Get Mystery Box with random crypto!

የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️

የቴሌግራም ቻናል አርማ geb19 — የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
የቴሌግራም ቻናል አርማ geb19 — የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
የሰርጥ አድራሻ: @geb19
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.75K
የሰርጥ መግለጫ

👉ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤዛም የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ከአጽራረ ቤተ ክርስትያን ለመጠበቅ የራሱን ድርሻ ለመወጣት የሚተጋ ቻናል ነው።
✥✥✥✥✥join @Geb19 ✥✥✥✥✥
👇ለአስተያየትዎ
📧 contact me @efr21 or @GEB19bot
ልብ እንበል
እናታች እንኳን የማትቀይረን ሞት ከፊታችን አለ🛌

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-01-08 22:51:41
Share share share share
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
════◄✣••✥••✣►════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @eotc27
2.3K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 06:43:57 ያለመጠን የሚያስገርም ልደት
••●◉ ✞ ◉●••
ሕፃን ተወልዶልናል፣ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፣አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ፣ስሙም ድንቅ መካር፣ኃያል አምላክ ፣የዘለዓለም አባት፣የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።ኢሳ ፱፥፮
••●◉ ✞ ◉●••
እናቱን የፈጠረ ልጅ፤
ፈጣሪዋን የወለደች እናት፤
አባቱ የማይቀድመው ልጅ::
••●◉ ✞ ◉●••
መልክን ከደም ግባት ፣ንፅህናን ከቅድስና አስተባብራ የያዘች እናት ማረፊያ አጥታ እንዴት በበረት ወለደች
አለቅነት በጫንቃው የሆነ ጌታ አንዴት በበረት ተወለደ
••●◉ ✞ ◉●••
አንደበቶች ሁሉ ስለ እርሱ በጐነት የሚያወሩለት ጉልበቶችም ሁሉ የሚንበረከኩለት የሁሉም ጌታ የሁሉም ሀኪም የሁሉም መድሐኒት የሆነው ጌታ የዛሬ 2014 በከብቶች በረት ከንፅህት ድንግል ተወለደልን ይህ የፍቅሩ ጅማሬ ነው።ተወለደ ስንል ተወለድን ማለታችን ነው
••●◉ ✞ ◉●••
በበረት የወደቁ ፣ጊዜ የከዳቸው፣የታሰሩ፣የተፈናቀሉ፣የተሰሳደዱ፣በመንገድና በቤት በችግር ያሉ አሉና እናስባቸው።
••●◉ ✞ ◉●••
በዚህ ሰጪ ይፀድቅበታል፣ተቀባይ ያመሰግንበታል ሰጥተን ለመፅደቅ፣ተቀብለን ለማመስገን ያብቃን ።
••●◉ ✞ ◉●••
ተወዳጆች ሆይ ፍቅር ተወልዶልናል
እንኳን አደረሳችሁ

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን

@efr21 @Geb19
@Geb19bot @Geb19
@efr21 @Geb19
1.8K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-05 13:31:06 ለዘተወልደ
••●◉ ✞ ◉●••
ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ምንተንብሎ ናስተማስሎ ለመድኀኒነ
አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ/2/ ከራድዮን
••●◉ ✞ ◉●••
ትርጉም፦
ከቅድስት ድንግል የተወለደውን ምን እንበለው መድሀኒታችንንስ በምን እንመስለዋለን በአንበሳ ነውን ወይንስ ከራድዮን በሚባል ነጭ ወፍ ነውን
••●◉ ✞ ◉●••
እንኳን ለአምላክ የልደት ቀን በሰላም አደረሰን
••●◉ ✞ ◉●••

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን

@efr21 @Geb19
@Geb19bot @Geb19
@efr21 @Geb19
1.7K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 08:44:37 በዓለ ክብሩ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
••●◉ ✞ ◉●••
ነቢዩ ዳንኤል ዐይኖቼንም  አነሣሁ አለና አስከትሎ እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ብረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡…ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ  ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ አለ፡፡ዳን 10÷5-9
••●◉ ✞ ◉●••
ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡ የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ይህን ለመረዳት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ መለኮቱ ለወንጌላዊው ዮሐንስ የተገለጠበትን መገለጥ መመልከት በቂ ነው፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ በራእይ ስለተመለከተው የክርስቶስ ግርማ ሲናገር ከኋላዬም እንደ መለከት ድምፅ ያለ ታላቅ ድምፅን ሰማሁ፡፡…የሰው ልጅ የሚመስልን አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ልብስ የለበሰ ፣ ወገቡንም በወርቅ ዝናር የታጠቀ ነበር፡፡ራሱና የራስ ጠጉሩም እንደ ነጭ የበግ ጠጉር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፡፡እግሮቹም በእሳት የነጠረና የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙህ ውኃ ድምፅ ነበረ፡፡… ባየሁትም ጊዜ ከእግሩ ሥር ወደቅሁ አንደ ሞተ ሰው ሆነሁ አለ፡፡ራእይ 1÷2-17 በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች ቅዱስ ገብርኤል በግርማው አምላኩን እንደሚመስል አንረዳለን፡፡የስሙም ትርጓሜ የሚያስዳው ይህን እውነታ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ማለት ነውና፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ቅዱስ ገብርኤል በብሉይ ኪዳን በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው(ዳን 5÷11)ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ መልአክ ነበር፡፡ ለዚህ ነቢይ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡ዳን 9÷21-22) አሁንም ነቢዩ ዳዊት አቤቱ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ብፁዕ ነው፡፡ በልቅሶ ሸለቆ በወሰንኸቸው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፡፡መዝ 83÷5-6 እንዳለው በቅድስና ሕይወት በመጽናታቸው ምክንያት ቅዱስ ገብርኤል መምህር የሆናቸው ቅዱሳን ብዙዎች ናቸው፡፡ የእኛ እውቀት በሰማያት ከትመው ካሉት ቅዱሳን መላእክት እውቀት ጋር ሲነጻጸር እኛን እንደ ሕፃናት ያደርገናል፡፡ እኛ የእነርሱን እውቀት ገንዘባችን የምናደርገው በትንሣኤ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ዛሬ በመስታወት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፡፡ አሁን በከፊል ኋላ ግን እንደተገለጠልኝ መጠን ሁሉን አውቃለሁ(1ቆሮ 13÷12) ብሎ አስተማረን፡፡ ስለዚህም እውቀታችን የተሟላ እንዲሆንና ሰይጣንን ለመቃወም እንድንበቃ የቅዱሳን መላእክት የእውቀት ድጋፍ በእጅጉ ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም ከእኛ ይልቅ ሳጥናኤልን የሚያውቁት እነርሱ ናቸውና፡፡ እንዲህም ስለሆነ ጌታችን በእውቀታቸው እኛን እንዲረዱን ለእያንዳንዳችን  ጠባቂ መልአክትን ሰጠን፡፡ማቴ 18÷10፤ሉቃ 13÷6-9
••●◉ ✞ ◉●••
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው።ንጉሥ ናብከደነፆርም ሠልስቱ ደቂቅ እሳቱ አንዳች ጉዳት ሳያደርስባቸው በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ ከእነርሱ ጋር የሰው መልክ ያለው ነገር ግን አምላክን የሚመስል መልአክ ተመለከተ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊቀ ካህናቱን ቀያፋን ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን (ዮሐ 11÷49) ብሎ እንዳናገረው እንዲሁ ናብከደነፆርንም እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን በዚያ አያለሁ ምንም የነካቸው የለም፤የአራተኛውም መልክ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል ብሎ እንዲናገር አደረገው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅን መልክ ያለው ያለው በኋላም መልአክ ብሎ የተናገረለት ቅዱስ ገብርኤልን ነበር፡፡ እርሱ ስለመሆኑ ለነቢዩ ዳንኤል በተገለጠበት ግርማ ማረጋገጥ እንችላለን።
••●◉ ✞ ◉●••
ናብከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ከእሳቱ ወጡ ሹማምንቱና መኳንንቱ፣ አማካሪዎችና የአገር ገዢዎች ሁሉ እሳቱ በእነዚህ ብላቴኖች ላይ አንዳች አቅም እንዳልነበረው፣ ከጠጉራቸው ቅንጣት አንዱን እንኳ እንዳላቃጠለው፣ ሰናፊናቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ፡፡ ንጉሥ ናብከደነፆርም መልአኩን ልኮ ያዳናቸውን የእነዚህን ቅዱሳንን አምላክ አመሰገነ፡፡ በእነርሱ አምላክ ላይም የስድብን ቃል የሚናገር ሰው እንደሚገደልና ቤቱም የጉድፍ መጣያ እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ አዛርያ አናንያ ሚሳኤልም በንጉሡና በሹማምነቱ ዘንድ ሞገስ አገኙ በክብርም ከፍ ከፍ አሉ፡፡ዳን ም 3 በሙሉ
••●◉ ✞ ◉●••
ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መንጎቹዋ የእምነትን ፍሬ ከእነዚህ ብላቴኖች ተምረው እግዚአብሔርን በማምለክ እንዲጸኑና የመልአኩን የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት እንዲረዱ በታኅሣሥ 19 ቀን ይህን ዕለት ትዘክራለች፤ በታላቅ ድምቀትም ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እምነት በድርጊት ሊታይ የሚገባው ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ የሚል ሁሉ ካመነበት ጊዜ አንስቶ ክርስቶስን መስሎ ለመኖር ሊተጋና መስሎ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡ በሠልስቱ ደቂቅ  የታየው እምነት በአንድ ጀምበር የተገነባ እምነት ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ በአንድ እግዚአብሔር ታምነው በቅድስና ሕይወት በመመላለስ የመጣ እምነት ነው፡፡ እነዚህ ብላቴኖች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኙትን የድል አክሊል ተስፋ አድርገዋልና አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል የነደደውን የእሳት እቶን አላስፈራቸውም፤ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው ጽኑ እምነት በእሳት ተቃጥለው ለመሞት እንኳ አስጨከናቸው፡፡ እንዲህም ሆነው በመገኘታቸው በእምነታቸው እግዚአብሔርን ደስ አሰኙት፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ባለሟሉን ቅዱስ ገብርኤልን በመላክ ከእሳቱ እቶን ታደጋቸው፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @eotc27
2.8K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 06:44:32 እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ብረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ  ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ አለ፡፡ዳን 10÷5-9
••●◉ ✞ ◉●••
ኦርቶዶክሳውያን ተወዳጆች እንኳን ለታህሳስ ፩፱የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሰን
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @eotc27
1.5K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 16:00:29 የገኃነም ደጆች አይችሏትም pinned an audio file
13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 15:59:43 በጣም ደስ የሚል ስብከት ══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @eotc27
1.5K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-06 06:29:05 ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
••●◉ ✞ ◉●••
የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። ማቴ 5፡42-48፡፡
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @won21
2.3K viewsËfřõñ Ýëđñķūñůâ Mãřýām ፮ ༒ً , 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ