Get Mystery Box with random crypto!

የፒኤችዲ (PhD) ትምህርት ለመቀጠል አስበዋል? የ2023/2024 የጀርመን የትምህርት ልውውጥ | Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

የፒኤችዲ (PhD) ትምህርት ለመቀጠል አስበዋል?

የ2023/2024 የጀርመን የትምህርት ልውውጥ አገልግሎት (DAAD) ለዶክትሬት እጩዎች የሚሆን የምርምር ድጋፍ ዕድሎችን ፍላጎቱ ላላቸው አመልካቾች ክፍት አድርጏል::

- የትምህርት ድጋፉ የሚመለከታቸው:-

የዶክትሬት ትምህርታቸውን በሙሉ ሰዓት በጀርመን ሃገር ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ወይም የፒኤችዲ የጥናት ምርምራቸውን የተወሰነ ክፍል በጀርመን ማከናወን የሚፈልጉ ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ላሉ ወጣት ተመራማሪዎች እና ፒኤችዲ ለመስራት ለሚፈልጉ ተማሪዎች፣

- እነዚህ የትምህርት ዕድሎች፣ ከኬንያ-ጀርመን የድህረ ምረቃ ፕሮግራም በስተቀር ለሁሉም መስኮች እና ርዕሶች ክፍት ናቸው።
- የዕድሜ ገደብ የለውም፣ ነገር ግን በማመልከቻው ጊዜ የቀድሞው ዲግሪ ከ 6 ዓመት በላይ ያልበለጠ መሆን አለበት።
- በጣም አስፈላጊ የማመልከቻ መስፈርቶች:- ከ10-15 ገጽ የሆነ የምርምር ፕሮፖዛል እና ጀርመን ሃገር ካለ ፕሮፈሰር የማማከር ወይም የክትትል ማረጋገጫ ወይም በጀርመን ለሚገኝ ዩኒቨርስቲ የፒኤችዲ ፕሮግራም የሚሆን የመግቢያ ደብዳቤ ናቸው።

የማመልከቻው የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 31 ቀን፣ 2022 እ.ኤ.አ. ነው።

ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን መስፈንጠሪያ ይመልከቱ:- https://www.daad.or.ke/files/2022/08/PhD-in-Germany.pdf

ምንጭ። ጀርመን ኤምባሲ አዲስ አበባ ፌቡ ገጽ

@ethiopianarchitectureandurbanism