታል

በሞት ወቅት ሸሀዳን ያስታውሳል - በአንደበተ-ርቱእነት ፣ በአስተሳሰብና በማስታወስ ችሎታ ላይ ይጨምራል - እይታን ያጠነክራል - ጣእረሞትን ያቀላል - ጠላትን ያርእዳል - ምንዳን ያባዛል - ሽበትን ያዘገያል - ጥሩ የአፍ ጠረንን ይፈጥራል - ድድን ያጠነክራል - ባህሪን ያጠራል - ጌታን ያስደሳል - ጥርስን ያነፃል - ሀብትን እና ምቾትን ያላብሳል - የራስ ምታትና ጅማቱን ያስወግዳል - ጨጓራን ጤናማ ያደርገዋል ያጠነክረዋልም - ቀልብንም ያፀዳል

التقريرات السديدة
للحبيب زين بن سميط


https://t.me/RediyelahuAnhu
https://t.me/RediyelahuAnhu
480 viewsedited  15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 19:39:26 ለየት ያሉ ሰሐቦች
▬▱▬▱▬▱▬

አቡ ኡበይዳ ዓምር ኢብኑ አል ጀራህ
በኡሁድ ጦርነት አባቱን የገደለ ሰሃባ

ኡሰይድ ኢብኑ ሁደይር
ቁርዓን ሲቀራ መላኢኮች ድምፁን ሊሰሙ ከሰማይ የወረዱለት ሰሐባ።

ዒምራን ኢብኑ ሁሰይን
በታመመ ጊዜ መላሂኮች አሰላሙ ዐለይኩም ያሉት ሰሐባ።
https://t.me/RediyelahuAnhu
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ
ከታላላቅ ሰሐቦች ጋር ለሹራ ይቀመጥ የነበረ ወጣት ሰሐባ።

ዐብደላህ ኢብኑ ሰላም
አይሁዳዊ ሰሐባ

ደህየተል ከልቢ
ጅብሪል ዐለይህ ሰላም ብዙ ግዜ በርሱ ተመስሎ የሚመጣ መልከ መልካም ሰሃባ።

ዑስማን ኢብኑ ጠለሃ
የመካ መከፈት ቀን ነቢዩ የከዕባን ቁልፍ ያስረከቡት ሰሃባ።

ዑመር ኢብኑ አል ኸጣብ
ሸይጧን በፍራቻ መንገድ የሚለቅለት ሰሐባ።

ዑካሽ ኢብኑ መህስን
ያለ ምርምር ና ያለ ቅጣት ጀነትን ከሚገቡ 70ሺህ ሰዎች መካከል እንደሆነ ነብዩ የመሰከሩለት ሰሐባ።
https://t.me/RediyelahuAnhu
ኡሰይርም ኢብኑ አብዱል አሽሀል
በኡሁድ ጦርነት የሠለመ አንዲትም ሱጁድ ሳያደርግ ጀነት የገባ ሰሐባ።

▰▰▰▰▰▰▬▰▰▰▰▰▰▬

t.me/RediyelahuAnhu
455 views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 19:38:46 *ነብዩን ﷺ ከኃላው አስከትሎ የሰገደ ብቸኛ ሰሐቢይ
○◦ዐብዱረህማን ኢብኑ ዐውፍ

*ነብዩ ﷺ "ወርውር እናት አባቴ መስዋት ይሁኑልህ!"ያሉት
◌◦ሰሐቢይ ሰዕድ ኢብኑ አቢወቃስ

*ከነብዩ ﷺ ሞት በኃላ የሞተች የመጀመርያ ሚስታቸው
◎◦ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ

*ነብዩ ﷺ በሕይወት እያሉ የሞቱ ሁለት ሚስቶቻቸው
◎◦ኸዲጃ ቢንት ኹወይልድ እና ዘይነብ ቢንት ኹዘይማህ

*ከነብዩ ﷺ ሚስቶች በመጨረሻ የሞተች
◎◦ኡሙ ሰለመህ

*ከነብዩﷺ ሞት በኃላ የሞተች ብቸኛ ልጃቸው
◎◦ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ

*ወደ ሐበሻ ተሰደው የነበሩ የነብዩ ﷺ ሚስቶች
◎◦ሰውዳ፣ዘይነብ ቢንት ኹዘይማ ፣ዘይነብ ቢንት ጀህሽ፣ ሂንድ

*ነብያችን ﷺ በእጃቸው የገደሉት ብቸኛው ሰው
◎◦ ኡበይ ኢብኑ ኸለፍ

▰▰▬▬▬▬
t.me/RediyelahuAnhu
337 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 19:35:21 ከሰሀቦች መካከል ያስተላለፉት
ሀዲስ ከ1000 በላይ በመሆን
ለዚህ ኡማ ትልቅ ውለታ
ያበረከቱት 7 ሰሀቦች ሲሆኑ
እነሱም :

1)አቡ ሁረይራህ 5374 ሀዲስ
በማስተላለፍ.

2)ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር 2630.

3)አነስ ኢብኑ ማሊክ 2286 ሀዲስ
በማስተላለፍ

4)የሙእሚኖች እናት የሆነችው ዓኢሻህ
2210 ሀዲስ በማስተላለፍ.

5)ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ 1660
ሀዲስ በማስተላለፍ.

6)ጃቢር ኢብ ዐብደላህ 1540
ሀዲስ በማስተላለፍ .

7)አቡ ሰዒድ አል ኹድሪይ 1170
ሀዲስ በማስተላለፍ.

رضي الله عنهم

t.me/RediyelahuAnhu
312 views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 19:55:08 ኢብኑ ረጀብ አል-ሐንበሊ'ይ ረሒመሁሏህ :

«በትዕግስት ከጭንቀት መውጣትን መጠበቅ እራሱ አላህን መገዛት ነው .. መከራ ዘውታሪ አይደለምና»

t.me/RediyelahuAnhu
418 views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 19:55:06 «ሱልጧኑል ዑለማእ በመባል የሚታወቁት ታላቁ ዓሊም ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም (አል-ዒዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም) ዲመሽቅ በነበሩበት ጊዜ በጣም ከባድ የኑሮ ውድነት ተከስቶ ነበር ። ነገራቶች ከመወደዳቸው የተነሳ ትናንሽ እርሻ ቦታዎችና ጋርደኖች በርካሽ ይሸጡ ነበር ። የሰዪዲ ዒዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም ባለቤትም አንድ የነበራትን ጌጥ አውጥታ " እስኪ አንድ የሆነ እርሻ መናፈሻ ነገር ግዛልን በበጋ ሙቀት ግዜ አረፍ የምንልበት ብላ ትሰጣቸዋለች"

እሳቸውም ወስደው ይሸጡትና ገንዘቡንም ሰደቃ ሰጥተውት ይመጣሉ። ገዛህ ወይ ብላ ስትጠይቃቸው :

" አዎ ገዝቻለው .. ጀነት ውስጥ ። ሰዎች በጣም ጥበት ውስጥ ሆነው ሳያቸው ገንዘቡን ሰደቃ አደረግኩት " አሏት

እሷም : " ጀዛከሏሁ ኸይረን " አለቻቸው ..»

t.me/RediyelahuAnhu
360 views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 07:04:44 አይ ሴት #አጂብ

በኢማም ማሊክ ዘመን ነው።
ባል እና ሚስት ከባድ ጭቅጭቅ ውስጥ ገብተው ሚስት ደረጃ ላይ ሆና ባል ደግሞ ከታች ምድር ላይ ሆኖ ስድብ እየተቀባበሉ ነው። (ፎቅ ድሮም ነበር)

የሚስቱን የስድብ ናዳ መቋቋም የተሳነው ባል ዳግም ከዚህች ሴት ጋር አብሮ ላለመኖር ወሰነ'ና፦‹‹ከደረጃው ከወጣሽም፣ ከደረጃው ከወረድሽም፣ ደረጃው ላይ ቆመሽ ከቀረሽም ኒካችን ወርዷል ማለት ነው›› ብሎ ለፈትዋ እማይመች አይነት የኒካ ፍቺ መስፈርት አስቀመጠ።

የተወሰነ ቁማ አሰላሰለች። ደረጃውን ብትወጣ ባሏ ሊፈታት ነው፤ ደረጃውን ብትወርድም ሊፈታት ነው፤ ቆማ ብትቀርም መፈታቷ አይቀርም። አንድ ዘዴ ዘየደች'ና ከቆመችበት ደረጃ ላይ ዘላ ባሏ ላይ ሰፈረችበት።

እሷ ካላዩ ሁና ሁለቱም ወደቁ። በሚስቱ ብልኃት የተደመመው ባል ከስር ሁኖ እየተነፈሰ፦‹‹አቦ ፈትዋ! ወላሂ ኢማም ማሊክ ከሞቱ የመዲና ሙፍቲ (ፈትዋ ሰጪ) ምናደርግሽ አንችን ነው››

t.me/RediyelahuAnhu
434 views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 15:48:14
የአካሄድ ጥበብ

ዑመር እሳት አንድደው ተሰብስበው የተቀመጡ ሰዎችን ሲያይ እናንተ የመብራት ሰዎች በማለት ተጣራ ቃሏ እንዳትጎዳቸው በመስጋት 'እናንተ የእሳቱ ሰዎች' አላለም

ሐሰንና ሑሰይን አንድ ሰው በስህተት ውዱእ ሲያደርግ ተመለከቱ እና ወደርሱ ሄደው ከሁለታችን ውዱእ አሳምሮ ማድረግ ማይችለው ማን እንደሆነ በመካከላችን እንድትፈርድ እንፈልጋለን አሉትና ከፊቱ ሆነው ውዱእ ማድረግ ጀመሩ በዚህን ጊዜ ሳቀና ማድረግ እማልችለው እኔ ነኝ አላቸው


አንድ ሰው ወደ ኢማም ጘዛሊ ዘንድ መጣና ሶላት ችላ ባለ ሰው ላይ ፍርዱ ምንድርነው? አለ - ፍርዱ ከኛ ጋር ወደመስጂድ ይዘነው መሄድ ነው - አሉት።


https://t.me/RediyelahuAnhu
512 viewsedited  12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ