Get Mystery Box with random crypto!

New_Life : #ዘወር_በል! አንድ ዝሆን ገላውን በወንዝ ይታጠብና መንገድ ይጀምራል። ከመሻገ | Shaday

New_Life :
#ዘወር_በል!


አንድ ዝሆን ገላውን በወንዝ ይታጠብና መንገድ ይጀምራል። ከመሻገሪያው ድልድይ እንደደረሰም፣ አንድ መላ አካሉ በጭቃ የተጨማለቀ አሳማ ከፊት ለፊቱ ሲመጣ ይመለከታል።

ይህን ጊዜ ዝሆኑ ዘወር በማለት፣ አንዱን ጥግ ይዞ፣ በጭቃ የጨቀየውን አሳማ ያሳልፍና መንገዱን ይቀጥላል።

ከቆይታ በኋላም፣ አሳማው በእብሪት ተወጥሮ ለጓደኞቹ፦ "አያችሁ አይደል ምን ያህል ትልቅ እንደሆንኩ?፡ ዝሆን እንኳን ሳይቀር እኔን ስለሚፈራኝ ጥጉን ይዞ ያሳልፈኛል!" ይላል።

ታዲያ የአሳማውን ንግግር የሰሙ ጥቂት ዝሆኖችም ጓደኛቸውን "እውን ያደረከው ነገር ከፍርሃት የመነጨ ነውን?" ሲሉ ይጠይቃሉ።

ዝሆኑ ግን ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦ "አሳማውን በቀላሉ በእግሬ ልጨፈልቀው እችል ነበር፤ ይሁንና እኔ ንጹህ ስሆን አሳማው ግን ሲበዛ የቆሸሸ ነበር፤ እሱን ልጨፍልቅ ብል እግሬ ይቆሽሽብኛል። እናም ይህን ሽሽት ነበር ከፊቱ ዘወር ያልኩት"።

ልብ በል፤

የምታመዛዝን ነፍስም እንደ ዝሆኑ ናት፤ ከፍርሃት በመነጨ ስሜት ሳይሆን ከቆሻሻ/ግርድ አሳብ/ ራሷን ለመጠበቅ ስትል ከአሉታነት (negativity) ጋር ከሚኖር ግንኙነት ራሷን ታሸሻለች።

በመሆኑም ቆሻሻን (የወረደ አሳብ፣ ተራ ወሬ፣ ስድብና ጥላቻ) በቀላሉ ለማስወገድ ይቻላታል።

የግጥሚያ ስፍራህን በብልሃት ምረጥ።

የገጠመህን ነገር ወደጎን እየተወክ ወደፊት ብቻ ተራመድ!

ለእያንዳንዱ አመለካከት፣ አስተያየትና ሁኔታ ምላሽ መስጠት አይጠበቅብህም።

ሁሉም ሰው ሆነ ሁሉም ነገር፡ ጊዜህንና ትኩረትህን ሊወስድ የተገባው አይደለምና - ከፊቱ ዘወር በል!!

Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!