Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹ኢትዮ University

የሰርጥ አድራሻ: @ethiouniversity1
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 126.74K
የሰርጥ መግለጫ

Promotion ለምትፈልጉ ....🌀 @Euads🌀
@hilwauniversity
Use this for idea and question @ethiouniversity1bot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 321

2021-03-04 08:58:16 ለ Internship ተማሪዎች

በርካታ ተማሪዎች በውስጥ መስመር የአፓረንት ብር ተቀንሶ እንደተሰጣቸው ገልፀውልናል ፤ ከደረሱን መረጃዎች እንደተመለከትነው የተቀነሰው የብር መጠን እንደ ዩንቨርሲቲዎቹ ይለያያል ።

በዚህ ዓመት አፓረንት የወጣቹህ ተማሪዎች መረጃ በማሰባሰብ ላይ ስለምንገኝ ለአፓረንት የተሰጣችሁን የብር መጠን @ethiouniversity1bot ላይ ንገሩን።

የተቀነሰባችሁን የብር መጠን ለሚመለከታቸው የበላይ አካላት ለማሳወቅ ስለምንፈልግ መረጃውን በትክክል ይግለፁልን።

አንዳንድ ዩንቨርሲቲዎች ላይ ደግሞ የተጨመረ እንዳለም ሰምተናል የተጨመረላቹህ ወይም እስከ ዛሬ ከነበረው ያልተቀነሰባቹህ ተማሪዎችም መረጃው በጣም ስለሚጠቅመን ፃፉልን


ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
1.3K views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-04 07:21:53 Grade 12

Admission card ለሁሉም ተማሪዎች አርብ(የካቲት 26) ይሰጣል ። ስለዚህ ሁሉም ተማሪ በየ ትምህርት ቤቱ ቀርቦ መውሰድ ይኖርበታል ።

ሌላው ደግሞ ነገ ማለትም አርብ ለሁሉም ተማሪ #Orientation (ስለ ፈተናው ) ገለፃ የሚደረግበት ቀን ነው።

ቅደሜ ና እሁድ
ተማሪዎች ስነ ልቦናችሁን ለፈተናው ዝግጁ ማድረግ

ለፈተናው የሚያስፈልጋችሁን Material ( Uniform, pencil, rubber, sharpener ) ማዘጋጀት

ይህ ሁለቱ ቀን ፈተናው ባይወጣም ወጥቷል በማለት ተማሪዎችን ለመረበሽ (Business መስራት) የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ ተጠንቀቁ።


ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
1.1K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-04 07:00:25 በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!

በዛሬ ፅሁፍ ላይ ተማሪዎች መጪውን የፈተና ወቅት በተረጋጋ ሁኔታ እዲጀምሩ ለማስቻል ሲሆን በዚህ ጊዜያት ሊገጥማቸው የሚችለውን ውጥረት ለመቆጣጠር እገዛ የሚያረጉ የተወሰኑ ነጥቦች በዝርዝር ቀርበዋል። ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል። ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ። ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ:

• አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።

• በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ።

• የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ።

• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት። እነዚህ ዋና ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው። ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤
ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ -

• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።

• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ። እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።

• ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር መሰናክል ይፈጥራል። ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።

• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።

• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

• ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።

• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።

• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

• በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።

ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ "አሁን ደህና ነኝ" ፥ "ጥሩ ሆኛለሁ " ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መጀመር።

• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ •
በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን ፈተናውን መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት።
ለሁሉም ተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ!

#Addis express media
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
524 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 19:07:32 Haramaya University

ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሆን መረጃ አሪፍ በሚባል መልኩ

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
@ethiouniversity1bot

Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiostudent1
@ethiostudent1
@ethiostudent1
╚═══════════╝
361 views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 18:50:35 ማስታወቂያ
#AmboUniversity

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች በተከታታይ ትምህርት መረሃ-ግብር በአምቦ ዋና ግቢ፣ በአምቦ ሃጫሉ ሁንዴሣ ካምፖስ፣ በጉደር ማሞ መዘምር ካምፖስ እና በወሊሶ ካምፖስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የመግቢያ መስፈርት
በ2011ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ትምህርት ላጠናቀቁ በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንዶች 176 ለሴቶች 166፣ በማህበራዊ ሣይንስ ለወንዶች 174 ለሴቶች 164፣ ወይም በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ድግሪ ያለው/ያላት ሆኖ የትምህርት መስክ ቀይሮ መማር የሚፈልግ/የምትፈልግ፡፡
የማመልከቻ ቀንና ቦታ
ከየካቲት 26 እስከ መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት ካምፖሶች ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
ማ ሳ ሰ ቢ ያ
1. ትምህርት የሚሠጠው ከሰኞ እስከ አርብ ይሆናል፡፡
2. በየትኛዉም የትምህርት ዓይነት ገብቶ መማር የሚፈልግ የ1ኛ ዓመት የጋራ ኮርሶችን (Common Courses) መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡
3. ፕሮግራሞች የሚከፈቱት የሚፈለገዉ ዝቅተኛዉ የተማሪ ቁጥር ሲገኝ ብቻ ነዉ፡፡
4. ለማመልከቻ የማይመለስ ብር 50 የሚከፈል ሲሆን የሴሚስተር ክፍያ አንድ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ይፈጸማል፡፡
5. ክፍያ በECTS ሆኖ ለማኀበራዊ ሣይንስ 50 ብር በECTS፣ ለተፈጥሮ ሣይንስና ለግብርና ዘርፍ 70ብር በECTS፣ ለቴክኖሎጂ ዘርፍ 80ብር በECTS ነው፡፡

 ተጨማር መረጃ በስልክ ቁጥር +251118765860 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

@AUSUE
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
@ethiouniversity1bot

Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiostudent1
@ethiostudent1
@ethiostudent1
╚═══════════╝
1.1K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 17:05:18 #Textile የሚሰጡ ዩንቨርሲቲዎችን ዝርዝር ለጠየቃችሁን

Arbamich Universitiy
Axum Universitiy
DireDawa Universitiy
Wachamo Universitiy
Bahirdar Universitiy
Wollo University
Hawassa Universitiy
Wolkite Universitiy

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
@ethiouniversity1bot

Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiostudent1
@ethiostudent1
@ethiostudent1
╚═══════════╝
841 viewsedited  14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 16:57:32 ሜዲስን የሚሰጡ ግቢዎችን ዝርዝር ለጠየቃችሁኝ የ#12ኛ ክፍል ተማሪዎች Arbamich Universitiy Jigjiga Universitiy Adis Ababa University Welikite University Wolayta Sodo Universitiy Wachamo Universitiy Mizan Tepi Universitiy Selale Universitiy Arsi Universitiy Wollega Universitiy…
1.1K views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 16:53:42 #ONLY_FOR_GRADE12

12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ለሆናችሁ ብቻ የሚሆን ግሩፕ ተዘጋጅቷል። በዚህ ግሩፕ ላይ የሚገቡት ሰዎች በኛ እውቅና ብቻ ይሆናል።

የግሩፑ አላማ
ተማሪዎች ለፈተና የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሳወቅ
ፈተናው እንደ 2011 ተሰርቆ የሚወጣ ሁሉም ተማሪ እንድያውቅ ማድረግ

ፊልድ ና ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡ ምን ላይ Consider መሆን እንዳላቸው መነጋገር

የተለያዩ ጥያቄዎችን እስከፈተናው ቀን መስራት

ዩኒቨርስቲ ስገቡ ደግሞ የተለያ ድጋፍ ይሰጣቸዋል ።

የግሩፑ አላማ ይሄ ብቻ አይደለም ተመዝግባችሁ የኛ አባል በመሆን ተጠቃሚ ሁኑ እንላለን ።

ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ነገሮች

ሙሉ ስም፦

ስ.ቁ :-

Stream ፦ SOCIAL OR NATURAL

የሚኖርበት ሀገር :-

የሚማርበት ትምህርት ቤት፦


ከላይ ያሉትን መስፈርቶች በዚኛው @grade12Registrationbot ቦት ላይ ስትልኩ ወደ ግሩፑ እናስገባችኋለን ። ወደ ግሩፑ ማስገባት የሚንችለው እኛ ብቻ ስለሆንን የግሩፑን አላማ ለመጠበቅ ያስችለናል።

ይሄ ግሩፕ በተለየ መልኩ ስለሆነ Control የሚደረገው ምንም አይነት ስጋት አይግባችሁ።

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  @ethiouniversity1bot

            Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
@ethiouniversity1 
╚═══════════╝
1.2K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 16:40:15 ሜዲስን የሚሰጡ ግቢዎችን ዝርዝር ለጠየቃችሁኝ የ#12ኛ ክፍል ተማሪዎች

Arbamich Universitiy
Jigjiga Universitiy
Adis Ababa University
Welikite University
Wolayta Sodo Universitiy
Wachamo Universitiy
Mizan Tepi Universitiy
Selale Universitiy
Arsi Universitiy
Wollega Universitiy
Jimma Universitiy
Hremaya Universitiy
Wollo University
Debre Tabor Universitiy
Bahirdar Universitiy
Gonder Universitiy
Adigrat Universitiy
Mekelle Universitiy

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
@ethiouniversity1bot

Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiostudent1
@ethiostudent1
@ethiostudent1
╚═══════════╝
620 views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 16:20:33 የ12ኛ ክፍል ፈተና ወረቀት እስከ አርብ ድረስ ተጓጉዞ ይጠናቀቃል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከየካቲት 29 ቀን 2013 ጀምሮ የሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወረቀት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እስከ መጪዉ አርብ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።

የፈተናዎች ኤጀንሲ ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር ባደረገዉ ስምምነት መሰረት ፈተናዎቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተጓጓዙ መሆናቸዉን የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ቱሬ ተናግረዋል፡፡

በጥብቅ ቁጥጥር በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ አጃቢነት በተቀመጠዉ አቅጣጫ እና የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተጓጓዘ ነዉ ብለዋል፡፡

አያይዘዉም ፈተናዎቹ ወደ ክልል ከተሞች ሲደርሱ የየክልሎቹ ፖሊስ እና ልዩ ሀይል ጥብቅ ቁጥጥር እና እጀባ አድርገዉ ወደ ዞኖች እንደሚያደርሱም ተናግረዋል፡፡

እስካሁን እየተደረገ ያለዉ የማጓጓዝ ሂደትም ሰላማዊ ነዉ ፤ ምንም አይነት ችግር አልገጠመም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የጸጥታ ስጋት አለባቸዉ የተባሉ ቦታዎች ላይም ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ በመከላካያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ታጅቦ እንደሚጓጓዝ ገልጸዋል፡፡

በመላዉ ሀገሪቱ ፈተናዉ እስከ መጪዉ አርብ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ ዶክትር ዲላሞ ማረጋገጣቸውን አሃዱ ሬድዮ ጣቢያ 94.3 (Ahadu FM RADIO) ዘግቧል።


ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
@ethiouniversity1bot

Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiostudent1
@ethiostudent1
@ethiostudent1
╚═══════════╝
1.2K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ