Get Mystery Box with random crypto!

እነሆ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢሏችሁ አትመኑ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና ቢቻላቸውስ | የገኃነም ደጆች አይችሏትም❗️

እነሆ ክርስቶስ ከዚህ አለ ወይም ከዚያ አለ ቢሏችሁ አትመኑ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ እነሆ አስቀድሜ ነገርኳችሁ።በማቴ 24፥24
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁማር 13፥15
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
ወንድሞች ሆይ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።ዕብ 3፥12
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
እንደተማራችሁት በሃይማኖት ጽኑ፣ ልዩ ልዩ ዓይነት በሆኑ እንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፣ በዐመጸኖች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፣ ልጆች ሆይ መጨረሻው ሰዓት ነው የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቋዋሚዎች ተነሥተዋል፣ ስለዚህም የመጨረሻው ሰዓት እንደሆነ እናውቃለን።ቆላ 2፥7 ፣ ዕብ 13፥7 ፣ 2ኛ ጴጥ 3፥6 ፣ 1ዮሐ 2፥18
┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈
በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ ።ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን .......በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል።የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።ማቴዎስ 7፥13-23
══════◄✣••✥••✣►══════
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ። ከምታልቀዋ ከዛሬዋ ቀን እስከማይፈጸም ዘመን ። ከደካማው ልባችን እስከ ጸናው ሰማይ።
ለዘላለሙ አሜን
══════◄✣••✥••✣►══════

@Geb19bot @eotc27
@Geb19bot @efr21