Get Mystery Box with random crypto!

ታደሰ ደምሴ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia2123 — ታደሰ ደምሴ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia2123 — ታደሰ ደምሴ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopia2123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

ሥነ_ግጥም
ግጥሞችን በዩቱብ ለመከታተል👇👇👇
https://youtube.com/@maryam2116

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-22 17:51:55 እዛ ...
ቀን ያደላደለው  የፍቅር መኃልይ ረቂቅ ይነድፋል
ሌላኛው...
ውብ ገላ ታቅፎ ሀሴት ይጎነጫል
ከዚህ..
የኔ ቢጤ ምስኪን 
ህልሙ እየተቀማ በእምባ ይታጠባል


እዝጎ
344 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 15:45:17 ልጇን የጠረጠረ
የእናቱን አበሰረ"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ነፍሴና ጉልበቴ ይሉልሻል በርከክ
ውዳሴሀ ለእግዝትነ ማርያም
ዘይትነብብ በ'ለተ ሰርክ::

ሰኞ
ቶማስን ያየ
ከንቱ ነፍሴ ያስብሻል በሰመመን
ልጅሽን የጠረጠረ ባንቺ የተዘጋ ማመን::

ኦ ማርያም
ናፍቆት የመላዕክት
ኦ ማርያም
የአዳም ምልክት

ማክሰኞ
ብልህ ነው እግዜሩ ብቻ ሁሌ ጥሩት
በእናት ይመልሳል ልጅ ቢጠረጥሩት::

ኦ ማርያም
መነሳት በቅድስና
ኦ ማርያም
እንበለ ሙስና::

ረዕቡ
እንደሚከተለው የክፉ ቀን ወጥመድ
ከቀጭን ሽቦ ላይ ፈርቶ እንደሚራመድ
እንደዚያ ሰው አለሁ::

ኦ ማርያም
ፀጋ ትምክህቱ
ኦ ማርያም
ሚካኤል እህቱ::

ሐሙስ
እንደዚያ ሰው አለሁ
ጨለማ ባቅሙ ደፍሮ ሚያስጨንቀኝ
መቀነትሽ ታጥቆ ማንስ ባጠመቀኝ?

ኦ ማርያም
ብሳሳት ነፍሴን
ነፍስሽ ታንሳት::
ኦ ድንግል ሆይ
ማርያምን ብረሳት
ነፍሴን ቀኜ ትርሳት::

አርብ(ስቅላት)
አትሂጅ ትተሽኝ አኑሪኝ በግርግም
ግድ ሆኖብኝ እንጂ መኖር አልፈልግም ::
ግድ ሆኖብኝ እንጂ የምመላለሰው
ግድ ሆኖብኝ እንጂ አፈር የምልሰው
ያነጫንጨኛል
የእናቱን መዳፍ ከእጁ እንደቀሙት
ልረፍና ጥሪኝ ከጥላሽ ስር ልሙት::

ቅዳሜ
ፍቅርሽ የለው ጠረፍ
መንገዴ ይቅናና ጥሪኝ ልቤ ይረፍ::

እሁድ
ደከመኝ እኮ ጌታዬ ደከመኝ እኮ የኔ አምላክ
ወይ እንደሰው አይደለሁ? ወይም እንደመልአክ?
ደከመኝ እኮ ማርያም - ደከመኝ እኮ እማምላክ

ደከመኝ እኮ

(16-12-14)

@ethiopia2123
@ethiopia2123
360 viewsHáŷmî, edited  12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 09:18:37
ለኃይማኖቱ ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ትንሳዔ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ

መልካም በዓል!

@ethiopia2123
355 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 17:28:08 "ዝም በል"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ከሳሽህ ፊት ዘንበል
ሰዳቢህ ፊት ዘንበል
በነፍስህ ተናገር በቃልህ ዝም በል።

ዝም

እሺ በል አጎንብስ
ፊደል አታገግበስብስ
ዝም በል ጭጭ ጭጭ
ስንፍናን በልምጭ
ዝምታህን እቅጭ
አድርገህ ተቀበል
ዝም ብለህ አስጩህ እንደቅዱስ ፀበል::

አስብ ዝም ብለህ
እንደሊቅ ተራቀቅ
እንደንጉሥ ውደቅ::

ዝም ብለህ ሞክር
ዝም ብለህ ጨክን
ዝምበል ተንገዳገድ
ማስራዳት ሲያስብ ነው ሰው የሚወላገድ::

ዝም::

እግዜርን ተመልከት
ሊያስረዳህ ሲሞክር አታየውም ሲጥር
መች ብዙ አወራ ዓለምን ሲፈጥር።

(ዝም ብለህ ቀጥል

@ethiopia2123
400 viewsHáŷmî, 14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 13:50:15
"ለምን ይህ ሆነ አትበሉ!"
(ታደሰ ደምሴ)

ለክረምት ሌሊት ተልካ
ጨረቃን ደመና ቢያንቃት
ደቂቀ ሰራዊቶቿ
ከጠፈር ቢሸሹ ከዋክብት

ከሰማይ ጭነት ተዳምሮ
ጨለማ ግርማው ቢገዝፍ
የእይታይን ቅጽር ደርምሶ
በእውር በድንብር ቢቀዝፍ

በአምላክ ጥበብ ስር ገብታችሁ
ለመፍረድ አትቸኩሉ
"ህጻን የሰራው ስህተትነው"
ለምን ይህ ሆነ አትበሉ!

ሆኖ ያየነው በመላ ለኛ ቅል ጥፋት ቢመስልም
ማስተዋል ቸግሮን እንጂ
ተፈጥሮ ስህተት አያውቅም

ይልቅ...
ይልቅ...
እስኪ ሰፊልብ ግዙና መጨረሻዋን ታዘቡት
ለቁጣ ሳትቸኩሉ በአርምሞ ምሽግ ጠብቋት

አያችሁ...
አያችሁ...
የሽንፈት ክሯ ሲበጠስ
የመገለጥ ተራ ሲደርሳት
ያ ጸሊም ደመና ሸሽቶ
ዙሪያ ገባዋን ሲከባት
ምን ያክል አይን እንደገዛች፣
ምን ያክል ቀልብ እንደሳበች፣
መፍካትን ግምጃ ስታደርግ ጠለ_ጸዓዳ ዘንቦባት
በመወደድ ላይ መወደድ ከፍጥረት እንደጎበኛት!

#ሼርር
@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
633 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 15:58:44 አንድ ተራራ ነበር፣
ጽናት የሚጠይቅ~ጉልበት የሚፈትን
ግርጌ ሆኖ ላየው፣
ጠርዙ ይጨበጣል ቢባል ማይታመን
ደግሞ ግን ደግሞ ግን...
ደቂቅ የአዳም ልጆች፣
ጥጉን ከጅለውት ወጥተውት እናያለን!
እኛም የአሁኖቹ፣
እኛም ታናሾቹ፣
ከሸለቆ ወጥተን፣
ከማደባይ አርፈን፣
ከከፍታው ማማ ከጫፉ ተጓዥ ነን
ፊቶችን የረዳህ፣
ፊቶችን የደገፍህ፣
በአምሳለ ህሊና ግዳፍ ያደረግንህ ምርኩዝ ሆይ አበርታን!
ከጨለማ ማዶ ጎህን የምትሰብክ ተስፋ ሆይ አትክዳን!
:
:
:
አሜን!

#ሼርርርር
@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
538 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., edited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 07:53:47 ሰው ሁን በይኝ

በቀደም ለት ጉንጨ መሐል
በከንፈሯ በትዳብሰኝ፤
ሙት አካሌ ፊት እንዳለኝ አስታወሰኝ፤

ደሞ ድንገት ቀልድ ነግራኝ
ስቄ ስቄ እንዳባራሁ፤
''ጥርስህ ያምራል'' ስላለችኝ
ዘላለሜን ማልቀስ ፈራሁ፤

ተካተትኩኝ ከተፈጥሮ
እፍ ....አልሽብኝ ድብቅ ውበት፤
/እስቲ ባክሽ አሁን ደሞ/
'ሰው ሁን' ብለሽ ሹሚኝና
ሰው መሆኔ ልመንበት፤

ሰው ተብዬ ልጠራበት።

አስታወሰኝ ረጋሳ
#ወደ_ነገ_ሒያጅ_ነኝና

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
686 viewsHáŷmî, 04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:14:52 አንቺየ...
(ታደሰ ደምሴ)

እንዲያ...
አንቺን ፍለጋ ስባክን~ ተሳልቀሽ ስትሰወሪኝ
"አይኖችሽ እራቡኝ" ላልሁሽ~ገጽሽን ላላይ ስትነፍጊኝ

በንጹህ ልቤ በወደድሁ፣
በአንድያ አሳቤ ባፈቀርሁ፣

ካንቺ ከፍ አልልም ብየ~ ለመውደድ አጎብዳጅ ስሆን
አንቺኑ አግኝቸ ልባረክ~ ለፍቅርሽ ሳጣው እራሴን

ከጠማኝ ልሳን አፍልቀሽ ድንበር ተላልፈሽ ስትዘልፊኝ
በራቡኝ አይኖችሽ ግልምጫ የጎሪጥ ቢጤ ስትሾፊኝ

ፍላፃ ጦርሽን አውልቄ ከቀልቤ ልሆን ስቃጠር
ባስብሽ እርም እንዲሆነኝ ለአድባር ተስየ ሲሰምር

ዛሬ ላይ ዘመን ገልብጦሽ
ከትቢያ የፈረጅሽኝን የትናንት እኔን ቢያሰኝሽ

በተራሽ ፍለጋ ስትወጭ ላታይኝ ብደበቅብሽ
ሞገሴን ገዝፎ ብታይው ስለዚህ ለምን ገረመሽ
የዘራሽውን ገብስ እንጂ ያልዘራሽውን መች አጨድሽ

#ሼርርርር

@ethiopia2123
@ethiopia2123
@ethiopia2123
562 viewsአ.ቡ.ጊ.ዳ.., 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 08:14:34 #አንቺዬ... ...
ይዤሽ በወጣሁኝ ፣ በዚህ ድቅድቅ ምሽት
"ባሕር ያሞራል”፣ አትበይ ከኔ ልብ ሽሽት።
የባሕር ዳር ውበት ፣ በስሜትሽ ዐይተሽ
ጨረር አታድንቂ ፤ ጨረቃን ረስተሽ፤
ዕዪው... ልብ ብለሽ!
ባሕር ለጨረቃ ፣ ደረቱን ገልብጦ፤
የጨረቃ ጨረር፣ በባሕር ተውጦ፤
ሲግባቡ እያየሽ፣
አንቺ ግን ሔዋኔ
ብርሃን ፍላጋ ፣ጨለማ ላይ ቆየሽ።
ባሕር ምን ቢሰፋ ፣ጨረቃ ሞላችው
ጨረቃስ ብትሞቅ ፣ አላደረቀችው።
የመዋዋስ ፍቅር፣ከልባቸው ጠፍቶ
ሲሞላሉ ዐየሽ ፣ኀይሏቸው ሰፍቶ።
ተቃርኖ ተመልከች!
ጨረቃ ወላድ ናት፣ እናት ብርሃን፤
ባሕር ጨለማ ነው፤ የብልጭታ መሀን።
ተቃርኖ ተመልከች!
ባሕር ሕይወት አለው፤ ከሰው የረቀቀ፤
ጨረቃ ግን በድን ፣ ከሕይወት የራቀ።
የዋጡትን ዐየሽ...
የሌላትን ሕይወት በብርሃን ቀዘፋ
ጨረቃን ተመልከች ፣ ከባሕሩ ገዝፋ።
የዋጡትን ዐየሽ...
ሕይወትን ቢቀዝፍ ፤ ጨለማን ተዋርሶ፣
ዕድሜ ለጨረቃ...
ባሕሩን ተመልከች ፣ እስከሰማይ ደርሶ፡፡
ያዋጡትን ዐየሽ
ሕይወት ከጨለማ ፣ ጨለማ ከሕይወት፣
በድን ከብርሃን ፣ ብርሃን ከበደን
ሲሰጣጡ ጊዜ
ትንሿ ጨረቃ ፣ ባሕር ስትከድን።
ይዤሽ የወጣሁት ፣ በዚህ ድቅድቅ ሞሽት
ባሕር ያምራል አትበይ ፤ከኔ ልብ ሽሽት።
ጨረቃና ባሕር ፣ሲግባቡ ያስቃል፤
ያአዳሜ ና ሔዋን ፣ፍቅሩ በቃል ያልቃል።
ያዋጡትን ዐየሽ!


ኤልያስ ሽታኹን

@ethiopia2123
@ethiopia2123
552 viewsHáŷmî, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 22:11:08 ///ናፈቀን\\\
-------------------
በግዙፍ ታሪኳ
በድንግል አካሏ፤
ፍካሬው ደርሶባት
 የፊቱ ወደኋላ።
አላስነካም ብላ
ሀፍረቷን ብትሸፍን፤
ከልጆቿ ጠፍታ
አንዳች ሆነች ሚስጢር።
ተርጓሚው ሊፈታሽ
ቅኔውን ሲቆጥር፤
ጠቢቡ ቢጠበብ
አንዳች ሊያመሰጥር፤
እንደሙት ተቆጥረሽ
ጠላትሽ ሲከብር፤
ገደልኳት እያለ
ሲያቅራራ ሲፎክር፤
ሀገሬ ትንሳኤሽ
ከልጅ ልብ መቃብር።
ሶስት ቀን ረዝሞ
ሀዘን በዝቷል ደጅሽ፤
እሁድሽ ናፈቀን
ያ ውዱ ትንሳኤሽ።

abela_black

join
t.me/ethioia2123
t.me/ethiopia2123
t.me/ethiopia2123
509 viewsYibe Kasa, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ