Get Mystery Box with random crypto!

«ሱልጧኑል ዑለማእ በመባል የሚታወቁት ታላቁ ዓሊም ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም (አል-ዒዝ ቢን ዐ | ቢላሉል ሀበሺይ || Bilalul habeshiy

«ሱልጧኑል ዑለማእ በመባል የሚታወቁት ታላቁ ዓሊም ዐብዱልዐዚዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም (አል-ዒዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም) ዲመሽቅ በነበሩበት ጊዜ በጣም ከባድ የኑሮ ውድነት ተከስቶ ነበር ። ነገራቶች ከመወደዳቸው የተነሳ ትናንሽ እርሻ ቦታዎችና ጋርደኖች በርካሽ ይሸጡ ነበር ። የሰዪዲ ዒዝ ቢን ዐብዱ-ሰላም ባለቤትም አንድ የነበራትን ጌጥ አውጥታ " እስኪ አንድ የሆነ እርሻ መናፈሻ ነገር ግዛልን በበጋ ሙቀት ግዜ አረፍ የምንልበት ብላ ትሰጣቸዋለች"

እሳቸውም ወስደው ይሸጡትና ገንዘቡንም ሰደቃ ሰጥተውት ይመጣሉ። ገዛህ ወይ ብላ ስትጠይቃቸው :

" አዎ ገዝቻለው .. ጀነት ውስጥ ። ሰዎች በጣም ጥበት ውስጥ ሆነው ሳያቸው ገንዘቡን ሰደቃ አደረግኩት " አሏት

እሷም : " ጀዛከሏሁ ኸይረን " አለቻቸው ..»

t.me/RediyelahuAnhu