Get Mystery Box with random crypto!

The True Love Family

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewunetegnawfikir — The True Love Family T
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewunetegnawfikir — The True Love Family
የሰርጥ አድራሻ: @ewunetegnawfikir
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.33K
የሰርጥ መግለጫ

💓💨በዚህ መረብ ውስጥ ኢየሱስ ብቻ ይነገራል ይሰበካል💨💓
🌻 ህይወት ለዋጭ
👉ስብከቶች 🙏
👉ትምህርቶች 🙏
👉የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች 🙏
👉ክርስቲያዊ አባባሎች 🙏
👉ዝማሬዎች 🙏
የዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://www.youtube.com/channel/UCSGAYhj6BgS8kXnsF7uyBaQ
#ƒσɾ_αηy_ɕσʍʍεηt
✍ @Ewunetegnawfikirbot ን ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2020-12-05 21:28:27 አስተማሪ ታርክ

ከአሮጌ ህይወት ወደ አድስ ህይወት ለመለወጥ ትዕግስት....

ንስር አሞራ እና ......አንቺ .........አንተ .

ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...

የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...

ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...

ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።
እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?

2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?

የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።

ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።

፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።

፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።

፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡

፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።

፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል።
ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡



ወዳጄ ሆይ:-

ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ...

በቃ! ... ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ...

፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ...

፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ...
••• አስተውል ... •••

ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ...

፩ኛ. ራስህን ከነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ... እዚህ ጋር ከወዳጅም ከጠላትም መራቅ ፍቱን መድሃኒት ነው ... ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል።

፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ።

፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ።

፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ።

፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በዋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል።

ሲጠቃለል ...

አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በዋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል።


Ke maranata channel yetewesede
12.0K viewsBtsit Leulekal, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-05 21:19:14 የመኖሬ ምክንያት ነህ
3.6K viewsBtsit Leulekal, edited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-05 21:18:49 ዝማሬ

3.4K viewsBtsit Leulekal, edited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-05 21:14:20 ሰላም እጅግ የምንወዳችሁ ቤተሰቦቻችን እንዴት አመሻቹ በኢየሱስ ፈቃድ ዛሬ በሰአታችን ተገኝተናል የተለያዩ ፕሮግራሞች አሉን አብራችሁን ቆዩ ።
3.4K viewsBtsit Leulekal, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-02 21:49:21 የተወደዳቹ ቤተሰቦቻችን ለዛሬ የነበረን ኘሮግራም ይሄን ይመስል ነበረ እንደተማራችሁበት እናምናለን ቅዳሜ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ መልካም አዳር ተባረኩ።
3.8K views░▒▓█ yab █▓▒░, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-02 21:47:14 "፤ ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 6: 22)
=======================
ስንሄድ/ስንጓዝ....... መሪ
ስንተኛ............... ጠባቂ
ስንነሳ ................አነጋጋሪ/የሚያናግር
#እውነተኛ_አምላክ_አለንና_ስሙ_ይመስገን።


ይ ላ ሉን

✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯
Ꮖɦɛ Ꮖʀʊɛ ʟօʋɛ ʄǟʍɨʟʏ
✯┄┅┅✿❀ ❀✿┅┅┄✯

Share to your brothers and sisters
Join
@ewunetegnawfikir
3.8K views░▒▓█ yab █▓▒░, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ