Get Mystery Box with random crypto!

#EthiopiaCheck Explainer በኦጋዴን ቤዚን እንደሚገኝ በጥናት የተረጋገጠዉ የተፈጥሮ | Ethiopia Check

#EthiopiaCheck Explainer

በኦጋዴን ቤዚን እንደሚገኝ በጥናት የተረጋገጠዉ የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት ምን ያክል ነዉ?

የማዕድን ሚኒስቴር በዛሬው እለት ኔዘርላንድ፤ ሲዌል ኤንድ አሶሺየተስ ኢንክ (NSAI) ከተሰኘ የአሜሪካ ካምፓኒ በኦጋዴን ቤዚን የሚገኘዉን የተፈጥሮ ጋዝ መጠንና የኢኮኖሚ አዋጭነት የማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተረክቧል።

ይህ ሰርተፊኬት በዓለም አቀፍ ደረጃ የቴክኖሎጂ፣ የፋይናንስ እና ነዳጅ ኢንቨስትመንት አቅም ያላቸው ኩባንያዎች መጋበዝ የሚያስችል እና የመንግስትን የመደራደር አቅም የሚያጎለብት እንደሆነ የማዕድን ሚኒስትሩን ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ አስፍረዋል።

ይሁን እንጂ በኦጋዴን ቤዚን ይገኛል ስለተባለዉ የተፈጥሮ ጋዝ መጠን ግልጽ ያልሆኑ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ሲጋሩ ተመልክተናል።

ይህም አንዳንድ ሚዲያዎችና ማህበራዊ ትስስር ገጾች “ ሰባት ትሪሊየን ጫማ ጥልቀት ያለው የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ” ሲሉ አንዳንዶች ደግሞ “ሰባት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ” ሲሉ ዘግበዋል።

ስለዚህም ሰባት ትሪሊዮን የምድር ዉስጥ ትልቀት ወይስ ብዛት (volume) የሚለዉን አወዛጋቢ አድርጎታል።

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ የማዕድን ሚኒስትሩን ኢንጂነር ታከለ ኡማ መረጃ የጠየቀ ሲሆን ትክክለኛ መረጃዉ ሰባት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የሚለዉ እንደሆነ አረጋግጠዋል።

ስለዚህ ጥናቱ በኦጋዴን ቤዚን በሶስት ጉርጓዶች ዉስጥ ሰባት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ ያረጋገጠ ነው ማለት ነዉ።

ይህ አራት ወራትን የፈጀዉ ሲዌል ኤንድ አሶሺየተስ ኢንክ (NSAI) ጥናት ከዚህ በፊት ሲነሳ ለቆየዉ “ምን ያክል የተፈጥሮ ጋዝ አለን” ለሚለዉ ጥያቄ ምላሽ የሰጠ እንደሆነ ተነግሯል።