Get Mystery Box with random crypto!

#በአፍሪካ_ትልቁ_የደሀዎች_መንደር.! በአፍሪካ ትልቁ የደሀዎች መንደር ያለው የ'Kenya' ዋና | ፍልስፍና ከፈላስፎች💆

#በአፍሪካ_ትልቁ_የደሀዎች_መንደር.!

በአፍሪካ ትልቁ የደሀዎች መንደር ያለው የ"Kenya" ዋና ከተማ በሆነችው "Nairobi" ውስጥ "Kibira" የሚባል ቦታ ነው። እዚህ መንደር ውስጥ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ጥቅጥቅ ብለው የድህነት የመጨረሻ ጥጉን እያዩ ይኖራሉ! ሁሌም የሚደንቀኝ ከዚህ መንደር ትንሽ ርቀት ሄድ ስትል የ "United Nations Agency forሸ Human Settlement" ዋና መቀመጫ ቢሮ ይገኛል! ይህ ተቋም የደሓዎችን ማህበራዊ ህይወት ለማሻሻል እና ሰዎች ምቹ መጠለያ እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚሰራ ተቋም ነው፣ በየአመቱም በብዙ ሚልዮን ዶላሮች ፈሰስ ይደረጉለታል! ነገር ግን እዛው ከጎኑ ላሉት እንኳን ምንም አላደረገም! እርዳታ ደሓዎችን ይበልጥ ደሓ እያደረገ ነው! የአፍሪካ ሃገራት እድገት የተንቀረፈፈው በዋነኝነት በእርዳታ ምክንያት ነው! ረጂዎቹ ግን ተቃራኒውን እንድናስብ አድርገውናል። አፍሪካ በሙስና ብቻ ወደ 150 ቢልዮን ዶላር በአመት ታጣለች! 20% የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ በጠኔ ምክንያት የሞት አፋፍ ላይ ነው! 31% የሚሆኑ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ህፃናት የተመጣጠነ ምግብ አጥተው ቀንጭረዋል! ግማሽ ቢልዮን የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ አሁንም በመብራት እጦት ዳፈና ውስጥ ይኳትናል! 50% የሚሆነው አፍሪካዊ በኮሌራ እና ተቅማጥ የመያዝ እድሉ ሰፊ ነው። አንዲት አፍሪካዊ ሴት ከአሜሪካዊት ሴት ጋር ስትነፃፀር 231 እጥፍ በወሊድ ወቅት የመሞት እድል አላት!  25 ሚልዮኑ አፍሪካዊ የ "HIV" ታማሚ ነው። 600 ሚልዮኑ አፍሪካዊ ማንበብ እና መፅሃፍ የማይችል መሃይም ነው። ያልተረዳነው አፍሪካ የምትሻገረው በእርዳታ ሳይሆን በስራ ፈጠራ እና በካፒታል ነው።  ቻይና 850 ሚልዮን ህዝቧን ከደህነት አረንቋ ያወጣችው በእርዳታ ሳይሆን በራሷ ስራ ነው! በእርዳታ ያደገች/የበለፀገች አህጉር አይደለም ሃገር እንኳን የለችም! የሚገርመው አሜሪካ ከቻይና ገንዘብ ትበደራለች! ከዛ የተበደረችውን ደግሞ ለአፍሪካ በእርዳታ መልክ ትሰጣለች! አሜሪካ ምን ያህል ብታስብልን ነው ባክህ? የአፍሪካ ሃብት የሚመዘበረው በእርዳታ መጋረጃ ነው። ረጂዎቻችን "አፍሪካ እስከመቼ ትረዳ? ከዛስ ምን ትሁን?" የሚል ምንም እቅድ የላቸውም! ስለዚህ የአፍሪካ መሪዎች ለየሃገሮቻቸው የሚሰጠው እርዳታ ቋሚ እና መቼም የማይቆም አድርገው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል! የአፍሪካ መሪዎች የሃገራቸውን ኢኮኖሚ በምን መልኩ ፋይናንስ ማድረግ እንዳለበት አያውቁም! እርዳታ ቋሚ ገቢያቸው እንደሆነ አድርገው እንዲያስቡ ተደርገዋል! ለምሳሌ አውሮፓም ሆነች አሜሪካ ለአፍሪካ ሃገራት እርዳታ ማድረግ የሚያቆሙበትን ቁርጥ ያለ የግዜ ገደብ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል! የአፍሪካ ሃገራት ከቀጣዮቹ አምስት አመታት በኋላ ምንም አይነት እርዳታ እንደማያገኙ ቢነገራቸው አህጉሪቷ ታድግ ነበር! ስራ ፈጠራ እና ኢንቨስትመት ላይ ታተኩር ነበር! ሃገራቱም እርዳታ ስለማያገኙ መውጫ እቅድ(Exit plan) አርቅቀው በግድ ይተገብሩ ነበር! ረጂዎቻችን ግን ይህንን መቼም አያደርጉም! መሪዎቻችንም ስለዚህ አያስቡም! "....10% አድጋችኃል! 12% አድጋችኃል!..." እያሉ ተቋሞቻቸውም አፍሪካን መሸወዳቸውን አያቆሙም!...." ትላለች "Dr. Dambisa Moyo"!

ጌታዬ! ከዚህ በላይ ከቀደድኩ ሙሉ መፅሃፉን መጨረሴ ነው! መፅሃፉን የማንበብ ፍላጎት ካላችሁ በውስጥ መስመር ለማቀበል ዝግጁ ነኝ! አንብብላት አትጎዳም ጌታዬ!

በመጨረሻም!

መፅሃፉን ካሳተመች በኃላ "Oxford" እያለች "Economics" ያስተማራት ያ ነጭ ሼባ ፕሮፌሰር እንዳብጠለጠላት ስትሰማ እንዲህ ነበር ያለችው!

"....ሃገራት የሚያድጉት በስራ ፈጠራ፣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና ገበያን መሰረት ባደረገ ፖሊሲ እንጂ በነጮች ምፅዋት፣ እርዳታ እና ችሮታ እንዳልሆነ ያስተማርከኝ አንተው መሆንህን ዘነጋኸው ወይ ውድ ፕሮፌሰር?...."

ጌታዬ! ልክ መፅሃፉ ሲጀምር እንዲህ ይላል!

".....የተከበራችሁ የአውሮፓ መሪዎች እና ባለስልጣናት! አፍሪካ ውስጥ በጣም እየተሰቃየን ነው! እባካችሁ እርዱን! አፍሪካ ችግረኛ አህጉር ናት! ምንም መብት የለንም! ጦርነት እና ህመም አሰቃይቶናል! የሚላስ የሚቀመስ ነገር የለንም!... እናንተ ጋር መጥተን መማርና እንደ እናንተ መሆን አጥብቀን እንፈልጋለን!...."

ይህ ደብዳቤ የተገኘው ሁለት ህይወታቸው ያለፈ የ "ጊኒ" ዜግነት ያላቸው መጣቶች ኪስ ውስጥ ሲሆን ህይወታቸው ያለፈው ደግሞ ከ "ጊኒ" ተነስቶ ወደ አውሮፓ የሚሄድ የአንድ አውሮፕላንን ጎማ ተንጠልጥለው ወደ አውሮፓ ለመሄድ ሲሞክሩ በመውደቃቸው ሳብያ ነው!

እና አያሳፍርም ወይ?

መልካም ምሽትን ተመኘሁላችሁ

#ፍልስፍና_ከፈላስፎች