Get Mystery Box with random crypto!

የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️

የቴሌግራም ቻናል አርማ geb19 — የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
የቴሌግራም ቻናል አርማ geb19 — የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️
የሰርጥ አድራሻ: @geb19
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.75K
የሰርጥ መግለጫ

👉ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤዛም የሆናት ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ከአጽራረ ቤተ ክርስትያን ለመጠበቅ የራሱን ድርሻ ለመወጣት የሚተጋ ቻናል ነው።
✥✥✥✥✥join @Geb19 ✥✥✥✥✥
👇ለአስተያየትዎ
📧 contact me @efr21 or @GEB19bot
ልብ እንበል
እናታች እንኳን የማትቀይረን ሞት ከፊታችን አለ🛌

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-11 08:33:16 እነሆ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢሏችሁ አትመኑ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ።በማቴ 24፥24
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁማር 13፥15
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ወንድሞች ሆይ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።ዕብ 3፥12
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
እንደተማራችሁት በሃይማኖት ጽኑ፣ ልዩ ልዩ ዓይነት በሆኑ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፣ በዐመጸኖች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፣ ልጆች ሆይ መጨረሻው ሰዓት ነው የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቋዋሚዎች ተነሥተዋል፣ ስለዚህም የመጨረሻው ሰዓት እንደሆነ እናውቃለን።ቆላ 2፥7 ፣ ዕብ 13፥7 ፣ 2ኛ ጴጥ 3፥6 ፣ 1ዮሐ 2፥18
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ።ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን .......በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል።የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።ማቴዎስ 7፥13-23
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21
1.8K views₩ōňđĩ€ Ýëđñķūñůâ Mãřýām ፮ ༒ً , 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 23:30:20 በትንሣኤሁ ቅድስት አግብኦ ለብእሲ ዳግመ ውስተ ገነት/ልዩ በሆነች መነሳቱ ሰውን እንደገና ወደ ገነትአገባው::ቅ/ ኤፍሬም
••●◉ ✞ ◉●••
ይግብሩ በዓለ ሰማያት ይግብሩ በዓለ ደመናት ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሃጺባ በደመ ክርስቶስ።ቅ/ያሬድ
••●◉ ✞ ◉●••
ሞቱን በሚመስል ሞት ከርሱ ጋር ከተባበርን ትንሳኤዉን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡ ሮሜ 6፥5
••●◉ ✞ ◉●••
በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንልን ፡፡እግዚአብሔር በህመም የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን ምህረትን ይላክላቸው፡፡የጎደለንን እግዚአብሔር ይሙላልን።እንደ ሰደድ እሳት በአለም ዙሪያ የሰው ነፍስ እያጠፋ ያለውን የጊዜውን ክፍ መንፈስ በእግዚአብሔር በበረታው ክንዱ ተመቶ ከእግራችን ስር ያድርግልን።ስንዱዋን አመቤት እምዬ ተዋህዶ ቤታችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን።ባለ ቀሰተ ደመነዋ ሀገር ኢትዮጵያን ክፍዋን አያሳየን
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21
2.2K views₩ōňđĩ€, 20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 23:30:19
ስለ ዓለም መበዥት ልጇ የተሰቀለባት የመጀመሪያም የመጨረሻም እናት
••●◉ ✞ ◉●••
ከሄሮድስ የሞት አዋጅ ታስጥለው ዘንድ ዓመታትን ስለእሱ ስትል ወደ በረሃ ተሰዳለች።ወንበዴዎች እንዳይነጥቋት፤ ዘራፊዎች እንዳይወስዱባት እልፍ ቀናትን በሰቀቀን አሳልፋለች።30 ዓመታትን ክርስቶስ የሚለውን ስም ከእርሷ ውጪ ማንም አያውቅም።ልጇ ታምራትን ሳያደርግ፤ሙት ሳያነሳ፤ሽባ ሳይተረትር ሰማያዊ መናን እና ፅዋን ከሰማይ አውርዶ ሳይመግብ በልቧ ያነገሰችው ውድ ልጇና ጌታዋ ነው።ዓለምን በመዳፏ የያዘውን ልጇን በጀርባዋ ተሽክማ ይዛ የተሰደደቸውን፤ ከበረሃ ወንበዴ በሰቀቀን የጠበቀችውን ልጇን ጲላጦስ በበርባን ምትክ ሞት ፈረደበት።በስስት የምትመለከተውን ገፁን በደም ለወሱት።
••●◉ ✞ ◉●••
በጀርባዋ ተሸክማው ዘመናትን የተሰደደችው አካሉ በሮም ወታደሮች ግርፋት ተበጣጠሰ።በእሱ ሞት ፍጥረት ነፃ ሲወጣ ድንግል ማርያም ግን በእናትነቷ አንጀቷ አነባች።የተከተሉት ሁሉ ሲበተኑ የወለደችው እናቱ ግን እስከመጨረሻው እስትንፋሱ ድረስ ሽቅብ ልጇን ከተቸነከረበት መስቀል ሆኖ ተመለከተችው።ቅዱሱን ልጇን ርኩሳኑ ገደሉት።አንዳች በደል ሳይገኝበት በበደለኞች እጅ ተገረፈ።ሆሳዕና ብለው ያነገሱትን ጌታ ይስቀል ይሰቀል ይሰቀል ብለው ፈረዱበት።ፍርደኛውን አርነት ያወጣው ዘንድ እሱ ፍርድን ተቀበለ።በስስት ጥቂት በጥቂት ያሳደገችውን ብቸኛውን ልጇን ለህዝብ ሁሉ ድህነት ለሞት ተላልፎ ሲሰጥ ሞቱን በእንባ አጀበችው።
══════◄✣••✥••✣►══════
እንኳን ለቅዳሜ ስዑር በሰላም አደረሰን

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21
1.6K views₩ōňđĩ€, 20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 06:50:41 አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ " አሉት።
••●◉ ✞ ◉●••
ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን።ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን ሰው ሁን ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው።ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።
••●◉ ✞ ◉●••
ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው። "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል
••●◉ ✞ ◉●••
የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት ይባላል ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን
••●◉ ✞ ◉●••
በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን በፍጹም አይሆንም የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ
••●◉ ✞ ◉●••
አባ ጊዮርጊስ ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣ ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ ይል የለምን ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም።
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን።ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን።ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21
1.9K viewsËfřõñ Ýëđñķūñůâ Mãřýām ፮ ༒ً , 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 06:50:41 በተደጋጋሚ በውስጥ መስመር በመጠየቁ የተለጠፈ
1.3K viewsËfřõñ Ýëđñķūñůâ Mãřýām ፮ ༒ً , 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 15:38:59 ፊርማው የሚጠናቀቀው ነገ የካቲት 20 ቀን 2014 ከለሊቱ 6:00 ነው ስለዚህ ሊጠናቀቅ 23 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ብቻ ይቀረናል። በቀረን ጊዜ ላልሰሙ ወገኖቻችን መረጃውን በማድረስ እንዲሁም ሰምተው ያልፈረሙትን የማስፈረም ስራ ብንሰራ እና ቢያንስ 5 መቶ ሺህ ወገኖቻችን ብቻ 20 ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ማስፈረም ቢችሉ ። የምንፈልገውን ቁጥር በማግኘት ወደ ቀጣዩ ጉዳያችን ከመሄዳችን ባሻገር በሳምንት ጊዜ ውስጥ10 ሚሊዮን ፊርማ በማሰባሰብ የመላው ዓለምን ትኩረት መሳብም ያስችለናል ለዚህ ደግሞ በመላው ዓለም ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችንን እናሳትፍ እያነረዳንዳችን ቢያንስ 20 ሰው ማስፈረም ብንችል አሳካነው ማለት ነው በተለያዩ የአገልግሎት መዋቅሮች በኩል ሲከናወን ደግሞ ከዚህ በነሰ ቁጥር የሚፈፀም ይሆናል። በሉ እስኪ አሁን ኦንላይን ያላችሁት ላልሰሙት እና ሰምተውም ላልፈረሙት ሊንኩን እያጋራን እንዲፈርሙ እናድርግ ታዲያ መፈረማቸውን እየጠየቅን እናረጋግጥ።

https://chng.it/T28XNjKbH7
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21
@Geb19bot @won21
2.2K viewsËfřõñ Ýëđñķūñůâ Mãřýām ፮ ༒ً , 12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 06:33:01
ሰው እንዴት ለጊዜአዊው ዓለም ፣ብዙ ሀብት እየሰበሰበ፣ወደ ዘለዓለም ቤቱ ባዶ እጁን ይሄዳል ሰው እንዴት እንደሚሞት እርግጠኛ ሆኖ እድር እየተመዘገበ፣እንዴት እንደሚሞት አምኖ ንሰሐ አይገባም
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ሰው እንዴት ሞቼ የት እቀበራለሁ ብሎ ከመጨነቅ ይልቅ፣እንዴት ሞቼ የት እገባለሁ ሲኦል ነው ወይስ ገነት ብሎ አይጨነቅም ሰው እንዴት አሟሟቴን አሳምረው ብሎ ለአንድ ቀን ሥነ ሥርዓተ ከመጨነቅ ይልቅ፣አኗኗሬን አሳምረው ብሎ አይጸልይም
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
የማንቂያ ደወል ድምፅ
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21
2.4K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 10:07:20 ከተራ ምንድን ነው

ከተራ "ከበበ" ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ-ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን(ዳስ) ይተክላል፡፡ የምንጭ ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል፣ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
ታቦቱ የጌታችን ምሳሌ ሲኾን፣ ካህናቱ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌ፣ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። ኢያሱ ፫÷፫
••●◉ ✞ ◉●••

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን

══════◄✣••✥••✣►══════
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
══════◄✣••✥••✣►══════

@efr21 @Geb19
@Geb19bot @Geb19
@efr21 @Geb19
2.0K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 14:37:15
1.9K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-11 22:09:47
የማንቂያ ደወል
___________
ነገ 10 ሰዓት አይቀርም
በቦሌ መድሃኒአለም
እርሶም ቢያንስ ለ10 ሰዎች ሼር ያርጉት


ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
2.0K views₩ōňđĩ€ Zēfñōte-Hïwõt ፲፱ ༒ً , edited  19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ