Get Mystery Box with random crypto!

የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️

የቴሌግራም ቻናል አርማ geb19 — የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
የቴሌግራም ቻናል አርማ geb19 — የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
የሰርጥ አድራሻ: @geb19
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.75K
የሰርጥ መግለጫ

👉ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤዛም የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ከአጽራረ ቤተ ክርስትያን ለመጠበቅ የራሱን ድርሻ ለመወጣት የሚተጋ ቻናል ነው።
✥✥✥✥✥join @Geb19 ✥✥✥✥✥
👇ለአስተያየትዎ
📧 contact me @efr21 or @GEB19bot
ልብ እንበል
እናታች እንኳን የማትቀይረን ሞት ከፊታችን አለ🛌

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 14:19:37

348 viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉, 11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 11:24:25
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ።

ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው። ወንጌላዊ ዮሐንስም፣ እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤ ታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕዐ ሕይወት ሥር ተቀምጦአየው። የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እን ዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው። እነርሱም የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት። ያን ጊዜም ከዕዐ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ። የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመለሱ።የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግልማርያም አማላጅነት ያማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ ፡ ማትያስ ፡ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን።

በዚችም ዕለት ዳግመኛ የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው።የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗልና ስለዚህም እርሷን መው ደዱን የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑየድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በኃያሉ ተጋዳይ በጊዮርጊስም ጸሎት በእኛ ላይ ምሕረት ይቅርታ ቸርነት ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።

በዚችም ቀን የሶርያ መስፍን ጊጋር በሰማዕትነት ሞተ።ሰማዕት የሆነበትም ምክንያት ጌታችን ከእመቤታችን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ በተሰደደ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ሳለ ኀሮድስ ሰምቶ ከበው ይዘው ይገድሏቸው ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ ጊጋርም ጭፍሮች እንዲያገኙአቸው አሸሻቸው።ስለዚህም ኄሮድስ ተቆጣ ጊጋርንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ሕዋሳቱንም ሁሉ ቆራረጠ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት መታሰቢይውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በሦስት አክሊሎችም ተጋረደ ሦስት አክሊላትን ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @efr21
437 viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً , 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 13:27:25
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @efr21
541 viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً , 10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 13:21:39
በታላቁ መምህራችን መምህር ምህረታአብ አሰፋ ለተዋህዶ ልጅ በሙሉ ጥሪ ተደርጉል ቴቄል ክፍል ሁለት ሊለቀቅ ነው። ከታች በተቀመጠው የዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ::ባለ ማህተቦች ሼር በማድረግ ላልሰሙት

══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @efr21
441 viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً , 10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 08:33:20 መልካም ወጣት ማለት
══════◄✣••✥••✣►══════
በሆሆታ እና በዳንኪራ ወጣት አይገነባም። ወጣቱን ገና ከዩንቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ዘርግቶ ለሀገር እና ለወገን ከብሄር እና ጎጠኝነት የፀዳ እንክርዳድ ያልገባበት መልካም ዘርን ለሚያመርተው ማህበረ ቅዱሳን ታላቅ ክብር አለኝ። አለም እንዲህ ያሉትን ማህበራት አትወድም አለም ወርቅ እና ብሯን ምትሰጥህ ማንነትህን ከጣልክ ነው። ለዚህ ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትር ደረጃ የተንቆለጳጰሰውን ሀገር የተባለችውን ሀይማኖቱን ወጣቱን በብር እየደለለ ሚገዛውን ዬናታንን ማየት ነው።
══════◄✣••✥••✣►══════
መልካም ወጣት በሚል ሰበብ ማህተብህን ምትበጥስ አንተ ሰው አስተውል ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ይልሀል " ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና አጥብቃችሁ ተቃወሙት ፩ ጴጥ ፭
══════◄✣••✥••✣►══════
ብር ልስጥህ እምነትህን ካድ ፣ቤተክርስትያን ይቅርብህ አዳራሽ ና፣ፓስተር እገሌ ጋር ልውሰድህ ፣ ስራ አስገባሀለው ትዳር ታገኛለህ ፣ሲልክ አጥብቀህ ተቃወም።እመነኝ ብሩ ያልቃል አንተ ግን ከገባህ መውጫም የለህ ።እንደ ጨው ሟሙተህ ትቀራለህ። ከቀደመችው አባቶችህ ለተሰውባትለተሰደዱባት ለታረዱባት ከተዋህዶ በረት ሚለይህን ሁሉ ለይ። ይች አለም ምድራዊ ነች ታልፋለች ትመክናለች ።የማታልፈው ዘልዐለማዊ ርስት መንግስተ ሰማያትን ለስባሪ ሳንቲም ብለህ በምስር ወጥ እምነትህን እንዳታጣ አስተውል የመጨረሻው ዘመን እንደሰረሰ አትዘንጋ
══════◄✣••✥••✣►══════
ታስታውሳለህ አይደል ሀዋርያት ጌታችንን ንገረን የመምጣትህ ምልክት ምንድን ነው ብለው ሲጠይቁት የመለሰላቸውን ማቴ 24 የጥፋት እርኩሰት በተቀደሰው ቦታ ላይ ስታዩ አስተውሉ ወንድሜ (እህቴ) እናስተውል ዛሬ በተቀደሰው ስፍራ ለይ እርኩሰት አለ።የይሁዳ ልጆች ካህናት ጌታችንን ደሙን ያፈሰሰበትን መስቀል ይዘው ፣የቅዱስ አባ እንጦንስ ቆብ ደፍተው ስለመለየት እና መገንጠል ይሰብኩናል ።አስተውል አስቀድሞ ጌታ ባይነግረን አልቆልን ነበር ግን እንደሚመጡ ነግሮናል መጥተዋልም ። እመነኝ ሀሳባቸው ምድራዊ ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው ከእነዚህ ደግሞ ራቅ ሽሽ።አንተ ግን የቀደመችውን መንገድ ታውቃታለህ የቅዱስ ያሬድ ሀገር ኑር።የተክለሀይማኖት የሰማዕታት ሀገር አለችህ። የጠላትን ወሬ አትስማ በተማርክበት ፀንተህ ኑር።
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ። ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @efr21
509 viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً , 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 13:51:27 ደብረታቦር
══════◄✣••✥••✣►══════
ደብረታቦር ማለት በወይራ የተከበበ ተራራ ማለት ። ደብረታቦር ከጌታ ከዘጠኙ በዓላት አንዱ ነው። ወእምድኅረ ስሱ መዋዕል ነሥኦሙ እግዚእ ኢየሱስ ለጴጥሮስ ወለ ያዕቆብ ወለዮሐንስ እኍሁ ወአዕረጎሙ ደብረ ነዋኃ እንተ ባሕቲቶሙ ማቴ 17:-1 ከስድስተኛው ቀን በኃላ ወደ ጴጥሮስ፣ዮሐንስ፣ያዕቆብን ወደ ተራራ አወጣቸው ማለት በፍልጵስዩስ ከተማ የሰውን ልጅ ሰው ማን ይልዋል ብሎ ጠይቋቸው ዮሐንስ ነው የሚሉህ አሉዉ ኤልያስ ነው የሚሉህ አሉዉ እናተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ የእግዚአብሔር አብ የባህይሪ ልጅ ነህ ቢለው በአንተ ቃል መሰረትነት ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን አንፃታለው።የሲኦል ደጆችም አይበረታቱባትም። ══════◄✣••✥••✣►══════
ነሐሴ 13 ከነቢያት መሴና ኤልያስን። ከሐዋርያት ያዕቆብ፣ጴጥሮስና ዮሐንስን ይዞዎ ካወጣቸው በኋላ ባህርየ መለኮቱን ቢገልጥባቸው ያዕቆብና ጴጥሮስ ወደቁዉ ሙሴም መቃብሬ ይሻለኛል አለ። ኤልያስም በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ተነጠቀ። ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ሲሆን ቢወድቁም አትፍሩ እኔ ነኝ አላቸው። ለምን ምስጥሩን በከተማ አላደረገውም ቢሉ በከተማ አድርጎት ቢሆን ምስጢር አፈሳ በሆነ ነበርና። ለምን በታቦር አደረገው ቢሉ ሐዋርያት በሲኖዶስ ታቦር ብለው አንስተውታል። ══════◄✣••✥••✣►══════
ትንቢት ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚኣከ ይትፌሥሑ ተብሎ ተነግሯል። ምሳሌም ባርቅ ሲሳራን ድል ነሥቶበታል። ጌታም በልበ ሐዋርያት ያደረውን ሰይጣን ድል ነስቶበታል። ከደናግል ኤልያስን ከመአስባን ሙሴ ማምጣቱ መንግሥተ ሰማያትን ማአስባንም ደናግልም እዲወርሳት ሲያጠይቅ ነው ። መልካም በዓል። ══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @eotc27
1.0K viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً , 10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 11:56:17 በፈጣሪ ስም ይቅርታችሁ ትድረሰን
482 viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً , 08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 11:55:23 ተወዳጆች ባጋጠመን #ችግር ከአገልግሎት ርቀን ብንቆይም ከዛሬ ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ #አገልግሎት የምንጀምር ሲሆን @geb19bot ላይ ጥያቄዎን እንዲጠይቁ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።
••●◉ ✞ ◉●••
ለረጅም ጊዜ ታግሳችሁ ከቻናላችን ላልወጣችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን ፈጣሪ ክብረት ይስጥልን
••●◉ ✞ ◉●••
#አንድ_ጌታ_አንድ_ሀይማኖት_አንዲት_ጥምቀት ኤፌ 4፥4-5
••●◉ ✞ ◉●••
#ለሚጠይቁዋችሁ_ሁሉ_መልስ_ለመስጠት_ዘወትር_የተዘጋጃችሁ_ሁኑ_ነገር_ግን_በፍርሃትና_በየዋህነት_ይሁን።1ኛ ጴጥ፫፥፲፭

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ ። ለዘላለሙ አሜን ።


@efr21 @Geb19
@Geb19bot @Geb19
575 viewsወ ҉ን ҉ደ ҉ ሰ ҉ ን ҉ ༒ً , edited  08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 08:20:39
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @eotc27
456 views₩ōňđĩ€ Ýëđñķūñůâ Mãřýām ፮ ༒ً , edited  05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 07:11:09 ቅዱስ ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ
••●◉ ✞ ◉●••
እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ ይላል (ኢያሱ 5÷13-15)፡፡ ይህን ጥቅስ ልብ ብለን ብናጤነው ለሌላው ሁሉ መርህ ይሆናልና ጥቂት ለማብራራት እንሞክራለን፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
እንዲሁም እግዚአብሔር ራሱ ለኢያሱ በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆነው እንዲሁ ካንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም አልተውህም፡፡ (ኢያሱ 1÷1-9) በማለት ምን ያህል እንዳከበረው ያስረዳል፡፡ እስራኤላውያን አሞራውያንን በወጉ ጊዜ ቀኑ ስለመሸባቸው ከመደበኛው የተፈጥሮ ሕግ ውጭ ቀኑ እንደማይጨልምና መዓልቱ እንዲረዝም ኢያሱ በጸሎት ፈጣሪውን ስለጠየቀ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ቀኑን አስረዝሞ ከሰማይ በረድ አዝንሞ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት የፈጸመውን አስደናቂ ተአምር እንዲህ ብሎ ጸፏል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና እግዚአብሔር የሰውን ቃል (ልመና) የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም›› (ኢያ 10÷12-14) በማለት ተገልጿል፡፡ በጠቅላላው ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ የአሕዛብ ምሽጐችን አፍርሶ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሰ ኢያሱ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ይህ የእስራኤል መሪ በእጅ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የተገለጸለት ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን አላወቀም፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም ከመልአኩ የተሰጠው መልስ ታላቅ መሪና ነቢይ የሆነውን የኢያሱን አስተሳሰብ ለወጠው፡፡ ይኸውም ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ የሚለውን ቃል ሲሰማ ኢያሱ በፊቱ የቆመው ተራ ወታደር ሳይሆን የመላእክት ሠራዊት አለቃ ከሙሴ ሳይለይ የእስራኤልን ሕዝብ የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ አንተ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ለኢያሱ የምትነግረኝ ምንድነው በማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም መላእክት ጌቶች ይባላሉ፡፡ ጌትነታቸውም የጸጋ ጌትነት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛማ ኃጢአተኞች ጌታዬ፤ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ…በማለት የአክብሮት (የጸጋ) ስግደት በመስገድ ብንለምነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጭ አልወጣንም፡፡ የፈጣሪን ክብር ለፍጡር አልሰጠንም፡፡ ተሳስታችኋል የሚለን ሰው ቢኖር እኛ አብነት ያደረግነው የእግዚአብሔር ወዳጅ ኢያሱን ስለሆነ ኢያሱም ተሳስተሃል ይባል፡፡ መልአኩም ኢያሱ ያቀረበለትን የአክብሮት ስግደትና ጥያቄ በመቀበል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን መልእክት ነገረው፡፡ ኢያሱም ትእዛዙን ፈጸመ፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ኦርቶዶክሳውያን ተወዳጆች እንኳን ለሰኔ 12,የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ህይወት ለቀየረበት በአል በሰላም አደረሰን
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @won21
1.0K views₩ōňđĩ€ Ýëđñķūñůâ Mãřýām ፮ ༒ً , 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ