Get Mystery Box with random crypto!

#የጊዜ ትርጉም እና አስፈላጊነት# . . የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ክፍሉን የደገመ ተማሪ | ፍልስፍና ከፈላስፎች💆

#የጊዜ ትርጉም እና አስፈላጊነት#
.
.
የአንድን አመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ክፍሉን የደገመ ተማሪ ጠይቀው።

የአንድ ወር ዋጋን ማወቅ ከፈለክ ካለወሩ የተወለደን ህፃን የወለደችውን ሴት ጠይቃት።

የአንድን ሳምንት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በየ ሳምንቱ የሚወጣን ጋዜጣ አሳታሚ ጠይቅው።

የአንድን ቀን ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ የወሳኝ ፈተና ውጤት ነገ ለመውሰድ የሚጠብቀውን ተማሪ ጠይቀው ።

የአንድን ሰአት ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኛሞችን ጠይቃቸው ።

የአንድን ደቂቃ ለማወቅ ከፈለክ አውቶቡስ ለትንሽ ያመለጠውን ሰው ጠይቀው።

የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ ከአደጋ ለጥቂት የተረፈን ሰው ጠይቀው።

የአንድን ማይክሮ ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለክ በኦሎምፒክ ሩጫ ለጥቂት የተቀደመን ሯጭ ጠይቀው።
.
.
......ዶክተር እዮብ ማሞ

#ፍልስፍና_ከፈላስፎች.!