Get Mystery Box with random crypto!

Shaday

የቴሌግራም ቻናል አርማ godshaday — Shaday S
የቴሌግራም ቻናል አርማ godshaday — Shaday
የሰርጥ አድራሻ: @godshaday
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.56K
የሰርጥ መግለጫ

https://youtube.com/channel/UCrUVrlQb09LzTVYU05rnaSA
የተወደዳችሁ በዚህ ቻናል ዝማሬዎቻችሁን፣ ስብከታችሁን፣ግጥሞችና ጹሁፍ በዚህ አድርሱን አብረን እናገልግል

@Chere2013
@Abrham2013
ይህ በውስጣቸው የመዘመር የመስበክ እንዲሁም የተለያዩ የፀጋ ስጦታ ያላቸው ግን እድሉን ና ቦታ ላላገኙ ማገልገል ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት ነው
የጌታን ስራ አብርን እንስራ

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-05 20:38:56 ሕይወት ቀያሪ ድንቅ ትምህርት
#የሚተላለፍ_የዘር_መንፈስ
ሁሉም ሰው ሊሰማው የሚገባ
Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!
809 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 14:21:39 #ዛሬ_የባረከኝ_ቃል_ላካፍላችሁ


ኢሳይያስ 58
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
¹² ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ።

በኢየሱስም እፀልያለሁ #የፈረሰው ስፍራዎች በእናንተ ይሰሩ

Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!
2.2K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:58:46 በሻዳይ መንፈሳዊ ቻናል ዛሬ ማታ ድንቅ ትምህርት
#የሚተላለፍ_የዘር_መንፈስ
ሁሉም ሰው ሊሰማው የተገባ

እንዳያመልጣችሁ! ለመስማት ዝግጁ የሆነ እጅን ያንሳ
781 views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:02:06 #የሕይወት_መልህቅ

ከባለፈው ታሪክ የቀጠለ ድንቅ የሕይወት ምስክርነት
#ከዶክተር_ታሪኩ_ፉፋ_ጋር

በማንም ያልተደፈሩና ለመግባት በጣም ከባድ የሆኑትን ቦታዎችን ነፍስን በማስያዝ ያልተደፈሩትን ቦታዎች በወንጌል የደፈረ እንሁም ..... ከሀገር ውጪ ቤተክርስቲያንን በመትከል

በብራዚል ል ውስጥ የሆነው ድንቅ ታሪክ የጋንግስተር መንደሮች ውስጥ በጨለማው ክፍል ........ መንግስትም የሚፈራቸው .....

ኸረረረ ስሙት .....

Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!
860 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 09:06:47 #ሻዳይ_የድሮ_መዝሙሮች

ኢየሱስ
ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ

Share share Share


@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!
800 views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:23:19 New_Life :
#ዘወር_በል!


አንድ ዝሆን ገላውን በወንዝ ይታጠብና መንገድ ይጀምራል። ከመሻገሪያው ድልድይ እንደደረሰም፣ አንድ መላ አካሉ በጭቃ የተጨማለቀ አሳማ ከፊት ለፊቱ ሲመጣ ይመለከታል።

ይህን ጊዜ ዝሆኑ ዘወር በማለት፣ አንዱን ጥግ ይዞ፣ በጭቃ የጨቀየውን አሳማ ያሳልፍና መንገዱን ይቀጥላል።

ከቆይታ በኋላም፣ አሳማው በእብሪት ተወጥሮ ለጓደኞቹ፦ "አያችሁ አይደል ምን ያህል ትልቅ እንደሆንኩ?፡ ዝሆን እንኳን ሳይቀር እኔን ስለሚፈራኝ ጥጉን ይዞ ያሳልፈኛል!" ይላል።

ታዲያ የአሳማውን ንግግር የሰሙ ጥቂት ዝሆኖችም ጓደኛቸውን "እውን ያደረከው ነገር ከፍርሃት የመነጨ ነውን?" ሲሉ ይጠይቃሉ።

ዝሆኑ ግን ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦ "አሳማውን በቀላሉ በእግሬ ልጨፈልቀው እችል ነበር፤ ይሁንና እኔ ንጹህ ስሆን አሳማው ግን ሲበዛ የቆሸሸ ነበር፤ እሱን ልጨፍልቅ ብል እግሬ ይቆሽሽብኛል። እናም ይህን ሽሽት ነበር ከፊቱ ዘወር ያልኩት"።

ልብ በል፤

የምታመዛዝን ነፍስም እንደ ዝሆኑ ናት፤ ከፍርሃት በመነጨ ስሜት ሳይሆን ከቆሻሻ/ግርድ አሳብ/ ራሷን ለመጠበቅ ስትል ከአሉታነት (negativity) ጋር ከሚኖር ግንኙነት ራሷን ታሸሻለች።

በመሆኑም ቆሻሻን (የወረደ አሳብ፣ ተራ ወሬ፣ ስድብና ጥላቻ) በቀላሉ ለማስወገድ ይቻላታል።

የግጥሚያ ስፍራህን በብልሃት ምረጥ።

የገጠመህን ነገር ወደጎን እየተወክ ወደፊት ብቻ ተራመድ!

ለእያንዳንዱ አመለካከት፣ አስተያየትና ሁኔታ ምላሽ መስጠት አይጠበቅብህም።

ሁሉም ሰው ሆነ ሁሉም ነገር፡ ጊዜህንና ትኩረትህን ሊወስድ የተገባው አይደለምና - ከፊቱ ዘወር በል!!

Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!
3.2K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 08:04:27
#ሻዳይ_ፓስፖርት ተቋረጦ የነበረው ሻዳይ ፓስፖርት ( ከእንስሳት አለም) በግሩም አቀራረብ ተመልሶል። ዛሬ ስለዚች #ብልሀተኛ ወፍ ድንቅ ብቃት እንዳስሳለን


ድሮንጎ ( Drongo )

ዛሬ ድሮንጎ ስለተባለችው ብልሀተኛ ወፍ ድንቅ ጥበብ እንነግራችኋለን።
ይቺ ድሮንጎ ወፍ ትላትል ወይም ጊንጥ ተመጋቢ የሆኑ አጥቢ እንስሳቶች ወይም ወፎች ያሉበት አካባቢ የሚገኝ ዛፍ ላይ ትቀመጥና እነሱን ሊበላ ጠላት ሲመጣባቸው ቀድማ የማስጠንቀቂያ ጩኸት ትጮሀለች እነሱም ድምፁን ሰምተው ቀና ሲሉ ጠላታቸው እየመጣ መሆኑን ስለሚመለከቱ ወዲያው ሮጠው ያመልጣሉ።

በተደጋጋሚ ይሄን ድምፅ እያሰማች ከአደጋ ስታድናቸው እንስሳቶቹ ድምፁን ይላመዱት እና የሷን ድምፅ ሲሰሙ መሮጥ ይጀምራሉ። ይቺ ድሮንጎ ወፍ ድምጿን እንደለመዱ ስትረዳ እንስሳቶቹ መሬት ቆፍረው ታግለው ጊንጥ ወይም ትላልቅ ትሎችን ሲያገኙ ወዲያው ይሄን ድምጿን ታሰማለች የዛኔ ጠላት መጣብን ብለው ያደኑትን ምግብ ጥለው ይሮጣሉ ከዛም ድሮንጎዋ መሬት ወርዳ እነሱ ያደኑትን ምግብ ያለ ተቀናቃኝ ተዝናንታ ትበላለች።
ተፈጥሮ ይሄን ብልሀት ለዚች ወፍ መስጠቱ አስገራሚ ነው

Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!
2.0K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 16:48:00
937 views13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:52:40
ያልሰማችሁት ስሙት Part 2 በቅርብ ቀን
ድንቅ የህይወት ምስክርነት #ትለወጡበታላችሁ
980 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:53:18 #አላለም

አዎ አላለም
ላይሰጥ ጠይቁ ላይከፍት አንኳኩ ላይገኝ ፈልጉ
#አላለም መጠየቅ መፈለግ ማንኳኳት #የእኔ ድርሻ ነው

Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!
1.4K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ