2022-09-02 18:39:35
#EthiopiaCheck የአርብ የሚድያ ዳሰሳ
1. ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ነበር ባላቸው 111 የዲጂታል ሚዲያዎች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁን ኢቢሲ በሳምንቱ አጋማሽ ዘግቧል። ፖሊስ ሚዲያዎቹን “ህገ-ወጥ” በማለት የጠራቸው ሲሆን ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ኢትዮጵያን የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ ሲሠሩ ነበር ብሏል። የሚዲያዎቹ ማንነት በዘገባው አልተካተተም።
2. አስር የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆኑ ግለሰቦች መንግስታት ሀሠተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክት የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱ ዛሬ ባወጡት ባለ አስር ነጥብ ማኒፌስቶ ተማጽነዋል። የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊዎቹ ማኒፌስቶውን ይፋ ያደረጉት በኖርዌ ኦስሎ ከተማ በሚገኘው የሰላም ኖቤል ማዕከል በመካሄድ ላይ ባለው ሀሳብን በነጻነት መግለጽን በተመለከተ ኮንፈረንስ ላይ ነበር። ሎሬቶቹ ሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ መልዕክትን በዴሞክራሲ ህልውና ላይ የተቃጡ ጥቃቶች ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
3. የትዊተር ተጠቃሚዎች መልዕክት ካጋሩ በሗላ አርትዖ (edit) ማድረግ የሚያስችላቸውን አገልግሎት ለመጀምር ወደ ሙከራ መግባቱን ካምፓኒው በትናንትናው ዕለት አስታውቋል። በአገልግሎቱም የትዊተር ተጠቃሚዎች አርትዖ ማድረግ የሚችሉት መልዕክት ባጋሩ በ30 ደቂቃዎች ውስጥ ሲሆን የአርትዖ ስራ መስራታቸውን የሚገልጹ ምልክቶች ለተከታዮቻቸው በግልጽ እንዲታዩ ይደረጋል ተብሏል። አርትዖ የተደረገው መልዕክት ቅድመ-ታሪክንም (edit history) ማየት እንደሚቻል ትዊተር አስታውቋል።
4. የበለጸጉ ሀገራት ዜጎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን እንደዋነኛ የህልውና ስጋት እንደሚመለከቱት ፒው የጥናት ማዕከል (Pew Research Center) በሳምንቱ አጋማሽ ይፋ ያደረገው አንድ የዳሰሳ ጥናት አሳየ። ማዕከሉ የዳሰሳ ጥናቱን በ19 ከፍ ያለ ምጣኔ ሃብት ባላቸው አገሮች ያደረገ ሲሆን 24,525 ሰዎችን አሳትፏል። በውጤቱም ከአየር ንብረት ለውጥ በመቀጠል ሃሰተኛ መረጃ በዋና የህልውና ስጋትነት ተቀምጧል። ከሌሎች አገሮች የሚሰነዘር የሳይበር ጥቃት፣ የዓለም የምጣኔ ሃብት ሁኔታ እንዲሁም የተላላፊ በሽታዎች ስርጭት ቀጣይ ደረጃዎችን ይዘዋል።
በዚህ ሳምንት ያቀረብናቸው መረጃዎች እና የቴሌራም ሊንኮቻቸው:
- በሰኞ መልዕክታችን ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም የጥላቻ መልዕክቶችን ሪፖርት የማድረግ አስፈላጊነትንና ሂደቶችን የሚያስቃኝ ጽሁፍ በትግረኛ አጋርተናል: https://t.me/ethiopiacheck/1501
- እንዲሁም በተመሳሳይ ቀን ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያዘጋጃቸውን የሽልማት ፕሮግራሞች በመንተራስ የሌብነት ተግባር ከሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያሳስብ መረጃ አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/1502
- ከሳምንቱ አጋማሽ ጀምሮ እራሳችንን ከክሊክ አጥማጆች እንዴት መጠበቅ እንዳለብን የሚያስተምር ጽሁፍ በአማርኛ፣ በትግርኛና በአፋን ኦሮሞ አጋርተናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1503
https://t.me/ethiopiacheck/1511
https://t.me/ethiopiacheck/1513
- ዕረቡ ዕለት በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ስላሉ ኩባንያዎች እና ሰራተኞች ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስ ስ ጽሁፍ ወደናንተ አድርሰናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1506
- ትናንት በዩትዩብ ቻናሎች የሚተላለፉ መረጃዎችን ከማመናችን በፊት ልንጠይቃቸው የሚገቡ ነጥቦችን የተመለከተ ጽሁፍ አስነብበናል:
https://t.me/ethiopiacheck/1509
- ስለ ዲፕፌክ ምንነት የሚያሳዩና በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በትግረኛ የተዘጋጁ ቪዲዮዎችም በሳምንቱ ካጋራናቸው ይዘቶች መካከል ናቸው:
https://t.me/ethiopiacheck/1507
https://t.me/ethiopiacheck/1515
- ዛሬ የበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ኦፊሴላዊ የትዊተር አካውንትን የተመለከተ ዘገባን አስነብበናል: https://t.me/ethiopiacheck/1516
@EthiopiaCheck
3.1K views15:39