2022-09-16 18:54:29
#EthiopiaCheck የአርብ የሚድያ ዳሰሳ
1. ግዙፎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሜታ፣ አልፋቤት፣ ማይክሮሶፍት እና አማዞን በኢንተርኔት አማካኝነት የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን ለመቀነስ ይረዳሉ የተባሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ማቀዳቸውን በትናትናው ዕለት በዋይት ሀውስ በተደረገ ጉባዔ ላይ ይፋ አድርገዋል። ኩባንያዎቹ የጥላቻ ንግግር እያስከተለ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት አዳዲስ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለማድረግ፣ በተለይ በታዳጊዎችና በወጣቶች ላይ ያተኮሩ የሚዲያ አጠቃቀም ንቃትን ላይ ለመስራት፣ ምርምሮችን ለመደገፍ እና ሌሎችንም እርምጃዎች ለመውሰድ ማሰባቸውን ገልጸዋል። በጸረ-ጥላቻ ላይ ባተኮረው የትናንቱ ጉባዔ የዩናይትድ ስቴት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ሰላባ የሆኑ ግለሰቦችና ቤተሰቦች የተገኙበት ነበር።
2. በቲክቶክ ከሚታዩ አምስት የፍለጋ ውጤቶች (search results) አንዱ ሀሠተኛ፣ የተዛባ ወይም አሳሳች ይዘት መሆኑን ያደረኩት ጥናት አሳይቷል ሲል ኒውስጋርድ (NewsGuard) የተባለ ተቋም ይፋ አድርጓል። ተቋሙ ኮቪድ-19ን፣ የአየር ንብረት ለውጥን፣ ምርጫን እንዲሁም የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት የተመለከቱ ይዘቶችን ለጥናቱ መጠቀሙን ገልጿል። በተጨማሪም የቲክቶክ የፍለጋ ውጤቶች ከጎጎል የፍለጋ ውጤቶች አንጻር ከፍ ያለ የሀሠተኛ፣ የተዛባ ወይም የተሳሳተ ይዘት እንዳሳዩ ተመልክቻለሁ ብሏል።
3. የትዊተር ባለድርሻዎች ኩባንያው ለባለጸጋው ኢሉን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር እንዲሸጥ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ ማጽደቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ውሳኔው ከግዥው ለመውጣት አፈግፍጓል የተባለውን ኢሉን መስክ ግዥውን እንዲፈጽም ለማስገደድ ያለመ መሆኑ በዘገባው ተካቷል። በዚህም ኩባንያውና ኢሉን መስክ የፍርድ ቤት ሙግታቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል። ሁለቱ ወገኖች በፕላትፎርሙ የቦቶች ምጣኔ ባለመስማማታቸው ምክንያት ወደ ፍርቤት ማቅናታቸው ይታወቃል።
4. የአየር ንብረት በጥላቻ ንግግር ስርጭት ላይ የራሱ የሆነ ተጽኖ እንዳለው መቀመጫውን ጀርመን ያደረገው የፖስትዳም የአየር ንብረት ጥናት ተቋም (Potsdam Institute for Climate Impact Research) ከቀናት በፊት ይፋ ያደረገው ጥናት አሳይቷል። ጥናቱ በትዊተር በሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ሞቃታማ በነበሩ ቀናቶች (ከ42 ዲግሪ ሴንትግሬድ በላይ) በፕላትፎርሙ የተሰራጩ የጥላቻ ንግግሮች በ22% ከፍ ማለታቸውን አስነብቧል። እንዲሁም ቀዝቃዛ በነበሩ ጊዜያት የስርጭት መጠኑ በ12% ጭማሪ ማሳየቱን የጥናት ውጤቱ አሳይቷል። ተቋሙ እ.አ.አ ከግንቦት 1/2014 እስከ ግንቦት 1/2020 ዓ.ም አድራሻቸው የተለየ (geolocated) 4 ቢሊዮን ትዊቶችን በናሙናነት መጠቀሙ ተገልጿል።
በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌራም ሊንኮቻቸው:
- በሰኞ መልዕክታችን ሀሠተኛና የተዛቡ መልዕክቶችን በተመለከተ በአዲሱ አመት ማድረግ ያለብንን ጥንቃቄ የተመለከተ ጽሁፍ በአፋን ኦሮሞ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1534
- እንዲሁም በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም ወጣ የተባለን ሠተኛ መግለጫ አጋልጠናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1535
https://t.me/ethiopiacheck/1537
- በተመሳሳይ ቀን በኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የጥቆማ መቀበያ ስልክን የተመለከተ ማብራሪያ ወደናንተ አድርሷል:
https://t.me/ethiopiacheck/1539
- ማክሰኞ ዕለት ከረጅም ቪድዮዎች ላይ ተቆርጠው የሚጋሩ አጠር ያሉ ቪዲዮዎች ሊያሳስቱን ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን የሚያስታውስ ጽሁፍ በትግርኛ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1540
- ሀሙስ የሂጅራ ባንክን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ ሀሰተኛ የቴሌግራም ቻናሎች የተመለከተ ጽሁፍ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1541
- እንዲሁም የጋዜጠኛ መዓዛ ብሩን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈተ የትዊተር አካውንት መኖሩን አሳውቀናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1542
- በተጨማሪም በአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ስም እና ማህተም ተቀናብሮ እየተሰራጨ ያለ ሀሰተኛ ደብዳቤን የሚጋልጥ መረጃ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1544
@Ethiopiacheck
5.6K views15:54