Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ከፈላስፎች💆

የቴሌግራም ቻናል አርማ filsifina_kefelasfoch — ፍልስፍና ከፈላስፎች💆
የቴሌግራም ቻናል አርማ filsifina_kefelasfoch — ፍልስፍና ከፈላስፎች💆
የሰርጥ አድራሻ: @filsifina_kefelasfoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.87K
የሰርጥ መግለጫ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
●👉 በፍልስፍናቸውና፣በመጠቀ አስተሳሰባቸው፣ዓለምን ማስደመምና መሳብ የቻሉ የፍልስፍና ሰዎች ምልከታቸው፣ታሪካቸውና፣የተለያዩ ጉዳዮችን የሚያነሳ ቻናል ከኛ ጋር ስለሆናችሁ እናመሰግናለን...!👈
👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆
👆👆👆👆👆❤❤❤❤👆👆👆

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-23 19:26:13
#ህይወትና_ግምት

ወንደላጤ እያለሁ 'ሳገባና ፍቅረኛ ሲኖረኝ' ባዶነቴ እንደሚሞላ፣ አሁን 'የሚደብረኝና የሚሰለቸኝ' ነገር እንደሚቀር አስብ ነበር፡፡

ከፍቅረኛዬ ጋር ግንኙነት ስጀምር ብቻዬን መሆንን 'ቻዎ' አልኩት...ግን ግን ብቸኝነት ይናፍቀኝ ጀመር! እየተጣሉና እየተኳረፉ መኖር ሰለቸኝ፣ አንገፈገፈኝ!

ባህሪዬ ቁጥብና ጭምት አይነት ስለነበር የማገኛቸዉ ሴቶች ደግሞ ተግባቢና ለፍላፊ አይነት ባህሪይ ያላቸዉ ነበሩ፡ ትርፍ የምለዉን ጊዜ እንኳን ሳይቀር ይዘዉብኝ እንደዚህ ሆኖ መቀጠል ሞት ሆኖ ታየኝ...እንዴት ብዬ ለራሴ ላስብ?

አሁን ተመልሼ የብቸኝነትን ኑሮ እየኖርኩት ነዉ፤ደስተኛ ነኝ፡፡ መጀመሪያ እንደነበረኝ አይነት የብቸኝነት ጊዜ እያሳለፍኩ አይደለም...በራሴ ነገሮችን ስርአት እያስያዝኩ ደስ ብሎኝ አለሁ፡፡

ደስተኛ ያልሆንክበትን ማንነት ሌሎች መጥተዉ ደስተኛ እንዲያደርጉህ አትጠብቅ፡፡ ፍቅረኛህ አንተን ደስተኛ የማድረግ አቅሟ ዝቅተኛ ነዉ፡፡ የቱንም ያህል ብትዋደዱ ከራስህ የመነጨ የደስታ ስሜት ካልፈጠርክ እሷ ልትፈጥርልህ አትችልም፡፡

ስታዝን በራስህ፣ ደስ ሲልህም እንዲሁ በራስህ እያደረክ ካላለማመድከዉ እዉነቴን ነዉ የምልህ ማንም ሊያስደስትህ አይችልም፡፡ እንደዉም ተጨማሪ ራስ ምታት፣ ተጨማሪ ቁርጥማት፣ ተጨማሪ ሆድ ቁርጠት ይሆኑብሃል፡፡

ላንቺም ለእህቴ እዉነቱ አንድ አይነት ነዉ፡፡ብቻዬን ስለሆንኩ ነዉ ያዘንኩት ብለሽ ፍቅር ብትጀምሪ ያ ያሰብሽዉ ሰዉ አይሞላዉም..

እግዜርን በደስታ እንዲሞላሽ እጆችሽን ዘርግተሸ ጠይቂ እንጂ ከፍጡር ለዛዉም 'ዛሬ እብድ ብዬልሽ ልሙት!ብሎ ማታ ደግሞ 'ሰለቸሽኝ' ከሚልሽ ተባእት ደስታን አትጠብቂ፡፡

መጀመሪያ በራስሽ ቆመሽ ፍቅር ብትጀምሪ ያምራል..ግንኙነቱም 'ከህፃናት ኩርፊያ ወደ ጎመራ ፍቅር ያድጋል፣ይለወጣል፣ይጠነክራል ማለት ነዉ፡፡
351 views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 19:43:49 በፍላጎት እንጂ በግፊት አታግቡ!
(“የፍቅር ሕይወት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)፡፡

አንዳንድ ሰዎች ፍቅረኛን ለመያዝና አልፎም ወደትዳር ለመሄድ የሚነሳሱባቸውን የተሳሳተ አመለካከቶች ጠቀስ እናድርግ፡-

1. ሰው ሁሉ ስላገባ?
አንዳንድ ሰዎች በዙሪቸው ያሉ አቻዎቻቸው፣ አብሮ አደጎቻቸውና፣ አንዳንዴም ታናናሽ እህትና ወንድሞቻቸው ተራቸውን እየጠበቁ ትዳር ሲይዙ ሲመለከቱ ይህ ነው የማይባል ስነ-ልቦናዊ ጫና ያድርባቸዋል፡፡ በዚህ ላይ የቤተሰብ ግፊትና የሕብረተሰቡ እረፍት-አሳጪ ሃሳብ ሰንዛሪነት ሰዎቹ ስለትዳር ትርጉም በሚገባ ሳይገነዘቡ በችኮላ በሚገባ ወዳላሰቡበት ግንኙነት ውስጥ በመግባት ትዳርን አደንዲመሰርቱ ግፊትን ያሳድርባቸዋል፡፡ የዚህ አይነቱን ውሳኔ መጨረሻ መገመት አያስቸግርም፡፡

2. የወሲብ ፍላጎትን ለማርካት?
በኋላ በሌላ ክፍላችን እንደምንመከተው ይህ የመነሻ ሃሳብ ትክክለኛ ገጽታ ቢኖረውም አንዳንድ ሰዎች ግን ሌላውን የትዳር ትርጉም ችላ በማለትና ሙሉ ስእሉን ባለመገንዘብ በወሲብና በወሲብብ ላይ ብቻ ያተኮረ መነሻ ሃሳብ ይዘው ለትዳር ይቸኩላሉ፡፡ ይህ ግማሽ ገጽታ ያለው ግንዛቤ ሊያስከትል የሚችለው ቀውስ ግልጽ ከመሆኑ የተነሳእዚህ ጋር መዘርዘር አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡

3. ከጊዜያዊ ሁኔታ ለመገላገል?
ከላይ ከተጠቀሱት የተዛቡ የመነሻ ሃሳቦች በተጨማሪ አንዳንድ ሰዎች ጊዜያዊ ከሆነ ብቸኝነት ለማምለጥ ሲሉ ዘለቄታዊ ትርጉም ወዳለው ትዳር ፈጥነው ይገቡና የብቸኝነት ስሜታቸው ሲሰክን ስለወሰኑት ውሳኔ እንደገና ማሰብ ይጀምራሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከጊዜያዊ የገንዘብ ችግር ለማምለጥና የመሳሰሉት ትንሽ ታግሰው ሊልፏቸው የሚችሉትን ሁኔታዎች ሽሽት ወደ ትዳር ዘልለው የሚገቡ ሰዎች አሉ፡፡

ከእነዚህ ሁኔታዎች አብዛኛዎቹ በትክክለኛና በተረጋጋ ምርጫ ውስጥ የምንጠቀምባቸው አስፈላጊ እውነታዎች ቢሆኑም ወደ አንድ ትዳር የመግቢያ ምክንያታችን እነሱ ላይ ብቻ ሲንጠለጠል መጨረሻውን አደገኛ ያደርገዋል፡፡

https://t.me/filsifina_kefelasfoch
396 views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 17:32:22
ህይወት አዙሪት ናት

ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው።
ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ጥርሱን በረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።

ዘመንም ተምኔታዊ ነው መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም በሉ ይመጣብሀል ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ።

ህይወት አዙሪት ናት፡ መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ነገ ህዝብ ብትበታትን ተሹመህ በህዝብ ላይ ብትሰለጥን ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው።

ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሔድም በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅት ትጨርሳለህ በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ
ህይወት መጀመሪያዋ እና መጨረሻዋ አንድ ነው ርቀህ የሔድክ ቢመስልህም ትልቅ ክብ ሰርተህ ትመለሳለህ።

አለማየሁ ዋሴ እሸቴ
#መርበብት

https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
527 viewsedited  14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 04:17:17
ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን . . .

ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ሌላ መንገድ አለ! ሌላ ሕይወት አለ! ሌላ አቅጣጫ አለ! ሌላ አማራጭ አለ!

• እውነት ነው፣ ተምሬ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር . . . የመማሩን እድል ካላገኘሁ ግን ሕይወትን ውብ የሚያደርጉ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉ፡፡
• እውነት ነው፣ ፍቅረኛ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ትክክለኛ ፍቅረኛ ካላገኘሁ ግን ትክክለኛ ሕይወት የምመራበት ብዙ እድሎች አሉኝ፡፡
• እውነት ነው፣ ትዳሬ በሰላም ቀጥሎ ቢሆንና ባይፈርስ ጥሩ ነበር . . . አንዴ ከሆነና ሁኔታውን በፍጹም ማደስ ካልቻልኩ ግን የተዝረከረከውን ሕይወቴን አፋፍሼ፣ ሰብስቤና እንደገና አደራጅቼ በአዲስ መልኩ ሕይወት ይቀጥላል፡፡
• እውነት ነው፣ የምወደው ስራ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ሁኔታው ያንን ለማግኘት ካልፈቀደልኝ ግን ባለኝና ካለሁበት በመነሳት የማድግበትን መንገድ የመፈለግ መነሳሳቱ አለኝ፡፡

በአጭሩ፣ ሕይወት እኔ እንደምፈልጋት ብትሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ለምን አልሆነም ብዬ ደብቶኝ አልውልም፡፡ ቀና እላለሁ! ብርቱ ሰው ለመሆን እወስናለሁ! ስብር አልልም! አልደካክምም!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
411 views01:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 23:29:22

ውድ የchannale ተከታታዮች በሙሉ #እንኳን_ለቡሄ_አምላክም_ነገረ_መለኮቱን_ጌትነቱን_ለገለጸበት ታላቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብያለሁ.!



https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
393 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 20:10:44
#የጊዜ ትርጉም እና አስፈላጊነት#
.
.
የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ክፍሉን የደገመ ተማሪ ጠይቀው።

የአንድ ወር ዋጋን ማወቅ ከፈለክ ካለወሩ የተወለደን ህፃን የወለደችውን ሴት ጠይቃት።

የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በየ ሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቅው።

የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ የወሳኝ ፈተና ውጤት ነገ ለመውሰድ የሚጠብቀውን ተማሪ ጠይቀው ።

የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኛሞችን ጠይቃቸው ።

የአንድን ደቂቃ ለማወቅ ከፈለክ አውቶቡስ ለትንሽ ያመለጠውን ሰው ጠይቀው።

የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ከአደጋ ለጥቂት የተረፈን ሰው ጠይቀው።

የአንድን ማይክሮ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀው።
.
.
......ዶክተር እዮብ ማሞ

#ፍልስፍና_ከፈላስፎች.!
816 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 15:24:06 Watch "I love u my kitty kat #shorts #dog #cute #cat #fyp" on YouTube
https://youtube.com/shorts/a87wy3hXi98?feature=share


#ፍቅርን_ያለማንም_አስተማሪነት.......በነሱ መማር ይቻላል
604 viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:51:13
...ፍቅር መሸነፍ ነው። ፍቅር መያዝ ነው። ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው። ፍቅር ከምክንያት ውጭ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው። ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጭ መሆን ነው” ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው። ያስፈራል ፍቅር፤ የማይታከሙት ህመም፣ የማይጠገን ቁስል፣ የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል።”

የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን፤ ማፍቀር ራሱ ነው። ካፈቀርሽ በኋላ “እኔ” የምትይው ሁሉ ይጠፋል። ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ። በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።”

ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፤ እጅ መስጠት፣ ወዶ መግባት፣ ከራስ መነጠል፣ መጥፋት፣ በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ። አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል።” ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው። ሰው ስለሆንን ነው። ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን። አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው። አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና ያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ ምን እንደሚመጣ፣ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም። ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጭ ነው”

አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል። ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩት ባለሁበት ሁኔታ፤ ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው። ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ” ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል። ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመሰያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ
ታውቂያለሽ” አላት...

ከ <አለመኖር >

#ፍልስፍና_ከፈላስፎች
663 viewsedited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:50:47
ልክ እንደ ትላንቱ
አጥብቄ ብመኝም መሆን እንዳሻዬ
ይኸው በየቀኑ
ሀገሬን ቢገድለዋት ጠፋኝ መድረሻዬ።

#ፍልስፍና_ከፈላስፎች

https://t.me/filsifina_kefelasfoch
https://t.me/filsifina_kefelasfoch
502 viewsedited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 20:46:47 #በአፍሪካ_ትልቁ_የደሀዎች_መንደር.!

በአፍሪካ ትልቁ የደሀዎች መንደር ያለው የ"Kenya" ዋና ከተማ በሆነችው "Nairobi" ውስጥ "Kibira" የሚባል ቦታ ነው። እዚህ መንደር ውስጥ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ጥቅጥቅ ብለው የድህነት የመጨረሻ ጥጉን እያዩ ይኖራሉ! ሁሌም የሚደንቀኝ ከዚህ መንደር ትንሽ ርቀት ሄድ ስትል የ "United Nations Agency forሸ Human Settlement" ዋና መቀመጫ ቢሮ ይገኛል! ይህ ተቋም የደሓዎችን ማህበራዊ ህይወት ለማሻሻል እና ሰዎች ምቹ መጠለያ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚሰራ ተቋም ነው፣ በየአመቱም በብዙ ሚልዮን ዶላሮች ፈሰስ ይደረጉለታል! ነገር ግን እዛው ከጎኑ ላሉት እንኳን ምንም አላደረገም! እርዳታ ደሓዎችን ይበልጥ ደሓ እያደረገ ነው! የአፍሪካ ሃገራት እድገት የተንቀረፈፈው በዋነኝነት በእርዳታ ምክንያት ነው! ረጂዎቹ ግን ተቃራኒውን እንድናስብ አድርገውናል። አፍሪካ በሙስና ብቻ ወደ 150 ቢልዮን ዶላር በአመት ታጣለች! 20% የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ በጠኔ ምክንያት የሞት አፋፍ ላይ ነው! 31% የሚሆኑ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ አጥተው ቀንጭረዋል! ግማሽ ቢልዮን የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ አሁንም በመብራት እጦት ዳፈና ውስጥ ይኳትናል! 50% የሚሆነው አፍሪካዊ በኮሌራ እና ተቅማጥ የመያዝ እድሉ ሰፊ ነው። አንዲት አፍሪካዊ ሴት ከአሜሪካዊት ሴት ጋር ስትነፃፀር 231 እጥፍ በወሊድ ወቅት የመሞት እድል አላት!  25 ሚልዮኑ አፍሪካዊ የ "HIV" ታማሚ ነው። 600 ሚልዮኑ አፍሪካዊ ማንበብ እና መፅሃፍ የማይችል መሃይም ነው። ያልተረዳነው አፍሪካ የምትሻገረው በእርዳታ ሳይሆን በስራ ፈጠራ እና በካፒታል ነው።  ቻይና 850 ሚልዮን ህዝቧን ከደህነት አረንቋ ያወጣችው በእርዳታ ሳይሆን በራሷ ስራ ነው! በእርዳታ ያደገች/የበለፀገች አህጉር አይደለም ሃገር እንኳን የለችም! የሚገርመው አሜሪካ ከቻይና ገንዘብ ትበደራለች! ከዛ የተበደረችውን ደግሞ ለአፍሪካ በእርዳታ መልክ ትሰጣለች! አሜሪካ ምን ያህል ብታስብልን ነው ባክህ? የአፍሪካ ሃብት የሚመዘበረው በእርዳታ መጋረጃ ነው። ረጂዎቻችን "አፍሪካ እስከመቼ ትረዳ? ከዛስ ምን ትሁን?" የሚል ምንም እቅድ የላቸውም! ስለዚህ የአፍሪካ መሪዎች ለየሃገሮቻቸው የሚሰጠው እርዳታ ቋሚ እና መቼም የማይቆም አድርገው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል! የአፍሪካ መሪዎች የሃገራቸውን ኢኮኖሚ በምን መልኩ ፋይናንስ ማድረግ እንዳለበት አያውቁም! እርዳታ ቋሚ ገቢያቸው እንደሆነ አድርገው እንዲያስቡ ተደርገዋል! ለምሳሌ አውሮፓም ሆነች አሜሪካ ለአፍሪካ ሃገራት እርዳታ ማድረግ የሚያቆሙበትን ቁርጥ ያለ የግዜ ገደብ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል! የአፍሪካ ሃገራት ከቀጣዮቹ አምስት አመታት በኋላ ምንም አይነት እርዳታ እንደማያገኙ ቢነገራቸው አህጉሪቷ ታድግ ነበር! ስራ ፈጠራ እና ኢንቨስትመት ላይ ታተኩር ነበር! ሃገራቱም እርዳታ ስለማያገኙ መውጫ እቅድ(Exit plan) አርቅቀው በግድ ይተገብሩ ነበር! ረጂዎቻችን ግን ይህንን መቼም አያደርጉም! መሪዎቻችንም ስለዚህ አያስቡም! "....10% አድጋችኃል! 12% አድጋችኃል!..." እያሉ ተቋሞቻቸውም አፍሪካን መሸወዳቸውን አያቆሙም!...." ትላለች "Dr. Dambisa Moyo"!

ጌታዬ! ከዚህ በላይ ከቀደድኩ ሙሉ መፅሃፉን መጨረሴ ነው! መፅሃፉን የማንበብ ፍላጎት ካላችሁ በውስጥ መስመር ለማቀበል ዝግጁ ነኝ! አንብብላት አትጎዳም ጌታዬ!

በመጨረሻም!

መፅሃፉን ካሳተመች በኃላ "Oxford" እያለች "Economics" ያስተማራት ያ ነጭ ሼባ ፕሮፌሰር እንዳብጠለጠላት ስትሰማ እንዲህ ነበር ያለችው!

"....ሃገራት የሚያድጉት በስራ ፈጠራ፣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና ገበያን መሰረት ባደረገ ፖሊሲ እንጂ በነጮች ምፅዋት፣ እርዳታ እና ችሮታ እንዳልሆነ ያስተማርከኝ አንተው መሆንህን ዘነጋኸው ወይ ውድ ፕሮፌሰር?...."

ጌታዬ! ልክ መፅሃፉ ሲጀምር እንዲህ ይላል!

".....የተከበራችሁ የአውሮፓ መሪዎች እና ባለስልጣናት! አፍሪካ ውስጥ በጣም እየተሰቃየን ነው! እባካችሁ እርዱን! አፍሪካ ችግረኛ አህጉር ናት! ምንም መብት የለንም! ጦርነት እና ህመም አሰቃይቶናል! የሚላስ የሚቀመስ ነገር የለንም!... እናንተ ጋር መጥተን መማርና እንደ እናንተ መሆን አጥብቀን እንፈልጋለን!...."

ይህ ደብዳቤ የተገኘው ሁለት ህይወታቸው ያለፈ የ "ጊኒ" ዜግነት ያላቸው መጣቶች ኪስ ውስጥ ሲሆን ህይወታቸው ያለፈው ደግሞ ከ "ጊኒ" ተነስቶ ወደ አውሮፓ የሚሄድ የአንድ አውሮፕላንን ጎማ ተንጠልጥለው ወደ አውሮፓ ለመሄድ ሲሞክሩ በመውደቃቸው ሳብያ ነው!

እና አያሳፍርም ወይ?

መልካም ምሽትን ተመኘሁላችሁ

#ፍልስፍና_ከፈላስፎች
602 views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ