2021-03-04 15:05:19
የ እንተርንሺፕ ብርን አስመልክቶ
የ Apparent ክፍያ በአጠቃላይ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ተመሳሳይ እንደ ነበር ይታወቃል ። በሁሉም ዩኒቨርስቲ ለ #Internship የሚሰጠው ክፍያ 7800 ነበር።
ከዚህ በፊት በተለያዩ መድረኮች ላይ ይሄ ገንዘብ በቂ እንዳልሆነ ና በየ አመቱ የኑሮ ውድነት እየጨመረ መምጠቱን አስመለክቶ በየ አመቱ ቅሬታ እያቀረቡ እንደነበር ተነግሮናል። ይህ ገንዘብ ከተወሰነ minimum 6 አመት አልፎታል። አሁንም ግን እዛው ነው። ለምን ???
የዘንድሮ ደግሞ በጣም የተለያ ነው። በኮሮና ምክንያት 4'ት ወር የነበረው እንተርንሺፕ ወደ 2 ወር ተቀይሯል። ይሄንን በማስመልከት የ #Internship_Cost በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተለያይቷል።
ለምሳሌ:- አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ =7800 ብር
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ =3900 ብር
ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ =5525 ብር
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ =7800 ብር
መቱ ዩኒቨርስቲ =3900 ብር
እንደሚታዩት በሁሉም ዩኒቨርስቲ የብሩ መጠን በጣም የተለያየ ነው። ይህ ደግሞ የሚያሳያው ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው ውሳኔ ብሩን እንደቀነሱና ከለይ በ #Moshe በኩል ምንም አቅጣጫ እንዳልተቀመጠ ያሳያል።
ከዚህ በፊት የነበረው ብር እራሱ አይበቃም እየተባለ እንዴት ይቀነሳል ???
እስቲ የአንድን ተማሪ በስሌት እንስራ
ለምሳሌ አንድ ተማሪ 3900 ብር ለ 2 ወር ብሎ ተቀበለ።
ለ 1 ወር 7800/2=1950 ብር።
በ 1950 ብር ለምሳሌ ይሄ ልጅ ሀዋሳ ላይ apparent ብወጣ
1) የ ቤት ክራይ ለ 1 ወር == 1200 ብር
2) ለምግብ ፦ ቁርስ 10 ብር ==10×30=300
፦ ምሳ 1 ምግብ 25 ብር=25×30=750
፦ እራት 1 ምግብ 25 ብር ==25×30=750
ቶታል የምግብ ብቻ ለ 1 ወር =300+750+750 =1800 ብር
ለ 1 ወር የቤት ክራይ + የምግብ ==1200+ 1800 ==4000ብር ነው
አስቡት ሌሎች ነገሮችን አላከታትንም። ለምሳሌ ታክሲ ሻይ እንኳን የለም። እና እንዴት ???
እና እንዴት ተደርጎ ለ 1 ወር =1950 ለተማሪ ይበቃል?? (4000-1950=2100) ለምግብ ና ለቤት ክራይ ብቻ እንኳን እንድበቃው 2100 ብር ከራሱ መጨመር አለበት ። አረ ይሄ ነገር ይታሰብበት
በተለይ ዘንድሮ ሁሉም ነገር ጨምሯል። ኑሮ ተወዷል። ሁሉ ነገር በጨመረበት ጊዜ የ Apparent ብር ለምን ይቀነሳል ???
ለተማሪዎቻቸው በማሳብ ሙሉ ክፍያ የፈፀሙትን ግቢዎች እያመሰግን ሌሎች ግቢዎች ላይ ያለው አሰራር ግን እንድቀየር ጥሪ እናደርጋለን ።
በሁሉም ከፍተኛ የመንግስት ተቋም ላይ ያለው አሰራር ተመሳሳይ እንድሆን በ #Moshe በኩል አቅጣጫ ቢቀመጥ እንላለን ።
Abdi ነበርኩ ከኢትዮ-ዩኒቨርስቲ
እስቲ በዚህ ላይ የተሰማችሁን ፃፉልኝ
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
@ethiouniversity1bot
Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1
@ethiouniversity1
@ethiouniversity1
╚═══════════╝
815 views12:05