Get Mystery Box with random crypto!

የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ከወጣ በኋላ ምርቱ ገበያ ላይ አለመኖሩ ተገለጸ አዲስ ማለዳ 27/08/2 | Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ከወጣ በኋላ ምርቱ ገበያ ላይ አለመኖሩ ተገለጸ

አዲስ ማለዳ
27/08/2022

የሲሚንቶ ምርቶችን ግብይት እና ስርጭት ስርዓት የሚደነግገው መመሪያ ከወጣ በኋላ በብዙ ከተሞች የሲሚንቶ ምርቶች አለመኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከተጠቃሚዎች እና ከምርት አከፋፋዮች አረጋግጣለች።

ይህ የሆነውም በመመሪያው የተላለፈው የሲሚንቶ ምርቶች ጊዜያዊ የመሸጫ ዋጋ ለነጋዴዎች አዋጭ አይደለም በሚል እንደሆነም ተገልጿል።

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ለሥርጭቱ የተመረጡ አንድ ወኪል ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ እኔ እንዳከፋፍል የተመረጥኩት ከዞን ከተማ 80 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላለው ማኅበረሰብ ነው።

ይሁን እንጂ ሲሚንቶ እንዳመጣና እንዳከፋፍል የተጠየኩት አንድ ኩንታል ሲሚንቶ በ40 ብር የትራንስፖርት ዋጋ ነው። ከዚህ ቀደም እንኳን ከ80 ብር በታች ስለማይጫን የትራንስፖርት ዋጋውን ስታስተካክሉ ጥሩኝ ብዬ ትቻቸው ወጣሁ ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

በዚህም እርሳቸው አከፋፋይ ሆነው በተመረጡበት የወረዳ ከተማ ለተጠቃሚው የሚደርስ ምንም ዓይነት የሲሚንቶ ምርት እንደሌለ ነው የተናገሩት። የሚፈልጉ አካላት ከዞን ከተማ ነው ከመመሪያው ውጪ ከሚሸጥ ሲሚንቶ ከ1 ሺሕ 500 ብር በላይ ገዝተው የሚያስመጡትም ሲሉ ተደምጠዋል።

በመዲናዋ የሚገኝ የአንድ ትልቅ ንግድ ድርጅት ተወካይ በበኩላቸው፣ ድርጅታችን ለኮንስትራክሽን ሥራ የሚያስፈልገውን ሲሚንቶ ለማግኘት ከአከፋፋይ በደብዳቤ ቢጠይቅም ሲሚንቶ የለም የሚል ምላሽ ነው ያገኘው ሲሉ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የሲሚንቶ አከፋፋዮች ለግዥ የሚመጡ ተጠቃሚዎችን ሲሚንቶ የለም ሲሉ አዲስ ማለዳ ተመልክታለች። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በመመሪያው የተቀመጠው መሸጫ ዋጋ አዋጭ ባለመሆኑ ሲሚንቶ አላስገባንም የሚል ነው።

ምንጭ። addismaleda.com

@ethiopianarchitectureandurbanism