Get Mystery Box with random crypto!

#ሻዳይ_ፓስፖርት ተቋረጦ የነበረው ሻዳይ ፓስፖርት ( ከእንስሳት አለም) በግሩም አቀራረብ ተመልሶ | Shaday

#ሻዳይ_ፓስፖርት ተቋረጦ የነበረው ሻዳይ ፓስፖርት ( ከእንስሳት አለም) በግሩም አቀራረብ ተመልሶል። ዛሬ ስለዚች #ብልሀተኛ ወፍ ድንቅ ብቃት እንዳስሳለን


ድሮንጎ ( Drongo )

ዛሬ ድሮንጎ ስለተባለችው ብልሀተኛ ወፍ ድንቅ ጥበብ እንነግራችኋለን።
ይቺ ድሮንጎ ወፍ ትላትል ወይም ጊንጥ ተመጋቢ የሆኑ አጥቢ እንስሳቶች ወይም ወፎች ያሉበት አካባቢ የሚገኝ ዛፍ ላይ ትቀመጥና እነሱን ሊበላ ጠላት ሲመጣባቸው ቀድማ የማስጠንቀቂያ ጩኸት ትጮሀለች እነሱም ድምፁን ሰምተው ቀና ሲሉ ጠላታቸው እየመጣ መሆኑን ስለሚመለከቱ ወዲያው ሮጠው ያመልጣሉ።

በተደጋጋሚ ይሄን ድምፅ እያሰማች ከአደጋ ስታድናቸው እንስሳቶቹ ድምፁን ይላመዱት እና የሷን ድምፅ ሲሰሙ መሮጥ ይጀምራሉ። ይቺ ድሮንጎ ወፍ ድምጿን እንደለመዱ ስትረዳ እንስሳቶቹ መሬት ቆፍረው ታግለው ጊንጥ ወይም ትላልቅ ትሎችን ሲያገኙ ወዲያው ይሄን ድምጿን ታሰማለች የዛኔ ጠላት መጣብን ብለው ያደኑትን ምግብ ጥለው ይሮጣሉ ከዛም ድሮንጎዋ መሬት ወርዳ እነሱ ያደኑትን ምግብ ያለ ተቀናቃኝ ተዝናንታ ትበላለች።
ተፈጥሮ ይሄን ብልሀት ለዚች ወፍ መስጠቱ አስገራሚ ነው

Share Share Share

@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
@Godshaday @Godshaday
ሊያደርግ ያለውን ያውቃል!!!