2022-08-26 18:41:57
#EthiopiaCheck የአርብ የሚድያ ዳሰሳ
1. የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ወዳጆ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012ን በመተላለፍ መከሰሳቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። በዘገባው መሰረት ረዳት ፕሮፌሰሩ የአዋጁን አንቀጽ 4፣ 5 እና 7(4) ን በመተላለፍ ነው ክስ የቀረበባቸው። ክሱን የመሰረተው የሶዶ ከተማ አቃቤ ህግ ተከሳሹ ከ5 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገጹ ሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክት አሰራጭቷል ሲል ወንጅሏል። አዲስ ስታንዳር ያነጋገራቸው የተከሳሹ ባለቤት አዋጁ ከመጣቱ በፊት በረዳት ፕሮፌሰሩ የፌስቡክ ገጽ የተጋሩ መልዕክቶች በክሱ መካተታቸውን አመልክተዋል።
2. የሰራዊቱን እንቅስቃሴዎች የተመለከቱ የተዛቡ መረጃዎችን የሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ማክሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። መግለጫው “ይህንን ተግባር በግዴለሽነት ወይም በማንአለብኝነት የሚቀጥሉና የማይታረሙ ካሉ” መከላከያ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድና የወንጀል ክስ ለመመስረት እንደሚገደድም አስነብቧል።
3. የናይጄሪያ የመረጃ አጣሪዎች ጥምረት (Nigerian Fact-Checkers Coalition) በሀገሪቱ በመጭው የፈረንጆች አመት የሚደረገው ምርጫ ከሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች የጸዳ ይሆን ዘንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቋል። ጥምረቱ በሳምንቱ አጋማሽ ባወጣው መግለጫ የምርጫ ቅስቀሳ የፊታችን መስከረም እንደሚጀመር አስታውሶ ሆኖም ከአሁኑ ምርጫን የተመለከቱ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የመጨምር ዝንባሌ ማሳየቱ እንዳሳሰበው ገልጿል። የናይጄሪያ የመረጃ አጣሪዎች ጥምረት አፍሪካ ቼክን ጨምሮ ስምንት አባላት አካቷል።
4. አንድ የብራዚል ፍርድ ቤት የሀገሪቱ ፕሬዝደንት አሰራጭተውታል ያለውን የተዛባ መረጃ ከፕሬዝደንቱ የግል የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችና ከመንግስት ገጾች እንዲሰረዝ የሚያዝ ብያኔ ማስተላለፉን ዘ-ብራዚሊያን ሪፖርት ድረ-ገጽ ዘግቧል። የብራዚል ልዩ የምርጫ ጉዳዮች ፍርድ ቤት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ፕሬዝደንት ቦልሶናሮ “የሀገሪቱ የኤሌክትሮኒክ የምርጫ ስርዐት ሊስጠለፍ የሚችል ነው” በማለት የተሳሳተ መረጃ አሰራጭተዋል በማለት ነው። ብራዚል በመጭው ጥቅምት ወር ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ታደርጋለች።
በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌራም ሊንኮቻቸው:
- በሰኞ መልዕክታችን በሃቅና በአስተያየት መካከል ያለውን ልዩነት የሚያስቃኝ ጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አቅርበናል: https://t.me/ethiopiacheck/1488
- በተመሳሳይ ቀን “የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል” ከሚል ፅሁፍ ጋር በስፋት የተጋራ ምስል የተቀናበረ መሆኑን የሚያስነብብ መረጃ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1490
- ማክሰኞ ዕለት በተደጋጋሚ በአፋን ኦሮሞ ሀሠተኛ መረጃ የሚያሰራጭን የዩትዩብ ቻናል የሚያጋልጥ መረጃ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1492
- በትናንትናው ዕለት ደግሞ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ስምና ምስል በመጠቀም ስለተከፈተ ሀሠተኛ ገጽ መረጃ አቅርበናል: https://t.me/ethiopiacheck/1494
- እንዲሁም “የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል ማን ምን ሚና ሊጫወት ይገባል?’ በሚል ርዕስ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በትግርኛ የተዘጋጁ ቪዲዮዎችን አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1493
https://t.me/ethiopiacheck/1496
https://t.me/ethiopiacheck/1495
@EthiopiaCheck
5.9K views15:41