Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianarchitectureandurbanism — Ethiopian Architecture Construction and Urbanism E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianarchitectureandurbanism — Ethiopian Architecture Construction and Urbanism
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianarchitectureandurbanism
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.68K
የሰርጥ መግለጫ

It is a platform for information on historical and contemporary architecture, urbanism, landscape, and the construction industry inside Ethiopia. It will also include similar issues from across the world.

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 23:30:13 ዘላቂ ውስጣዊ ንድፍ (መጽሀፍ)

Sustainable Interiors. A practical guide for Architects and Designers በሚል ርዕስ ዘላቂ የውስጣዊ ንድፍ ለመንደፍ የሚያግዙንን መሰረታዊ እሳቤዎች ጠቅለል እና መጠን አድርጎ የሚያወራ ባለ47 ገጽ መጽሀፍ አውርዶ ማንበብ ይቻላል።

ማሳሰብያ። በዚህ ጣብያ ላይ የምናያይዛቸው መጻህፍት፣ መጽሄቶችና የምርምር ወረቀቶች በሙሉ በነጻ እንዲወርዱ የተፈቀዱትን ሲሆን ፥ ያ ካልሆነ ደግሞ የቅጂ መብታቸው ከዘመን ብዛት ያለፉትን ብቻ መሆኑን እናስታውቃለን።

#ዘላቂውስጣዊንድፍ

ምንጭ። ugreen.io

@ethiopianarchitectureandurbanism
145 viewsedited  20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:53:31 የፒኤችዲ (PhD) ትምህርት ለመቀጠል አስበዋል?

የ2023/2024 የጀርመን የትምህርት ልውውጥ አገልግሎት (DAAD) ለዶክትሬት እጩዎች የሚሆን የምርምር ድጋፍ ዕድሎችን ፍላጎቱ ላላቸው አመልካቾች ክፍት አድርጏል::

- የትምህርት ድጋፉ የሚመለከታቸው:-

የዶክትሬት ትምህርታቸውን በሙሉ ሰዓት በጀርመን ሃገር ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ወይም የፒኤችዲ የጥናት ምርምራቸውን የተወሰነ ክፍል በጀርመን ማከናወን የሚፈልጉ ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ላሉ ወጣት ተመራማሪዎች እና ፒኤችዲ ለመስራት ለሚፈልጉ ተማሪዎች፣

- እነዚህ የትምህርት ዕድሎች፣ ከኬንያ-ጀርመን የድህረ ምረቃ ፕሮግራም በስተቀር ለሁሉም መስኮች እና ርዕሶች ክፍት ናቸው።
- የዕድሜ ገደብ የለውም፣ ነገር ግን በማመልከቻው ጊዜ የቀድሞው ዲግሪ ከ 6 ዓመት በላይ ያልበለጠ መሆን አለበት።
- በጣም አስፈላጊ የማመልከቻ መስፈርቶች:- ከ10-15 ገጽ የሆነ የምርምር ፕሮፖዛል እና ጀርመን ሃገር ካለ ፕሮፈሰር የማማከር ወይም የክትትል ማረጋገጫ ወይም በጀርመን ለሚገኝ ዩኒቨርስቲ የፒኤችዲ ፕሮግራም የሚሆን የመግቢያ ደብዳቤ ናቸው።

የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 31 ቀን፣ 2022 እ.ኤ.አ. ነው።

ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን መስፈንጠሪያ ይመልከቱ:- https://www.daad.or.ke/files/2022/08/PhD-in-Germany.pdf

ምንጭ። ጀርመን ኤምባሲ አዲስ አበባ ፌቡ ገጽ

@ethiopianarchitectureandurbanism
663 viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:49:14 ሦስት የሕንጻ ቀለማት ለሙከራ ተመርጠዋል።


ማክሰኞ ነሐሴ 24 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ)

የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ሦስት አይነት የሕንጻ መቀቢያ ቀለማት ለሙከራ መመረጣቸውን ገለጸ፡፡

የመዲናዋን የውበት ደረጃ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ የሕንጻ ቀለም መምርጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ሦስት አይነት ቀለማት ለሙከራ መመረጣቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የሕንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሄኖክ ለጋሳይ ተናግረዋል፡፡

የተመረጡት ቀለማት ግሬይ (ግራጫ)፤ ነጭ እና አልሙኒየም መሆናቸውን ተቋሙ በዛሬው ዕለት በአዜማን ሆቴል በሰጠው መግለጫ ላይ ሄኖክ አብራርተዋል፡፡

ጥናት ላይ መሰረት ተደርጎ ነው የቀለማት ምርጫ የተደረገው ያሉት ሄኖክ፤ ለአብነትም 65 በመቶ የሚሆነው ሕዝቦች የግራጫ ቀለም ተጠቃሚዎች መሆናቸው በጥናት ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

በከተማዋ የሚሰተዋለው የሕንጻ ቀለም ቅብ ዝብርቅርቅ በመሆኑ የከተማዋን ውበት ሳያደበዝዝ አልቀረም የተባለ ሲሆን፤ ሥርዓታዊ በሆነ መልኩ ሦስቱን ቀለማት በመጠቀም የከተማዋን ውበት ለማዘመን ይቻላል ነው የተባለው፡፡

ሦስቱን ቀለማት በማስማማት በተለያዩ ቀይ፤ ቢጫና ሌሎች ደማቅ ቀለማት የተቀቡትን ሕንጻዎች ማስዋብ ሙከራ እንደሚደረግና የማሕበረሰቡን አስተያየት መሰረት በማድረግ እንየኹኔታው ማስተካከያ እንደሚሰጥም ተብራርቷል፡፡

ከተማችን የአለማቀፍ ድፕሎማቶች መገኛ ናት ያሉት ሄኖክ፤ ጅማሮው ሕንጻዎች በየፈርጃቸው ውጥነት ባለው ቀለም ተቀብተው ደረጃቸው በመጠበቅ ለእይታ ሳቢ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ስለመገኘቱም አንስተዋል፡፡

ቀለማቱ ቋሚነት የሚኖራቸው በሙከራ ከታዩ በኋላ በሚገኘው አስተያየት ነው የተባለ ሲሆን፤ አልሙኒየም ቀለም በቸርችል ጎዳና ስለመሞከሩም ለአብነት ተነስቷል፡፡

ተቋሙ በነበረው መግለጫ የከተማዋን ውበት ያደበዘዙ ተለጣፊ፤ ተንጠልጣይ እና ማስታዎቂያዎችን በተመለከተም ማሻሻያ እንደሚደረግና እየተደረገ መሆኑን ዳይሬክተሩ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡

በኢዮብ ትኩዬ

ምንጭ አዲስ ማለዳ
@ethiopianarchitectureandurbanism
593 viewsedited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:40:06
649 views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:40:02 የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ከወጣ በኋላ ምርቱ ገበያ ላይ አለመኖሩ ተገለጸ

አዲስ ማለዳ
27/08/2022

የሲሚንቶ ምርቶችን ግብይት እና ስርጭት ስርዓት የሚደነግገው መመሪያ ከወጣ በኋላ በብዙ ከተሞች የሲሚንቶ ምርቶች አለመኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከተጠቃሚዎች እና ከምርት አከፋፋዮች አረጋግጣለች።

ይህ የሆነውም በመመሪያው የተላለፈው የሲሚንቶ ምርቶች ጊዜያዊ የመሸጫ ዋጋ ለነጋዴዎች አዋጭ አይደለም በሚል እንደሆነም ተገልጿል።

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ለሥርጭቱ የተመረጡ አንድ ወኪል ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ እኔ እንዳከፋፍል የተመረጥኩት ከዞን ከተማ 80 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላለው ማኅበረሰብ ነው።

ይሁን እንጂ ሲሚንቶ እንዳመጣና እንዳከፋፍል የተጠየኩት አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ40 ብር የትራንስፖርት ዋጋ ነው። ከዚህ ቀደም እንኳን ከ80 ብር በታች ስለማይጫን የትራንስፖርት ዋጋውን ስታስተካክሉ ጥሩኝ ብዬ ትቻቸው ወጣሁ ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በዚህም እርሳቸው አከፋፋይ ሆነው በተመረጡበት የወረዳ ከተማ ለተጠቃሚው የሚደርስ ምንም ዓይነት የሲሚንቶ ምርት እንደሌለ ነው የተናገሩት። የሚፈልጉ አካላት ከዞን ከተማ ነው ከመመሪያው ውጪ ከሚሸጥ ሲሚንቶ ከ1 ሺሕ 500 ብር በላይ ገዝተው የሚያስመጡትም ሲሉ ተደምጠዋል።

በመዲናዋ የሚገኝ የአንድ ትልቅ ንግድ ድርጅት ተወካይ በበኩላቸው፣ ድርጅታችን ለኮንስትራክሽን ሥራ የሚያስፈልገውን ሲሚንቶ ለማግኘት ከአከፋፋይ በደብዳቤ ቢጠይቅም ሲሚንቶ የለም የሚል ምላሽ ነው ያገኘው ሲሉ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ለግዥ የሚመጡ ተጠቃሚዎችን ሲሚንቶ የለም ሲሉ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በመመሪያው የተቀመጠው መሸጫ ዋጋ አዋጭ ባለመሆኑ ሲሚንቶ አላስገባንም የሚል ነው።

ምንጭ። addismaleda.com

@ethiopianarchitectureandurbanism
628 viewsedited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:27:33
የትኛውን ሶፍትዌር ልምረጥ?

እንደ ህንጻ ወይም ከተማ ነዳፊ የትኛውን ሶፍትዌር መርጬ ልጠበብበት የሚል ጥያቄ ይኖረዋል። አንድ በንድፍ ስራ የተሰማራ  ነዳፊ ቢያንስ ከ5-6 ፕሮግራሞችን ማወቅ ይጠበቅበታል።  ባለ ሶስት ደርዝ  ምስልን ለመገንባት፣ (3D modelling) ፣ ዝርዝር ወስኔ ንድፍ ግንባታ (parametric modelling)  ለማጎልበት እና ለመሳሰሉት   ደግሞ እነዚህ ፕሮግራሞች ላይበቁ ይችላሉ።

የሚያስፈልጉንን ሶፍትዌሮች ለመረዳትና ተያያዥነታቸውን ለመመልከት ሶፍትዌሮች በሚከተለው መንገድ የተከፋፈሉ ሲሆን በስራችን የሚገጥሙንን ችግሮች ለመፍታት ከዝርዝሮቹ መርጠን ራሳችንን ማስተማር ይኖርብናል።

1. ሁለት አውታር ንድፍ ገለጻ ( 2D Drafting)
2. ሶስት አውታር ንድፍ ግንባታ (3D modelling)
3. ዝርዝር ወስኔ ንድፍ ገለጻ እና እይታ ፕሮግራሚንግ (Parametric modelling and visual programing)
4. ሶስት አውታር ንድፍ ገለጻ ( 3D visualization)
5. እይታ አቅርቦት፣ ስእልና አውታር ንድፍ ( Presentation, graphics and layout design)
6. ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ድምጽና፣ እውነታ መሰል እንቅስቃሴ ( Video, sound and animation)


ምንጭ። studioalternativi

@ethiopianarchitectureandurbanism
577 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:37:54
ለፌሽታ ግዜ የሚሆን የመዋኛ ገንዳ ንድፍ ምሳሌ

ምንጭ። @lf_bayarea

@ethiopianarchitectureandurbanism
534 viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:25:29
597 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:25:29
በቅርቡ የሚመረቀው የአዲስ አበባው 5 ኮከብ ሃይሌ ሪዞርት።

በላምበረት አካባቢ የተገነባው ግራንድ ሀይሌ ሪዞርት የሚከተሉት ይኖሩታል

ባለ ዘጠኝ ወለል
160 የመኝታ ክፍሎች ፤
ስታንዳርድ እና ፕሬዝደንሺያል ክፍሎች
የመዋኛ ገንዳ ፤ ጂምናዝየም ፤ ቅርጫት ኳስ ፤ የቤት ውስጥ እግር ኳስ የጠረጴዛ ቴኒስ መጫወቻዎች እና የምሽት ክበብ
300 መኪኖች የሚይዝ ማቆምያ

ምንጭ፦ ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ፣ Haile Grand- Addis Ababa

@ethiopianarchitectureandurbanism
636 views06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:13:51
407 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ