Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Muslim Network

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianmuslimnetwork — Ethiopian Muslim Network E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianmuslimnetwork — Ethiopian Muslim Network
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianmuslimnetwork
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.09K
የሰርጥ መግለጫ

ስህተት ላይ አይቶህ
ከማይመክርህ
⇨ ተቸግረህ አይቶህ
ከማይረዳህ
⇨ ተዘናግተህ አይቶህ
ከማያስታውስህ ጓደኛ
ምንም ኸይር አትጠብቅ
https://t.me/joinchat/AAAAAEiwq-sMQEIRM7VWqg

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 13:33:27
አምላካችን አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ

ورحمتي وسعت كل شيء " ..

" እዝነቴ ሁሉን ነገር ሰፋች ...." ይለናል።

እዝነቱ ሲበዛ ሰፊ ነው።
የቱን ያህል ብታጠፉም አትፍሩ፣ አትሸበሩ፣
በእዝነቱ ዉስጥ አልካተትም፣ ችሮታውም አይደርሠኝም፣ ምህረቱም አይጎበኘኝም፣ ይቅርታውም አይተርፈኝም ብላችሁ አትስጉ።

ላ ወላሂ!
በፍጹም ስጋት አይግባችሁ። ..
እዝነቱ ይደርሰናል፣
ችሮታው ያካብበናል፣
ይቅርታውም ይተርፈናል፣

ኢንሻአላህ! !
218 views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:34:20 ነቢዩ(ሰዐወ) ልብሱ የቆሸሸን ሰው ባዩ ጊዜ "ይህ ሰው ልብሱን የሚያጥብበት ውኋ አጥቶ ነው እንዴ?!" በማለት ሁኔታውን አውግዘዋል።

ጸጉሩ የተንጨባረረ ሰው ባዩ ጊዜም
"ይህ ሰው ጸጉሩን የሚያስተካክልበት (ቅባትና ማበጠሪያ) አጥቶ ነው እንዴ?!" ብለዋል። አቡ ዳውድ 4062።

ኢስላም ውስጥን በዒባዳና በተውበት፣ ውጭን በውሃና በልብስ እንድናሳምር ያዛል። ጁሙዓህ ቀን ላይ ደግሞ ገላን መታጠብ፣ ንጹህ ልብስ መልበስና ለወንዶች ሽቶ መቀባት ይበልጥ ይወደዳል፤ ትልቅ ምንዳም ያስገኛል።
ይህም በትክክለኛ ሐዲሥ ከነቢዩ ተነግሯል።
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
ዛዱል-መዓድ
225 views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:45:56

513 views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 14:13:59 ሦስት ነገሮች ያለ ቀጠሮ ነው የሚመጡት። ሲሳይ፣ ሞት፣ እና ቀደር።

ሲሳይህን ሰማይ ይሁን ምድር አንተ ቦታዉን አታውቀዉም፤ እሱ ግን ያለህበት አይጠፋዉምና ድንገት ከተፍ ሊል ይችላል። አንተ ግን ተስፋ አትቁረጥ። ይመጣል ብለህ ማሰብ ነው።

የሞት ቀንህ አልተነገረህም ፤ መለከል መውት ሳታስበው ድንገት ደርሶ ሊይዝህ ይችላል ። ጣጣህን ጨርሰህ ዝግጁ ሆነህ መጠበቅ ነው።

ቀደር - በቀን ይሁን በማታ ዉስጥ አላህ ምን እንደወሰንልህ አታውቅም ፤ ድንገት ያላሰብከው ነገር ሊፈጠር ይችላል ። እሱ ሁሌም ሥራ ላይ ነው። ጥሩ ይሁን መጥፎ እሱ የለቀቀልህን መውደድ ነው። ለዚህም ሁሌ ዝግጁ ሁን።
መልካም ጁምዓ።

https://t.me/EthiopianMuslimNetwork
744 viewsedited  11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 06:02:58
538 views03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 06:02:00 «አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»
482 views03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 18:33:33 «የዐሹራእን ፆም የተመለከቱ የተወሰኑ ማስታዎሻዎች

የዐሹራእ ፆም የሚባለው እንደ ሒጅራ አቆጣጣር የመጀመሪያው የሙሐረም ወር በገባ በአስረኛው ቀን የሚፆም ፆም ነው።
ይህ ፆም እጅግ ከተጠኑ የሱና ፆሞች መካከል ከዋናዎቹ ነው።

وعن أبي قتادة -رضي الله عنه-، أنّ النّبي -صلّى الله عليه وسلّم- قال:
( صيامُ يومِ عاشوراء، أحتسب على اللَّه أنْ يُكَفِّرَ السّنة التي قبله ).
[أخرجه مسلم]

ከአቡ ቀታዳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዙ ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)
"የዓሹራእ ቀን ፆም ከሱ በፊት የነበረውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።

【ሙስሊም ዘግበውታል】

ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ)
ሰለ ዐሹራእ ፆም ተጠይቀው እንዲህ አሉ :-
" ነብዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሌሎች ቀኖች አሰበልጠው የሚፆሙበትን ቀን ሲጠባበቁ ከዚህ ቀን ውጪ አላውቅም (የዐሹራእን ቀን ማለቱ ነው።) ወርን ሲጠባበቁ አላየሁም የዚህን ወር ያክል (የረመዳን ወር ማለቱ ነው።)
【ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል】

የዐሹራእ ቀን የሚባለው የሙሐረም 10 ኛው ቀን ነው።
የሙሐረምን 10 ኛውን ቀን በፆም ማሳለፍ ከላይ በሐዲሡ ላይ እንዳየነው ያለፈውን የአንድ አመት ወንጅል ያስምራል

ለሙስሊሞች እሄን ቀን በመፆም እራሳቸውን፣ልጆቻቸውን፣ቤተሰቦቻቸውንና ማሀበረሰባቸውን ሊያነሳሱ ይገባቸዋል።

ማሳሰቢያ:- ያለፈውን የአመት ወንጀል ያስምራል ማለት ትንንሹን ወንጀል ነው እንጅ ትልልቁን ሀጢአት አይደለም ትልቅ ወንጀል ዝሙት፣ህሜት፣ነገረኝነት፣ሪባ እና መሰል ትልልቅ ወንጀሎች መስፈርቱን ያሟላ እራሱን የቻለ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።

በዚህ ቀን ወደአላህ ልንመለስ ካለፈው ወንጀላችን በአጠቃላይ ከትልቁም ከትንሹም በመፀፀት እውንተኛ ተውበትን ልንቶብት ይገባል። ተውበትን አላህ በማንኛውም ጊዜ ቢቀበልም በእንደዚህ ብልጫ ባላቸው ጊዜዎች ከሌላው በተለዬ ጊዜ ይቀበላል። በተለይ እኛ እንደሂጅራ አቆጣጠር አድስ አመትን እየጀመርን ስለሆነ ካለፈው ጥፋታችን በመመለስ በተረፈው በመስተካከል ወደአላህ ልንመለስ ይገባናል።

የዐሹራእ ፆም ምክኒያት:-

የዐሹራእን ቀን መፆም ሱና ሁኖ የተደነገገው አሏህ ሙሳንና ህዝቦቾዎን ከፊርዐውን ሰላም ያወጣበት ቀን እንዲሁም ፊርዐውንና ሰራዊቱን ያጠፋበት ቀን ስለሆነ አላህን ለማመስገን ነው።
ለዚህም ተብሉ ሙሳ(ዐለይሂ ሰላም) ይህን ቀን ፁመውታል አይሁዶችም ሙሳን ተከትለው ፁመውታል።እኛ ሙስሊሞች ሙሳን በመከተልና በሙሳ ሰላም መውጣት በጠላታቸው መጥፋት በመደሰት ከአይሁዶች የበለጠ የተገባን ነን

ከላይ የጠቀስኩት የዐሹራእ ፆም ምክንያት በዚህ ሐዲሥ ተገልፇል:-

عن ابن عباس ((قَدِمَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- المَدِينَةَ فَرَأَى الْيَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَقَالَ مَا هَذَا؟ قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللَّهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ فَصَامَهُ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ)). 【صحيح البخاري】

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ:–
"ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በገቡ ጊዜ አይሁዶች የዐሹራእን ቀን ሲፆሙ አዩዋቸው ነቢዩም (ለአይሁዶች) "ይህ (የምትፆሙት) ምንድነው?" አሉዋቸው ይህ ምርጥ ቀን ነው ይህ ቀን አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው ሰላም ያወጣበት ቀን ነው። ስለዚህ ሙሳ ፆሞታል። አሉ ነቢዩም "እኔ ለሙሳ ከናንተ የበለጠ የቀረብኩኝ(የተገባሁኝ) ነኝ ብለው ፆሙት እንዲፆምም አዘዙ።"
【ቡኻሪ ዘግበውታል】

ከአስረኛው ቀን በስተፊት ያለውን ማለት የዘጠነኛውን ቀን አብሮ መፆም ይወደዳል

ኢብኑ ዐባስ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ:-
"ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን በፆሞና እንዲፆምም ባዘዙ ጊዜ (ሱሐቦች) የአላህ መልእክተኛ ሆይ እርሱኮ አይሆዶችና ነሷራዎች የሚያከብሮት ቀን ነው አሏቸው። ነቢዩም (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) «አሏህ ካለ በቀጣይ አመት የዘጠነኛውን ቀን እንፆማለን» አሉ (ኢብኑ ዐባስ) "የቀጣዩ አመት አልመጣም ነቢዩ(አለሂሶላቱ ወሰላም) የሞቱ ቢሆን እንጅ" አለ
【ሙስሊም ዘግበውታል】
ስለዚህ ለዚህ ሐዲሥ ሲባል ዘጠነኛውን ቀን ከአስረኛው ጋር አብሮ መፆም ይወደዳል

« አስረኛውን ብቻ በፆም መለየት ከአይሁድ ጋር እንዳይመሳሰል ከሙሐረም ዘጠኝና አስርን አብሮ መፆምን ብዙ ዐሊሞች ይወደዳል ብለዋል (ከነርሱም መካከል) ኢማሙ ማሊክ፣ኢማሙ ሻፊዒይና ኢማሙ አሕመድ»

ምንጭ【ሶሒሁ ፊቂሂ ሱናህ (2/121)】

ከላይ ያሳለፍነው ሐዲሥ ከከሀዲዎች ጋር መመሳሰል በሸሪዓችን ክልክል እንደሆነ መረጃ ነው።ሸሪዓ እንድህ በዒባዳቸው እንኳ እንዳንመሳሰል ይከለክለናል ዛሬ የሚያሳዝነው ብዙው ወጣት በሚሰሩት ሀራም እና ፀያፍ ተግባራቸው ሳይቀር ይከተላቸዋል ውርደት ማለት እሄነው። አላህ ከውርደት ይጠብቀን

ቀደምቶቻችን የዐሹራእን ፆም በአስቸጋሪ ሆኔታ እንኳ ቢሆኑም ይፆሙት ነበር

ኢማም ዙህርይ ሙሳፊር(መንገደኛ) ሁነው ሳለ የዓሹራን ፆም ፆሙ
ለርሳቸውም "አንቱ በመንገድ ላይ ስትሆኑ ከረመዳን ፆም እያፈጠርኩ ለምን (በመንገድ ላይ ስትሆኑ) ዓሹራን ትፆማለሁ" ተባላቸው

"ረመዷን በሌላ ቀን (የቀዷ ማውጫ) ግዜ አለው ዓሹራእ ግን ያልፋል (የማካካሻ ቀን የለውም)
በማለት መለሱ

【ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ (5/342)】

በዚህ የዐሹራ ቀን ሁለት ቡድኖች ተሳስተው ጠመዋል

የመጀመሪያዎቹ:-
ዓሹራእን ልክ እንደ ዒድ ወን አድርጎ በመያዝ በዚህ ቀን አድስ ልብስ ይልብሳሉ የተለየ ምግብ ያዘጋጃሉ እንድሁም በመኳኳልና በመቀባባት ይበጃጃሉ አንዳንዶቹም መውሊድ በማድረግ ይደግሳሉ ይህ ሁሉ ረሱል(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንድንሰራው ያላዘዙን ጥመትና ቢድዓ ነው። ከእንድህ አይነት ጥፋት እኛም ቤተሰቦቻችንም ልንርቅ ይገባናል።

ሁለተኞቹ:-
አንጃዎች ደግሞ እሄን ቀን ሑሰይን ኢብኑ ዐሊይ(ረዲዬሏሁ ዐንሁ) የተገደለበት ቀን ነው በማለት የአዘን እና የለቅሶ ቀን አደረጉት በዚህቀን አዝነው ተግዘው ሲያለቅሱ ሌሎችም የጃሂልያ ተግባር ሲያደርጉ ይውላሉ ይህም በሸሪዓ ያልተደነገገ ጥመት ነው።

አሏህ በእነዚህ ሁለት የጠፉ አንጃዎች መካከል አህሉሱኖችን ለቀጥተኛው መንገድ መራቸው እሄንቀን ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳዘዟቸው በመፆም እና ሌሎችንም የተደነገጉ ዒባዳዎች በማድረግ ያሳልፉታል

የዐሹራእ ፆም ትሩፋቱና ምክኒያቱ እሄን ይመስላል ወሏሁ አዕለም


ዋናዉ ፃሙ የሚጀምረው ሰኞ ሲሆን
ዘጠነኛዉ ደግሞ እሁድ ነዉ።»

ኢብኑ ሙሐመድዘይን
683 views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ