Get Mystery Box with random crypto!

ሦስት ነገሮች ያለ ቀጠሮ ነው የሚመጡት። ሲሳይ፣ ሞት፣ እና ቀደር። ሲሳይህን ሰማይ ይሁን ምድር | Ethiopian Muslim Network

ሦስት ነገሮች ያለ ቀጠሮ ነው የሚመጡት። ሲሳይ፣ ሞት፣ እና ቀደር።

ሲሳይህን ሰማይ ይሁን ምድር አንተ ቦታዉን አታውቀዉም፤ እሱ ግን ያለህበት አይጠፋዉምና ድንገት ከተፍ ሊል ይችላል። አንተ ግን ተስፋ አትቁረጥ። ይመጣል ብለህ ማሰብ ነው።

የሞት ቀንህ አልተነገረህም ፤ መለከል መውት ሳታስበው ድንገት ደርሶ ሊይዝህ ይችላል ። ጣጣህን ጨርሰህ ዝግጁ ሆነህ መጠበቅ ነው።

ቀደር - በቀን ይሁን በማታ ዉስጥ አላህ ምን እንደወሰንልህ አታውቅም ፤ ድንገት ያላሰብከው ነገር ሊፈጠር ይችላል ። እሱ ሁሌም ሥራ ላይ ነው። ጥሩ ይሁን መጥፎ እሱ የለቀቀልህን መውደድ ነው። ለዚህም ሁሌ ዝግጁ ሁን።
መልካም ጁምዓ።

https://t.me/EthiopianMuslimNetwork