Get Mystery Box with random crypto!

ነቢዩ(ሰዐወ) ልብሱ የቆሸሸን ሰው ባዩ ጊዜ 'ይህ ሰው ልብሱን የሚያጥብበት ውኋ አጥቶ ነው እንዴ? | Ethiopian Muslim Network

ነቢዩ(ሰዐወ) ልብሱ የቆሸሸን ሰው ባዩ ጊዜ "ይህ ሰው ልብሱን የሚያጥብበት ውኋ አጥቶ ነው እንዴ?!" በማለት ሁኔታውን አውግዘዋል።

ጸጉሩ የተንጨባረረ ሰው ባዩ ጊዜም
"ይህ ሰው ጸጉሩን የሚያስተካክልበት (ቅባትና ማበጠሪያ) አጥቶ ነው እንዴ?!" ብለዋል። አቡ ዳውድ 4062።

ኢስላም ውስጥን በዒባዳና በተውበት፣ ውጭን በውሃና በልብስ እንድናሳምር ያዛል። ጁሙዓህ ቀን ላይ ደግሞ ገላን መታጠብ፣ ንጹህ ልብስ መልበስና ለወንዶች ሽቶ መቀባት ይበልጥ ይወደዳል፤ ትልቅ ምንዳም ያስገኛል።
ይህም በትክክለኛ ሐዲሥ ከነቢዩ ተነግሯል።
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
ዛዱል-መዓድ